“ጥቃት ደረሰባት የተባለችው ሉሲ በኢትዮጵያ በህጋዊ ጋዜጠኛነት እትታወቅም”

በኢትዮጵያ የሎሳንጀለስ ታይምስ፣ አልጀዚራና የኖርዌይ ሚዲያ ወኪል ሆና እነደምትሰራ ገልጾ የድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት Reporters Without Borders (RSF) የተሟገተላት ሉሲ ካሳ በኢትዮጵያ ህጉ በሚያዘው መሰረት ተመዝግባ የምትሰራና የምትታወቅ ጋዜጠኛ አይደለችም ተባለ። ስሟ ሉሲ በርሄ ካሳ ቢሆንም ተቋሙ የጠራት ሉሲ ካሳ ብሎ ሲሆን ከመንግስት ወገንም በተመሳሳይ ነው ስሟ የተጠቀሰው።

የውጭ ሚዲያዎች ወኪል በመሆን ትሰራ ነበር የተባለችው ሉሲ ካሳ በሕጋዊነት ተመዝግባ እንደማትንቀሳቀስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ያስታውቀው የድንበር የለሽ ጋዜጠኖች ቡድን ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ነው። ቡድኑ ህጋዊ እውቅና የለትም የተባለችውን ፍሪላንስ ጋዜጠኛ ባልታወቀ ግለሰብ ጥቃት ደረሰባት ብሎ ነበር። ቡድኑ እጅግ ማዘኑንን ገልጾ የተፈጸመውን ድርጊት አውግዞ ላሰራጨው ዜና “ሉሲ ካሳ በኢትዮጵያ የውጭ ሚዲያዎችን በህጋዊነት የሚወክል ፍቃድ እንደሌላት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንን አስታውቋል” ሲል ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ያመለከተው።

Reporters Without Borders (RSF) is shocked to learn that armed intruders physically attacked and threatened an Ethiopian freelance journalist in her Addis Ababa home with the clear aim intimidating her in connection with her reportingሙሉውን ሪፖርት እዚህ ላይ ያንብቡ

የድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድን ሉሲ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ብቻ ሳይሆን ቤቷ የሲቪል ልብስ በለበሱ ሰዎች በሃይል መበርበሩን፣ ኮምፒወተሯ ላይ ያሉ መረጃዎሽ መታየታሸውን በተለያዩ ጊዜያት ለውጭ ስማቸው ለተጠቀሱት ሚዲያዎች ሃሰት እንደምትዘግብና ጁንታውን የትግራይ ሃይል እንደምትደግፍ እየተገለጸ ማስፈራራት እንደተፈጸመባት አትቷል።

መረጃ ማጣሪያው ግን በዋናናት የተነሳው የአግሪቱን የስራ ህግ በማጣቀስ ነው። በአገሪቱ ሕገ መንግስት የትኛውም ግለሰብ በደህንነትና ነጻነት የመንቀሳቀስ መብቱ የተጠበቀ መሆኑንም አስታሶ፣ድንበር የለሽ የጋዜጠኞ ቡድን Reporters Without Borders (RSF) ፍሪ ላንስ ጋዜጠኛ ሉሲ ካሳ በዘገባ ወቅት ከምትዘግበው ሁነት ጋር በተያያዘ ጥቃት ደርሶባታል በሚል እንዲሁም በኢትዮጵያ የሎሳንጀለስ ታይምስ፣ አልጀዚራና የኖርዌይ ሚዲያ ወኪል ናት ብሎ መረጃ ማውጣቱን ያጣጥላል።

See also  37 ሺ በሚሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራ ተደረገ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ የውጭ ሚዲያን በመወከል መንቀሳቀስ የሚፈልጉ ጋዜጠኞች በብሮድ ካስት ባለስልጣን በመመዝገብ፣ ህጋዊ መሆንና የሚዲያ ይለፍ መታወቂያ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቋል። ይሁን እንጂ ሉሲ ካሳ በብሮድ ካስት ባለስልጣን ህጋዊ ምዝገባ አድርገው ከሚንቀሳቀሱ የውጭ ሚዲያ ወኪሎች መካከል አይደለችም። በህጋዊነት ተመዝግባ የምትታወቅ ጋዜጠኛ አለመሆኗን ጠቅሶ ሪፖርቱ የሳተ መሆኑንን ያከለው የአስቸኳይ አዋጅ ማጣሪያ የማስተካከያ መግለጫ ልጅቷ ላይ ተፈጸመ ስለተባለው ወንጀል ያለው ነገር የለም።

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ሉሲ ካሳ አል ጀዚራን ጨምሮ ሌሎች የውጭ ሚዲያዎች በወኪልነት ትሰራ ነበር ብሎ ያወጣው መረጃም የተሳሳተ መሆኑንና ቡድኑ መረጃ ከማሰራጨቱ በፊት የመረጃውን እውነተኝነት ግራና ቀኝ አጣርቶ ማውጣት ይገባው እንደነበረም አስታውቋል።

በአገሪቱ ሕገ መንግስት ማንም ሰው በነጻነት ደኅንነቱ ተጠብቆ መንቀሳቀስ እንደሚችል መደንገጉን ገልጾ፤ ቡድኑ በተሳሰተ ሁኔታ ያሰራጨውን መረጃ በአስቸኳይ እንዲያርም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያው ሊያርም እንደሚገባው አሳስቧል።

photo Reporters with out boarder

    Leave a Reply