ጫካ ገብተው የነበሩ ዜጎች እርቅ በመፈፀም ወደ ቤታቸው ተመለሱ

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር በጃዊ ወረዳ በተለያዩ ምክንያቶች ጫካ ገብተው የነበሩ ዜጎች እርቅ በመፈፀም ወደ ቤታቸው ተመለሱ

ከመንግስት ጋር ቅሬታ በመፍጠር ጫካ ገብተው የነበሩ ዜጎች በሀገር ሽማግሌዎች አደራዳሪነት እርቅ ፈፅመው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል።

እርቅ ፈፅመው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ሲያደራድሩ ከነበሩት የሀገር ሽማግሌዎች መካከል የጃዊ ወረዳ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ መጋቢ ሀዲስ ያረጋል አለነ እንደገለፁት ሰላም ለዜጎች መኖር ቁልፍ መሣሪያ ነው።

በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ጫካ የገቡት ዜጎች ከመንግስት ጋር ያላቸውን ችግር በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ በማድረጋቸውና በየደረጃው ከሚገኙ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ስምምነት ፈፅመው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ መደረጉን የቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

የተጀመረው ድርድር በዚህ የሚቆም ሳይሆን ከወረዳ ወረዳ፣ ከዞን ዞንና ከክልል ክልል ድረስ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር የሀገር ሽማግሌዎች ተግባሪን አጠናክረው ለመቀጠል አቅደው እየሠሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

መጋቢ ሀዲስ ያረጋል አለነ ሁሉም ዜጎች የሰላም አስፈላጊነትን በተገቢው መንገድ ተረድተው ለሰላም ዘብ እንዲቆሙ መልዕክት አስተላልፈዋል

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ ጌታቸው ቢሻው በመንግስት የስራ ኃላፊዎች ላይ ቅሬታ አንስተው ጫካ ገብተው የነበሩ ዜጎችን በሀገር ሽማግሌዎች አደራዳሪነት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንና ስምምነቱም በእለቱ በፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉትን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም የሚጨምር መሆኑን ገልፀዋል።

የተጀመረው ስምምነት ወደ ኋላ እንዳይመለስ የሀገር ሽማግሌዎችና አመራሩ አጠናክረው የሚሰሩ መሆኑን የመምሪያው ኃላፊ ተናግረዋል።

በፕሮግራሙ ላይ ያልተገኙት አባላት እንዲመጡ ለማድረግና ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱም የተገኙት አባላት መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።

በእለቱ 118 አባላት በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው በስምምነቱ ላይ የፈርሙ ሲሆን የያዙትን የነፍሰ ወከፍ መሣሪያ አስመዝግበው ሕገዊ ማድረግ ተችሏል።

See also  በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለው ግጭት ምንድነው?

Leave a Reply