የመረጃና ደህንነት አገለግሎት አርማ ያለባቸው የዋሌት ምርቶች ለማጭበረበሪያነት እየዋሉ ነው፤ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አርማ የታተመባቸውን የኪስ ቦርሳዎች በማዘጋጀትና መታወቂያ በማስመሰል ለሕገወጥ ተግባራት ጥቅም ላይ ለማዋል ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዛሬ ለኢፕድ በላከው መረጃ እንዳመለከተው የተቋሙ አርማ የታተመባቸውን የኪስ ቦርሳዎች ወይም ዋሌቶችን በማዘጋጀትና መታወቂያ በማስመሰል ለሕገወጥ ተግባራት ጥቅም ላይ ለማዋል ሙከራ ሲያደረጉ የነበሩ ተጠርጣሪ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ገልጾ ኅብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ዋሌቶችን መታወቂያ አስመስለው በማዘጋ ለማሰራጨት ሙከራ ሲያደርጉ እንደነበርና ካዘጋጇቸው

እነዚህ ግለሰቦች የተቋሙ አርማ የታተመባቸውን የኪስ ቦርሳዎች እንደመታወቂያ በማሳየት በሕገወጥ ተግባር መሰማራታቸውንና በተቋሙ ስም ያለአግባብ አገልግሎት ለማግኘት ሙከራ እያደረጉ መሆኑ እንደተደረሰበት አስታውቋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መረጃ እንዳመለከተው የተቋሙ አርማ የታተመበትን የኪስ ቦርሳ ወይም ዋሌት ይዞ መገኘት ብሎም ሕገ-ወጥ ለሆነ ተግባር ማዋል ሕጋዊ ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡

በመሆኑም ይህ የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ አርማ የታተመበት የኪስ ቦርሳ በእጁ የገባ ግለሰብ በአካባቢው ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ እንዲያስረክብ ወይም በስልክ ቁጥሮች 0115543681 እና 0115543804 በመወደል እንዲያሳውቅ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

ይህን ተላልፎ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል።

See also  የቻይና አፍሪካ ትብብር በእኩልነትና የጋራ ተጠቃሚነት መርህ

Leave a Reply