ሁለት የተለያየ ማለያ ለብሰው በጠርብ ዱላ፣ ድንጋይና ባገኙት ቁሳቁስ ሲደባደቡ የሚያሳየው ምስል ” በስደት ምድር በዚህ ደረጃ ቡድን ለይቶ መደባደብን ምን አመጣው” የሚል አስተያየት እየተሰነዘረበት ነው። የኤርትራ ተወላጆች በዚህ ዓመት በጀርምን፣ ስዊዲን፣ ኖርዌይና ካናዳ በተመሳሳይ ጎራ ለይተው ተፈናክተዋል። ንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል። ፖሊስ ጎድተዋል። እስራኤል አሁን የታየው ግን በይዘቱ ሰፊና ከባድ የሚባል ነው። ለዚህም ይመስላል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ “የኢኮኖሚ ስደተኞች” ሲሉ የጠሯቸውን ሁሉ ማባረር የሚያስችል ህግ እንዲዘጋጅ ያዘዙት።
- በቴል አቪቭ ከተማ በተከሰተው ግጭት የተሳተፉ ኤርትራውያኑ ሥደተኞች በአስቸኳይ እስራዔልን ለቀው እንዲወጡ እንደሚፈልጉ የእስራዔል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ገልጸዋል፡፡
- ኔታንያሁ ጉዳዩን አስመልክተው በሠጡት አስተያየት በጥገኝነት እስራዔል የሚገኙ አፍሪካውያን ሥደተኞች በሙሉ በአስቸኳይ ሀገሪቷን ለቀው እንዲወጡም እንዲታሰብበት ማሳሰባቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
- ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት ይኅን ያሉት ÷ በትናንትናው ዕለት የኤርትራ ተቀናቃኞች ከእስራዔል ፖሊስ ጋር ደም አፋሳሽ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
- በደቡብ ቴል አቪቭ በተቀሰቀሰው ግጭት ከደርዘን በላይ ሰዎች መቁሰላቸው በዘገባው ተመላክቷል፡፡ በእስራዔል የሚገኙት የኤርትራ ሥደተኞች በቀሰቀሱት ግጭት የግንባታ እንጨቶችን፣ የብረት ቁርጥራጮችን እና ድንጋዮችን ተጠቅመዋል ተብሏል፡፡
- የሱቅ መስኮቶችን እና የፖሊስ መኪናዎችን መሰባበራቸውም ነው ተነገረው፡፡
- የእስራዔል ፖሊሶች የተለያየ ዓይነት አድማ በታኝ ጭስ እና አስደንጋጭ የእጅ ቦምቦችን በመጠቀም ሁኔታውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል መሞከራቸው ተገልጿል፡፡
ሰላሳ የሚልቁ የፖሊስ አባላትን፣ መቶ አስራ አራት የሚጠጉ ተደባዳቢዎች በተለያዩ ደረጃዎች ጉዳት ደርሶባቸው የሕክምና ድጋፍ እንደተሰጣቸው የአገሪቱ የጤና ተቋም አስታውቋል። ከተጠቀሱት መካከል ስምንት ተጎድተዋል። አስራ ሶስት የሚሆኑት ደግሞ ቀላል በማይባል ደረጃ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው።
ቅዳሜ ነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓ.ም በቴል አቪቭ የኤርትራ የባሕል ፌስቲቫል ዝግጅትን ሲካሄድ የመንግስት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ከባድ ሁከት ፈጥረው በሰውና በንብረት ላይ ያደረሱት ጉዳት እንዳበሳቻቸው ያስታወቁት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አፍሪካውያን ስደተኞች በሙሉ በአስቸኳይ ከእስራኤል ለማባረር እቅድ እንዲወጣ አዘዋል። ሁከቱና ድብድቡ በዱላና በድንጋይ የታገዘ፣ ለማመን የሚከብድ እንደሆነ የተቀረጸው ፊልም ያስረዳል።
