ትናንት ከሀገር ፍቅር እና ደመ ሞቃትነት የተነሳ አንድ ትውልድ በሚባል መልኩ ዋጋ ከፍሏል። ከዚያ መማር የዚህ ትውልድ የቤት ሥራ ነው፡፡ ሀገርን መጠበቅ፣ ሥልጣኔን ማስቀጠል እና ውስብስብ የኾነውን ዓለም ተረድተው መውጫ ብልሃት የሚያመነጩ ልጆችን ኢትዮጵያ ትፈልጋለች ። እኛ ከእኛ የተሻለ ትውልድ መፍጠር ካልቻልን ሀገር እየገደልን ነው” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ጳግሜን 5 የትውልድ ቀን ” ኢትዮጵያ የትውልዶች ድምር” በሚል መሪ ሃሳብ በፌዴራል ደረጃ እየተከበረ ነው፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ፍትሕ ሚኒስቴር በጋራ ባዘጋጁት የትውልድ ቀን በዓል ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴን ጨምሮ አርበኞች፣ አረጋዊያን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ለበዓሉ ታዳሚዎች መልእክት ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአሁኑ ትውልድ ካለፈው የሚማር እና ለሚመጣው የሚያስተምር መደላድል ነው ብለዋል፡፡ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ ቆመን ያለፈውን እና የሚመጣውን ስናስብ ለነገ ተስፋ የምናይበት ነው ብለዋል፡፡
ሽግግሩ የአንድ ዓመት ብቻ ሳይኾን በርካታ ዘመናትን አስታውሰን፤ እልፍ ዘመናትን የምንቀበልበት ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ የእርሳቸው ትውልድ በርካታ ጥሩ ነገሮች እንዳሉት አንስተው አሁናዊው ትውልድ ሊማርበት የሚገባ በርካታ ጉድለቶች ነበሩበት ብለዋል፡፡ ሀገር ወዳድነት፣ ማንበብ፣ ማሰብና ማንሰላሰል እንዲሁም ምክንያታዊነት የዚያ ዘመን በጎ ጎኖች ነበሩ ብለዋል፡፡
“የእኛ ትውልድ የትግሉ ማዕከል ሀገሩ ነበረች” ያሉት የትምህርት ሚኒስትሩ ነገር ግን ዓለምን የምንመለከትበት መነጽር ጠባብ በመኾኑ በርካታ ዋጋ ከፍለናል ብለዋል፡፡ አንድ ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም እንደ መታገያ መስመር መውሰድ እና እርሱን ብቻ መፍትሔ አድርጎ መመልከት ድክመት ነበር፤ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ አለማስገባትም ዋጋ አስከፍሏል ብለዋል፡፡
ትናንት ከሀገር ፍቅር እና ደመ ሞቃትነት የተነሳ አንድ ትውልድ በሚባል መልኩ ዋጋ ከፍሏል ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከዚያ መማር የዚህ ትውልድ የቤት ሥራ ነው ብለዋል፡፡ ሀገርን መጠበቅ፣ ሥልጣኔን ማስቀጠል እና ውስብስብ የኾነውን ዓለም ተረድተው መውጫ ብልሃት የሚያመነጩ ልጆችን ኢትዮጵያ ትፈልጋለች ነው ያሉት፡፡
ሚኒስትሩ በንግግራቸው ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ትውልዱ የተወዛገበ የሞራል መሰረት ላይ መቆሙን ጠቁመው፤ “እኛ ከእኛ የተሻለ ትውልድ መፍጠር ካልቻልን ሀገር እየገደልን ነው” ብለዋል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ እየፈጸማቸው ያሉ የሥርዓተ-ትምህርት ማሻሻያ እና የትምህርት ፍኖተ ካርታ ትግበራ ዓላማው ተማሪዎችን መጣል ሳይኾን ራሱን ችሎ የሚቆም ትውልድ ማፍራት እንደኾነ አንስተዋል፡፡
በጎ፣ ግብረ-ገብ፣ አንሰላሳይ፣ አሳቢ፣ ምክንያታዊ እና ትጉህ ተማሪ ለማፍራት ኢትዮጵያዊያን በጋራ እንዲቆሙም ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው አሚኮ
- ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?ያለፈውን ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ሥነ መንግሥት ታሪክ በጥሞና የተከታተለ ኢትዮጵያዊ የግዛት አንድነቷን እና የፖለቲካ ነጻነቷን በአንጻሩ ጠብቃ የኖረች ሀገር፤ ከአሁን በኋላ በዜጎቿ ፈቃድ ላይ… Read more: ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?
- የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስአንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ የልብ በሽታና በደም ዝውውር ማነስ ምክንያት ለሚከሰት የአዕምሮ ሥራ መታወክ (ስትሮክ) የመጋለጥ ዕድሉ እጅግ በጣም… Read more: የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
- የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶችየስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ የህመም አይነት ነው። በዋናነት አራት የስኳር ህመም አይነቶች አሉ፤ እነርሱም አይነት አንድ፣ አይነት… Read more: የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
- ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮ ጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል። ትዳርንም ሊያፈርስ ይችላል። “ስለ ባለቤቴ ማንኮራፋት ቀላል አድርጌ… Read more: ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New Development Bank. In a media briefing regarding the country’s diplomatic… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership