ቻይና ውስጥ ሃያ ሺህ ህዝብ ዋጥ ያደረገው ህንጻ

በቻይና የሚገኝ ሬጀንት የተባለ አንድ አለም አቀፍ አፓርታማ 20 ሺ ሰዎችን በጉያው አቅፎ ያኖራል ፡፡ ይህ ጉደኛ አፓርታማ ይህን ሁሉ ሰው በአንድ ህንጻ ውስጥ አቅፎ መያዙ ጉድ አሰኝቷል፡፡ የአንድ ትንሽ ከተማ ያህል ነዋሪ አንድ አርጎ እና አቅፎ ደግፎ ማኖሩሰሚውን አጀብ አስብሏል፡፡

ቂያንጃንግ ሴንቸሪ በተባለ ከተማ የሚገነው በአለም ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ይህ አፓርታማ በእንግሊዘኛዋ ኤስ ፊደል ቅርጽ የታነጸ ነው፡፡ አፓርታማው መጀመሪያ ላይ ሲገነባ ለቅንጡ ሆቴልነት እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በኋላ ላይ ወደ አፓርታማነት እንደተቀየረ ተጠቁሟል፡፡

ይህ አስገራሚ አፓርታማ 206 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን 39 ወለሎች አሉት፡፡ አፓርታማው የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ሱቆች ፤ሱፐር ማርኬቶች፤ የመዋቢያ ሳሎኖች እና ካፌዎች ያሉት ሲሆን የመዋኛ ስፍራዎችም ተካተውበታል፡፡ ብቻ ምን አለፋዎት በአፓርታማው የፈለጉትን ቁሳቁስም ሆነ አገልግሎት ያገኛሉ፡፡ እናም ሆነ ነገር ፍለጋ ወደ ሌላ ቦታ የሚያስኬድዎት ምንም ጉዳይ የለም ማለት ነው ፡፡ ተአምረኛዋ ቻይና ነገ ደግሞ ምን ታሳየን ይሆን?መረጃው ኦዲቲ ሴንትራል ነው ፡፡

See also  ኢማኑዌል ማክሮን - "ተዉ! እኔ አሁን የፓርቲ ዕጩ አይደለሁም …"

Leave a Reply