አስራ አንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጣምረውበታል የሚባለው ህዝብረት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ባደረጉት ውይይት ያልተገኘው የሽግግር መንግስትን ጨምሮ ተመሳሳይ አሳሳቢ ጉዳዮች በውይይቱ ስለማይነሱ መሆኑንን አመለከተ።
የረዥም ጊዜ የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ በጥምረቱ ስም ለቢቢሲ እንዳሉት ከሆነ ውይይቱ ዋጋ ቢስ ነው። በኦርሚያ ክልል ሁሉም ዞኖች በሚባል ደረጃ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይና ፓርቲያቸው ሰፊ ቁጥር ያለው ህዝብ ወጥቶ ድጋፉን በአደባባይ በገለጸበት ቅጽበት ለቢቢሲ ቃላቸውን የሰጡት መረራ በኦሮሚያ ስለታየው የህዝብ ድጋፍ ያሉት ነገር የለም።
ሰኞ መጋቢት 23/2016 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር የተቃዋሚዎቹ ጥምረት አለመሰብሰቡ ” ዋጋ ይስከፍላችኋል” ተብሎ ተጠይቆ ነበር። መረራ ሲመልሱ ” ብዝይ ዋጋ ከፍለናል” ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ በርካታ እስረኞች ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ነጻ መሆናቸውና የሚታወስ ነው።
“መንግሥት አሳሳቢ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መነጋገር ስለማይፈልግ” በውይይቱ ለመሳትፈ አለመፈለጋቸውን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቢቢሲ መንግስት በአደባባይ የሰላም ንግግር እንደሚፈልግ ጠቅሶ ለዕመነት አባቶች፣ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በይፋ ማስታወቁን ቢቢሲ ለመራራ አላስታወሳቸውም።
በአገሪቱ መገዳደል እንዲያበቃ ንግግር መደረግ እንዳለበት መረራ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ በኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባርና በመንግስት በኩል ሲደረግ የነበረውን ውይይት መረራም ሆነ ፓርቲያቸው በይፋ ሲያበረታታ አልታየም።
ለፓርቲው ቅርበት ያላቸውና ስማቸውን እንዳይተቀስ የጠየቁ እንዳሉት ከሆነ ድርድሩ ወደ ሰላማዊ መግባባት ሲቃረብ “የሽግግር መንግስት” የሚል ጥያቄ እንዲነሳ ካደረጉትና ግፊት ከፈተሩት መካከል የኦፌኮ አመራሮችም ይገኙበታል። በሚፈለገው መተንና ደረጃ የንጹሃንን መፈናቀልና ግድያ የማይቃወመው ኦፌኮ፣ ” መገዳደል እንዲያበቃ ውይይት መደረግ አለበት፣ ከዚያ ያለውፈው ሁሉ ረብ የለሽ ነው” የሚል አቋም እንዳለው ሲያራስታውቅ ቢቢሲ ” እስኪ ደም መፍሰስና መፈናቀል እንዲቆም ምን ሰራችሁ” በሚል ጥያቄ አላቀረበም።
ጥሪውን አክብረው የሄዱ እንዳሉት ጥያቄ በተመሳሳይ ብተነስቶ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “ውይይት ለማድረግና ለመደራደር ዝግጁ ነን” የሚል ምላሽ መስጠታቸውን ምስክርነት ሰጥተዋል።
አገሪቱ ወደ ዲሞክራሲ የምታደርገው ሽግግር መክሸፉን በመጥቀስ፤ ይህንን የአገሪቱ የዲሞክራሲ የመቀልበስ ሂደት ላይም ገዢው ፓርቲ መወያየት እንደማይፈልግ ያስታወቁት መረራ በግልጽ የሽግግር መንግስት ጠይቀዋል። በታንዛንያው ድርድር እንደሆነው ሁሉ በተመሳሳይ የሽግግር መንግስት የጠየቁት መረራ፣ ሽግግሩ እንዴትና በምን ሁኔታ አሁን ያለውን ቀውስ ሊያስወግድ እንደሚችል አላብራሩም።
የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የኦጋዴን የነጻነት ግንባር፣ ህብር ኢትዮጵያ፣ አረና ትግራይ ፓርቲ፣ የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የአፋር ሕዝቦች ፓርቲን የተካተተቱበት ነው።