ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስራቸውን እየሰሩ ነው “ተላላኪዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል” ከምርጫ በሁዋላ ብልጽግና ሰባ ከመቶ ይጸዳል

የኢትዮ 12 ተባባሪ ከአዲስ አበባ ያነጋገራቸውን ከፍተኛ ባለስልጣን ጠቅሶ እንዳስታወቀው ምርጫው ሲጠናቀቅ ብልጽግና ሰባ ከመቶ በላይ ውስጡን እንደሚያጠራና በርካታ ሹመት በሜሪት እንደሚሆን የሰሙ፣ በመጪው ምርጫ እንደማይሳካላቸው ያወቁ ሃይሎች ከተፈጠረው አሳዛኝ እልቂት ጀርባ እንዳሉበት ታውቋል።

የአማራ ክልል ከፍተኛ ሃላፊ በበኩላቸው በምርጫ ማሸነፍ የማይችሉ ክፍሎች አቋራጭ መንገድ ለመጠቀም ከቀውሱ ጀርባ ሆነው እንደሚሰሩ፣ ሃዘኑንም ለፖለቲካ ፍጆታ እያዋሉት መሆኑን ሕዝብ እየተረዳ በመሆኑ ምርጫው ያለጥርጥር እንደሚካሄድ አረጋግጠዋል። ለጊዜው ትኩረቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ማቋቋም፣ ቸግር ፈጣሪዎችን ማደን፣ ታጣቂዎችን መደምሰስና ተላላኪዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ እንደሚሆን አመልክተዋል። ይህም የሚደረገው በሰከነ መንገድ እንደሆነ ገልጸዋል።

የብልጽግና ከፍተኛ ሰው የሆኑት ለተባባሪያችን እንዳሉት ” ወይይቶች፣ ጠበቅ ያሉ ክርክሮችና፣ ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድ ስለመከተል ያለማቋረጥ ውይይት እየተድረገ ነው” ይሁን እንጂ በሚናፈሰው ወሬ ደረጃ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ህዝብና አገርን ሜዳ ላይ ጥለው ስራ ስለማቆም አልተናገሩም።

ከአገር ሽማግሌዎችም ሆነ ከአባገዳና አግባብ ይኖራቸዋል ከሚባሉ ወገኖች ጋር መነጋገር መወያየት አዲስ እንዳልሆነ ያመለከቱት ሃላፊ ” እንደ መንግስት ተቀጣሪ ፖለቲከኞች የፈጸሙት አስነዋሪ ተግባር አስከፍቶናል። አዝነናል። ነገር ግን ጠላት ባስቀመጠው ቦይ የመፍሰስ እቅድ ምልክት የለም። ማጥራት ግን ይካሄዳል” ሲሉ ተናግረዋል።


RELATED

የጠላት ሃይል አሰፍስፎ ክልሉን ለማተራመስ እየሰራ መሆኑን አውቆ የክልሉ ህዝብ ከመንግስት ጎን ሊሰለፍ ይገባል – አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

በሰሜን ሸዋና አካባቢው መሽጎ የሚገኘውን ኃይል ለመደምሰሰስ እየሰራ መሆኑን ክልሉ አስታወቀ በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋና አካባቢው ሰሞኑን ተከስቶ የነበረው የጸጥታ […]

እውነትን ዋጁ!ሰከን ብለን የጥፋት ኃይሎችን ብንመክት አይሻለንም?

(በንጉሴ መሸሻ (ዶ/ር)) መነጋገር/ክርክር በምክንያትና በእውነት ላይ ሲሆን ከህሊና ወቀሳ ያድነናል፤ እንደየአምልኮታችንም ደግሞ ፈጣሪ ደስ ይለዋል ብለን እናስባለን። ነገር ግን […]


” ሆን ተብሎ መረጃ መፍተር፣ ማሰረጨትን አሳስቶ ለፖለቲካ ፍጆታቸው ማዋል የተለመደ አሰራር ነው” ሲሉ ለሚታወቁ ሚዲያዎች በትንሽ ጫፍ ተንተርሰው ምኞታቸውን የሚያሰራጩ ወሬ አቀባዮች ስላሉ ማንኛውንም መረጃ ማጥራትና አረጋግጦ መዘገብ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጫናን መቋቋም የሚችሉ ዘመናዊ መሪ ናቸው” በማለት ስለ ወቅታዊ አቋማቸው የገለጹት ሃላፊ ” ከተፈጠረው አደጋ አንጻር የከረረ መመሪያ መስተጠታቸውን አውቃለሁ፤ ግን አገር በትኜ በቃኝ እላለሁ ሲሉ አልሰማሁም። እንደ ቅርብ የስራና የድርጅት ባልደረባ ቢሉ ቅድሚያ የመስማት እድል ይኖረኝ ነበር። ሃሳቡም ካላቸው ለካቢኔዎች እንጂ ለሽማግሌዎች ይህን የሚሉበት አግባብ አይታይም” ብለዋል። ይህ ማለት ግን በኦሮሚያ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች እንዳይከናወኑ ቅድመ ጥንቃቄ አልተደረገም ማለት ግን አይድለም ሲሉ አክለዋል።

