ደቡብ ወሎ የሞርታር ተተኳሽ የደበቀው ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ

በአንድ ግለሰብ ቤት የሞርታር ተተኳሽ ተደብቆ መገኘቱን የአምባሰል ወረዳ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱን እንዳለው የሞርተር ከባድ መሳሪያ ተተኳሽ በፍተሻ የተገኘው በሕዝብ ጥቆማ ነው።

በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ልዩ ስሙ 02 ቀበሌ ጢሳ አባሊማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በግለሰብ ቤት ውስጥ ተገኘ የተባለው የሞርታር ተተኳሽ ብዛቱ 23 ነው። መገኘቱን የአምባሰል ወረዳ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በስምና በልዩ መለያ ስለማንነቱ ምንም ሳይገለጽ በቁጥጥር ስር የዋለው ግለስብ ሞርተር መደበቁ አስገራሚ ነደሆነ ዜናውን የሰሙ አመልክተዋል።

ከስምንት ኪሎሜትር በላይ ተሻግሮ መምታት የሚችል የሞርተር ተተኳሽ ሸሽጎ በጥቆማ የተደረሰበት ተጠርጣሪ በገለሰብ ደረጃ የማይያዝ መሳሪያ ደብቆ ያስቀመጠው ለምን ዓላማ እንደሆነ ከምርመራው በሁዋላ እንደሚታወቅ ተጠቁሟል። ተተኳሹ ካለ መተኮሻውስ የሚል ጥያቄም የሚያስነሳ ቢሆንም ጸህፈት ቤቱ ያለው ነገር የለም። የተገለጸው “ተተኳሹ ከኀብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በተደረገ ፍተሻ ተገኘ” በሚል ነው።

መሳሪያው የተገኘው እዚህ ቤት ውስጥ ነው።

ተተኳሹ የተገኘበት ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ ከአምባሰል ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ማመልከቱ በዜናው ተገልጿል። ደቡብ ወሎ ትህነግ ከትግራይ ቀጥሎ ስሩን የቀበረበት አካባቢ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚገለጽ መሆኑ ይታወሳል።Leave a Reply