የኪሎገር የሳይበር ጥቃት ምንድነው ? እንዴትስ ይፈጸማል?

ኪሎገር (Keylogger) የሳይበር ጥቃት ኮምፒውተራችን ላይ ያሉትን የጽሁፍ መተየቢያ ቁልፎች በመጫን ወደ ኮምፒውተራችን የምናስገባውን መረጃ እየመዘገበ ለጥቃት ፈጻሚው አካል የሚያቀብል አጥፊ ሶፍትዌር ወይም ሀርድዌር ነው፡፡

የኪሎገር ሀርድዌር በኮምፒውተራችን ላይ ከእኛ እውቅና ውጪ የሚጣበቅ/የሚሰካ ሆኖ በሆሄያት ቁልፎች አማካኝነት ወደ ኮምፒውተራችን የምናስገባውን እያንዳንዱን ቃል/መረጃ በመመዝገብ ለጥቃት ፈጻሚዎቹ የሚያቀብል ሲሆን፤ የኪሎገር ሶፍትዌር ደግሞ ኮምፒውተራችን ላይ ሳናውቀው ተጭኖ ተመሳሳይ ተግባር የሚፈጽም አጥፊ ሶፍትዌር ነው፡፡

የኪሎገር ጥቃትን አደገኛ ከሚያደርጉት ጉዳዮች መካከል ጥቂቶቹ ፦

ኮምፒውተራችን ላይ የምንጽፋቸውን መረጃዎች በሙሉ ለማንፈልገው አካል ይደርሳሉ፤

• የማህበራዊ ሚዲያ እና የድረ-ገጽ አካውንቶቻችን፣ የባንክ መረጃዎቻችን ወ.ዘ.ተ የይለፍ ቃሎቻችንን ሁሉ ስለሚመዘግብ እና ስለሚያስተላልፍ የግል መረጃዎቻች ለአደጋ ተጋላጭ ይሆናሉ ፤

ለዚህ ጥቃት የሚያጋልጡን ሁኔታዎች ምንድናቸው?

• በአካባቢያችን ያሉ ሰዎችን ማመን እና የይለፍ ቃሎቻችንን ማሳየት / ኮምፒውተሮቻችንን/ ስልኮቻችንን ክፍት መተው ወይም ለሰዎች አሳልፎ መስጠት፤

• የዘመነ ፋየርዎል አለመጫን፤

• የተበከለ ፋይል/ መተግበሪያ ከኢንትረኔት ማውረድ፤

በኪሎገር እንደተጠቃን እንዴት ማወቅ እንችላለን?

• የኮምፒውተራችን መዘግየት ወይም እየሠራን መቆም፤

• ጽሁፍ ስንተይብ ፈጣን ምላሽ አለመስጠት፤

• የኢንተርኔት ፍጥነት መዘግየት፤

• ታስክ ማኔጀር ገብተን ስንመለከት እኛ ከተገለገልንበት ውጪ የድረ-ገጽ ዓይነት ተመዝግቦ መታየት፤

ይህን ጥቃት እንዴት መከላከል እንችላለን ?

• የይለፍ ቃሎቻችንን፣ ኮምፒውተሮቻችንን፣ ስልኮቻችንን ወዘተ. ደህንነት መጠበቅ/ ለሌሎች አለማጋራት፤

• እርግጠኛ ያልሆንባቸውን ፋይሎች አለመክፈት እና ሀሰተኛ መተግበሪያዎችን አለመጫን፤

• ትክክለኛ አንቲ ቫይረስ በመጫን ማጽዳት / መከላከል፤

• ተቋማት ለሠራተኞቻቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት፤

• የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ በማውጣት ተግባራዊ በማድረግ፤

ወቅታዊና ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.insa.gov.et


See also  የ13 ዓመቱ ታዳጊ 66 ተማሪዎችን የያዘ አውቶብስ ሊገጥመው ከነበረ ከባድ አደጋ ታደገ

Leave a Reply