ብልጽግና ካለፈው አካሄድና የተሸከመው በርካታ ጉድፋና ሸክም ያለበት ፓርቲ እንደሆነ የጠቆሙት ሃላፊ ” ስናንጠባጥብ ቆይተን እዚህ ደርሰማል። ከምርጫው በሁዋላ እንጸዳለን። ይህን ለማስተጓጎል ነው ሴራው” ብለዋል። አያይዘውም ” በምርጫ ደጋፊ አለን የሚሉ ድርጅቶች ደጋፊዎቻቸው ወደ ምርጫ ጣቢያ ሄደው እንዲመርጡ ከመቀሰቀስ ይልቅ ተመዝጋቢ የለም ብለው ሲያለቅሱ መስማት አሳዛኝ ነው። ከችግር ጀርባ የሚነሱት ጥያቄዎችም የሽንፈታቸው ፍርሃቻ የፈጠረው ህመም ነው” ሲሉ አብራርተዋል።

የአማራ ክልሉ ሃላፊ በስልክ እንዳሉት ” አብን በምርጫ እንዲገጥመን እንመኝ ነበር። ጎንደርና አብዝናውን ጎጃም እንደምናሸንፍ ጥርጥር የለውም” ካሉ በሁዋላ ” ምርጫው በሚገባው አግባብ እንደሚጠናቀቅ እርግጠኛ ነኝ” ሲሉ አስታውቀዋል።

ጥበብ፣ ማስተዋል፣ እንዲሁም ስሜትን የመግዛት ፖለቲካ መከተል ግድ መሆኑንን፣ አማራ ክልል ላይ የተደቀነውን ችግር በርጋታ መመርመር ለሚችል ከዚህ እሳቤ ውጭ ያሉ መንገዶች አዋጪ እንደማይሆን እንደሚረዳ፣ ከደረሰውና ሲደርስ ከነበረው ጥፋት እንጻር በሃዘኑ ምሬት ተገፋፍቶ በስሜት መጋል አገር ከሚመራ ድርጅት እንደማይጠበቅ አስታውቀዋል።

አብን በሰሜን ሸዋ የደረሰውን ውድመትና ግድያ ተከትሎ ሕዝብ ራሱን ለመከላከል የተፈጥሮ መብቱን እንዲጠቀም፣ ድርጅቱ ከፊት ሆኖ ይህንኑ እንደሚመራ፣ የአማራ ሕዝብ የሚራራለት መንግስት እንደሌለው ጠቅሶና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ” አሸባሪ የኦነግ መሪ ” ብሎ በመፈረጅ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። ይህንኑ ተከትሎ ” ጠቅላይ ሚኒሥትሩን በዚህ ደረጃ መስደብ አግባብ አይደለም። አሸባሪ ሃይሎች በሁለት ሳምንት እንዲደቁ አመራር የሰጡ መሪ በወራት ልዩነት አውርዶ መሳደብ ሚዛናዊነትን አያሳይም። ለጊዜው ከዚህ ውጭ የምለው የለም” ሲሉ የኦሮሚያ ብልጽግና አመራር ለኢትዮ 12 የአዲስ አበባ ተባባሪ አመልክተዋል። ስድቡ ግን እጅግ ቀላል የማይባል ቁጣ እንደፈጠረ መሸሸግ እንደማይቻል አመልክተዋል።

በሰሜን ሸዋ ክፉዎች ዘርን መሰረት አድርገው የፈጸሙትን ወንጀል ተከትሎ፣ ” ከትህነግ ጋር ግንባር ፈጥረን አብይን እንታገለዋለን” የሚል አስተያየት በመረጃ ቲቪ የአበበ በለው ፕሮግራም ላይ በላይቭ መተላለፉ ክፉ ስሜት ፈጥሯል። ምን አልባትም አድሮ መነጋገሪያ ሊሆን እንደሚችል እየተደመጠ ነው። ይህን የሰሙ በላይቭ እውቅና አግኝተው የተናገሩት ተናጋሪ ብቻ ሳይሆኑ እውቀና ሰጪው አወያይን ጨምሮ መከለካይ ከተፈጸመበት ክህደት አገግሞ ላከናውነው ገድልና የማይረሳ ድል ምላሹ ይህ መሆኑ እንዳስገረማቸው አመልክተዋል።

ተባባሪያችን የአብንን አመራሮች ለማነጋገር ሞክሮ ለጊዜው እንደማይችሉ በመግለጻቸው ቀደም ሲል ያተምነውን መግለጫቸውን አትመነዋል። እዚህ ላይ ያንንቡ።


DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2659 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply