የለንደንን መጠነ-ሥፋት ከ2 እጥፍ በላይ የሚሆን የዓለማችን ትልቁ የበረዶ ግግር ተገምሶ እየሄደ ነው ተባለ፡፡ የበረዶ ግግሩ በፈረንጆቹ 1986 ላይ ከአንታርክቲክ ባሕር ዳርቻ ተቆርሶ በዌድል ባሕር አካባቢ የቆየ ሲሆን፥ ከመጠኑ ግዝፈት አንጻርም ‘የበረዶ ደሴት’ የሚል ስያሜን ይዞ በአካባቢው ከ30 አመታት በላይ ቆይታ አድርጓል። የበረዶ ግግሩ ‘የለንደን’ መጠነ ሥፋት ከሁለት እጥፍ በላይ እንደሚበልጥ ቢቢሲ አስነብቧል፡፡
ከ4 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር በላይ መጠን እና 400 ሜትር መጠነ ውፍረት ያለው የበረዶ ግግር አሁን ላይ በንፋስ እና በመሬት ውስጣዊ ግፊት ከነበረበት ስፍራ ለቆ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተመራማሪዎች እየገለጹ ነው። አሁን ላይ ግግሩ የአንታርክቲክ ባሕረ ገብ መሬትን ሰሜናዊ ጫፍ እያለፈ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ተመራማሪዎች “ኤ23 ኤ” በሚል ሥያሜ የሚያውቁትን የበረዶ ግግር እንቅስቃሴ በቅርበት እየተከታተሉት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ለበርካታ አመታት በባህር ላይ ሰፍር ዳርቻ የነበረው ግግር እንቅስቅሴ ስጋት እያጫረ መሆኑንም ዘገባው አመላክቷል።
ግግሩ አሁን ከያዘው የጉዞ አቅጣጫ አንጻር በደቡብ ጆርጂያ ዳርቻ ላይ ቢያርፍ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የዓሳ እና የባሕር ወፎች ዝርያዎች የመኖሪያ ምኅዳር እና ብዝኃ-ሕይወት ያቃውሳል የሚል ስጋት አሳድሯል፡፡
በሚፈጠረው አዲስ ያልተለመደ ምኅዳርም በብዝኃ ሕይወቱ ውስጥ አዲስ የሚፈለፈሉት የዓሳ እና ዐዕዋፍት ዝርያዎች አኗኗር ፣ አመጋገብ ፣ አስተዳደግ እና እንቅስቃሴ እንደሚቀየር ከወዲሁ መላ ምት አስቀምጠዋል።
ሌሎች አጥኚዎች ደግሞ እየተገፋ የሚመጣው የበረዶ ግግር ሥጋት ብቻ ሳይሆን ዕድልም ነው ይላሉ፡፡
በውስጡ የተለያዩ ማዕድናት የያዘ እንደመሆኑ የብዝኃ-ሕይወቱ የምግብ ሠንሠለት እንዲቀጥል አስተዋፅዖ አለውም ነው የሚሉት፡፡
ፋና
- ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?ያለፈውን ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ሥነ መንግሥት ታሪክ በጥሞና የተከታተለ ኢትዮጵያዊ የግዛት አንድነቷን እና የፖለቲካ ነጻነቷን በአንጻሩ ጠብቃ የኖረች ሀገር፤ ከአሁን በኋላ… Read more: ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?
- የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስአንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ የልብ በሽታና በደም ዝውውር ማነስ ምክንያት ለሚከሰት የአዕምሮ ሥራ መታወክ (ስትሮክ) የመጋለጥ… Read more: የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
- የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶችየስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ የህመም አይነት ነው። በዋናነት አራት የስኳር ህመም አይነቶች አሉ፤ እነርሱም… Read more: የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
- ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮ ጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል። ትዳርንም ሊያፈርስ ይችላል። “ስለ ባለቤቴ… Read more: ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New Development Bank. In a media briefing regarding… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership