ከህወሓትና ከኦነግ ሸኔ አመራሮች ተልዕኮ ተቀብለው ሰርተዋል የተባሉ ተጠርጣሪ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ሆነ

በጋምቤላ ክልል በእርሻ ስራ ላይ የተሰማሩት ባለሃብት አቶ አለም ደስታ ሃየሎም ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ በሙሉ ውድቅ ሆነ። የክስ መቃወሚያቸውን ውድቅ ያደረገው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምደብ 2ኛ የጸረ ሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። አቶ አዲስ አለም የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችን ጎብኝተው ጦርነት ላይ ስላሉ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግለት ከዾር ደብረጽዮን መክረዋል

ተከሳሹ አቶ አለም ደስታ ዐቃቤ ህግ በመሰረተባቸው ህገ መንግስቱና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለማፍረስ ሙከራ ወንጀል ክስ ላይ፤ ከጥር 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የኦሮሚያ ክልል እንዳይረጋጋ እና ክልሉ የጦርነት ማዕከል እንዲሆን እንዲሁም የፌደራል መንግስት እንዲፈርስና የመንግስት ስልጣንን ከህገ መንግስት ስርዓት ውጪ በሆነ መንገድ ለመያዝ በማሰብ ሲሰሩ እንደነበር በክሱ ተመላክቶ ነበር።

ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ደግሞ ከኦነግ ሸኔ ተወካይ ጋር ተገናኝተው በምዕራብ ወለጋ እና ኢሉባቡር ዞኖች በህወኃት ቡድን ስለሚደረገው የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለመነጋገር ከአምባሳደር አዲስ አለም ባሌማ ጋር በሚሰሩበት መንገድ ትራንስፖርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት አምስተኛ ወለል ላይ በሚገኘው ቢሮ መግባታቸውን ዐቃቤ ህግ በክሱ መጥቀሱ ይታወቃል።

በተጨማሪም ተከሳሹ በምዕራብ ወለጋ የሚገኘውን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችን ጎብኝተው ወደ  ጋምቤላ ተመልሰው መሄዳቸው እና ታጣቂዎቹ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ጦርነት ላይ ስለመሆናቸው አስቸኳይ ድጋፍ ለኦነግ ሸኔ እንዲደረግ ከዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል  ጋር መነጋገራቸውን ጠቅሶ ነበር።

ተከሳሹ ዐቃቤ ህግ ያቀረበው ክስ ተገቢነት የለውም በማለት መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን፥ ፍርድቤቱ መቃወሚያቸውን ውድቅ አድርጎታል።በዛሬው ችሎት ዐቃቤ ህግ ከክሱ ጋር የምስክር ማስረጃ አያይዞ እንዲያቀርብ ለዛሬ የታዘዘ ቢሆንም ማስረጃው ተያይዞ ባለመቅረቡ በቀጣይ ቀጠሮ ማስረጃውን አይይዞ እንዲያቀርብ እና ብይን ለመስጠት ፍርድቤቱ ለሚያዚያ 4 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በሌላ በኩል በከፍተኛ ፍርድ ቤት ከግዢ መመሪያ ውጪ የእርሻ ትራክተሮችን በተጋነነ ዋጋ  ግዢ በመፈጸም ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል የተከሰሱት፤ የቀድሞው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ ስምንት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር እንዲያሰሙ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ተከሳሾቹ ላይ ዐቃቤ ህግ በ2004 ዓ.ም ከ1 ሺህ 120 በላይ በተከናወነ የእርሻ መሳሪያ ትራክተሮች ግዢ  የእርሻ ትራከተሮቹ ያለ ጥቅም በመቆየታቸው እና የነዳጅ ማጠራሚያ ታንከራቸው የፈነዳ በመሆኑ በመንግስት ላይ ከ119 ሚሊየን 856 ሺህ ብር በላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቅሶ መከሰሳቸው ያታወሳል።

ይህን ክስ ተከትሎ ዐቃቤ ህግ የሰነድና የሰው ምስክር አሰምቶ ያጠናቀቀ ሲሆን የተከሳሾቹን መከላከያ ምስክር ለመስማት ከነገ በስቲያ ለመጋቢት 29 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

እነ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ከመርከብ እና ከሆቴል ግዢ ጋር ተያይዞ ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበር ይታወሳል።

በታሪክ አዱኛ FBC


 • አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ የምታስወጣ ከሆነ 200 ሺ የሚጠጉ ሴቶች ከሥራ ውጪ ይሆናሉ
  አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ የምታስወጣ ከሆነ በፋብሪካዎች ተቀጥረው የሚሠሩ 200 ሺ የሚጠጉ ወጣት ሴቶችና እናቶችን ከሥራ ውጪ ይሆናሉ ሲሉ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ገለጹ፡፡ የምጣኔ ሀብቱ ባለሙያ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአሁኑ ጊዜ አሜሪካ ለአፍሪካ አገራት ከሰጠችው ከቀረጥ ነፃ ንግድ ማበረታቻ ዕድል (አጎዋ) ተጠቅመው በአሜሪካ ገበያ ምርታቸውን በሚያቀርቡ ፋብሪካዎችContinue Reading
 • አሜሪካ በትህነግ ላይ ቃታ ሳበች፤ የዜጎች ርብርብ ውጤት አስገኘ
  የጦርነቱ መነሻ ምክንያት የሰሜን ዕዝ ላይ ትህነግ በፈጸመ ጥቃት ሳቢያ መሆኑ ትህነግ ከኦነግ ሸኔ ጋር የፈጠረርውን ጥምረት የለቅድመ ሁኔታ እንዲያፈርስ ህጻናትን ለውትድርና መጠቀምን እንዲያቆም በወረራ ከያዛቸው የአማራ አካባቢዎች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ለቆ እንዲወጣ በ H.Res.445 አዋጅ በአሜሪካ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ጉዳይ ውሳኔ አሳልፏል። የውሳኔው መግለጫContinue Reading
 • ኦፌኮ ብሔራዊ ውይይቱ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪና ሸኔ እንዲካተቱበት ጠየቀ
  የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ በቅርቡ ይካሄዳል የተባለው የብሄራዊ ውይይት የታጠቁ ሃይሎች ሙሉ በሙሉ እንዲካተቱበት ሲል ጠየቀ። ወንጀል የሰሩና በከፍተኛ ደረጃ የመከላከያ ሰራዊትን ያሳረዱ፣ ሰላማዊ ዜጎች እንዲፈናቅሉና በጅምላ እንዲጨፈጨፉ፣ መጤ ተብለው እንዲሰደዱ አድርገዋል፣ አዘዋል፣ አመራር ሰጥተዋል በሚል ህግ ይጠይቃቸዋል የተባሉትን አስመልክቶ መግለጫው ስምና ድርጅት ጠቅሶ አልጠየቀም። ሙሉ መግለጫውን ያንብቡ የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲContinue Reading
 • የትግራይ ነጻ አውጪ ኩታበር ገባሁ አለ፤ መንግስት ሙትና ቁስለኛ ሆኖ መበተኑና የተቀረውም እየታደነ መሆኑን ገለጸ
  ፎቶ የትግራይ ሃይሎች በወረሯቸው አካባቢዎች የደረሰ ዕህል በደቦ ሲያጭዱ የሚያሳይ፣ ምንጭ የደሴ ወጣቶች መቀለ የሚገኘው የጀርመን ድምጽ ዘጋቢ ትህነግ በሰጠው መግለጫ ኩታበርን መቆጣጠሩን እንደዘገበለት በመጥቀስ በፌስ ቡክ ገጹ አስፍሯል። የጀርመን ድምጽ የኢትዮጵያን መንግስት ዘገባ ለምን እንዳካተተ አላስታወቀም። ይሁን እንጂ መንግስት ማምሻውን ባሰራጨው መግለጫ በወሎ ግንባር በወረባቦ፣ በተሁለደሬ፣ ኩታበርና ደላንታ በወሰዱትContinue Reading

Leave a Reply