የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ሆነ ብለው የነዳጅ ዕጥረት ያጋጠመ ለማስመሰል መሞከራቸውን በክትትል እንደደረሰበት ገልጧል፡፡
በሀገር ውስጥ በቂ የነዳጅ አቅርቦት መኖሩ እየታወቀ የነዳጅ ዕጥረት ይከሰታል የሚሉ አዋኪ መልዕክቶች ሆነ ተብሎ የሚነዙ መሆኑን ሕብረተሰቡ እንዲገነዘብ ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡
በቀጣይም በነዳጅ ማደያዎች ላይ የአገልግሎት አሰጣጥ መዘግየት እና ዕጥረት መፍጠርን የመሳሰሉ ችግሮች በሚፈጥሩ አካላት ላይ ክትትል በማድረግ አስተማሪ እርምጃ እንደሚወስድ ነው የገለጸው፡፡
በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ምክንያት ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም የሚያስችል አካውንት ካለመክፈት ጋር የተያያዘ እንጅ የነዳጅ ዕጥረት አለመሆኑንም ነው ባለስልጣኑ ያረጋገጠው ሲል ፋና ዘግቧል፡፡