ቤኒያሚን ኔታኒያሁ “ትናንት በቴል አልቪቭ ሁከት ውስጥ ተሳታፊ የነበሩ ኤርትራውያን በአስቸኳይ ከአገር እንዲባረሩ እፈልጋለሁ” ብለዋል። አክለውም በአገሪቱ ያሉ አፍሪካውያን ስደተኞችን በሙሉ ከአገር ለማባረር ዕቅድ እንዲወጣ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ያስታወቀው አሶሲዬትድ ፕሬስ ነው።
በትላንትናው ዕለት በቴል አቪቭ ጎዳናዎች ላይ በኤርትራዊያን ስደተኞች መካከል የተፈጠረውን አስከፊ ግጭት ከዚህ በፊት ከተለመደው የተካረር እንደነበር በማህበራዊ ሚዲያዎች አስተያየት ተሰጥቶበታል።
የፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን አስተዳደርን በሚቃወሙና በሚደግፉ ኤርትራዊያን መካከል የተነሳው ግጭት ለአፍሪካዊያን ስደተኞችም መዘዝ ይዞ እንደመጣ ነው የተጠቆመው። ኔትናሁ አፍሪካዊያን ስደተኞችም የሚባረሩበት ሁኔታ እንዲመቻች ነው መመሪያ የሰጡት። በእስራኤል 25 ሺህ የሚልቁ አፍሪካዊያን ስደተኞች አሉ። አብዛኞቹ የኢኮኖሚ ስደተኞች እንደሆኑም የአገሪቱ መገናኛዎች አመልክተዋል።
የፖለቲካ ስደተኛ የሆኑና ወደ አገራቸው ቢመለሱ ችግር የሚገጥማቸውን መመለስ እንደማይቻሎ በዓለም ዓቀፍ የስደተኞች ድንጋጌ የሰፈረ በመሆኑ ከወዲሁ ” የኢኮኖሚ ስደተኞች” የሚል ጉዳይ እየተነሳ ነው።
በእስራኤል ኤርትራ ኤምባሲ ፊት ለፊት በዱላና ድንጋይ ሲከሳከሱ የታዩት የኤርትራ ተወላጆች በድጋፍና በተቃውሞ መጣላታቸው ከሚሰማው በቀር ዝርዝር ምክንያታቸው ተብራርቶ አልተገለጸም። ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ የሄደው ግጭት ግን አገር ውስጥ ያለው ብሶትና አፈና ነጸብራቅ እንደሆነ በርካቶች ይገልሳሉ።
ኤርትራዊያ እናቶች፣ አባቶች፣ በጥቅሉ እድሚያቸው የገፋ ሳይቀር በአውሮፓ፣ አማኤሪካ፣ ካናዳና አውስትራልያ በስደት እንደሚኖሩ ይታወቃል። በቅርቡ የኢትዮ ኤርትራ ድንበር በተከፈተ ጊዜ በሶስት ወር ብቻ ስምንት መቶ ሺህ የሚሆኑ የኤርትራ ተወላጆች መንደራቸውን ለቀው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የስደተኞች ጉዳይ የሚመለከተው ተቋም ከአዲስ አበባ መጠቆሙ አይዘነጋም።
የእስራኤል ፖሊሶች ድብድቡን ለማስቆም የፕላስቲክ ጥይቶችን ተጠቅመዋል። በፖሊሶቹ ላይ ድንጋይ ተወርውሮ ጉዳት ደርሷል። አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ፖሊስ እሳት መርጨቱን የአመልክቷል። አክሎም ሃያ ሰባት ፖሊሶች ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚመልከታቸውን ጠቅሶ ገልጿል።
ድብድቡን በቅርብ የተከታተሉ ቢጎዱም ህክምና ሳያገኙ ሸሽተው ወደ ቤታቸው የገቡ እንዳሉ አምልክተዋል። ራሳቸውን በህጻናት መጫወቻ የደበቁ እንደነበሩም አጃንዝ ፍራንስ ፕሬስ አመልክቷል።
በእስራኤል ሃያ ሺህ ኤርትራዊያን ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚገኙ ሲሆን አብዛኞቹም በህገወጥ መንገድ በግብጽ ድንበር አቋርጠው የገቡ መሆናቸውን የተለያዩ መረጃዎችን የሚጠቅሱ ሪፖርቶች ይገልጻሉ።