እነ ልደቱ እጅ ከፍንጅ ተያዙ!

በሀምሌ ወር 2013 ዓ/ም “ከአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የቀረበ የድርድር መነሻ ሀሳብ” በሚል የትግሬ ወራሪ አላማን በሚያራምደው ርዕዮት ሚዲያ መውጣቱ ይታወሳል። ሰነዱ በአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ስም የትግሬ ወራሪን አላማ ማስፈፀም የሰሩት ነው። በዋነኛነት የትግሬ ወራሪ በሁመራ በኩል የትግራይ ክልል የሚቆጣጠረው ኮሪደር ይከፈትለት የሚል ነው። ወልቃይትና ራያ በውጭ አገር ጦር ይተዳደር ይላል። ይህን ሀሳብ መጀመርያ ስዬ አብርሃ አሜሪካ ለሚገኙ ሎቢስቶች አንስቶት እንደነበር ይታወቃል። ቀጥሎ ያሬድ ጥበቡ መፅሔት ላይ ቃል በቃል ፃፈው። ቀጥሎ እነ ልደቱ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ነን ብለው ስማቸውን ሳይጠቅሱ የቴዎድሮስ ፀጋዬው ርዕዮት ሚዲያ ላይ አስነበቡት። ትናንት ማታ ልደቱ አያሌው ስማቸውን ደብቀው ያወጡት ሰነድ የእነሱ እንደሆነ በኢትዮ 360 ወጥቶ አምኗል። ያኔ ርዕዮት ያንብበው እንጅ ለ360 ደርሶ እንደነበር እናውቅ ነበር። በትናንቱ ውይይታቸው ልደቱ “ለእናንተም ልከንላችሁ ነበር” ይለዋል ኤርሚያስን። ያውቁ ነበር፣ ኤርሚያስ የፕሮጀክቱ አካልም ነው።

ከአምስት ወር በፊት ያ ሰነድ ሲወጣ፣ በነጋታው ስለ ስዬወወ ቡድን “አዲሱ ኢህዴን መጣልህ” ብዬ ረዘም ያለ ፅሁፍ ፅፌ ዘ ሀበሻ ላይ ተነብቦ ነበር። እነ ልደቱና ኤርሚያስ ለገሰም እንዳሉበት አስረድቸ ነበር። መረጃዎቹ ስለነበሩኝ በድፍረት ስልፅ ውሸት የመሰላቸው ወገኖችና የትግሬ ወራሪን አላማ ለማሳካት ደፋ ቀና እያሉ፣ ስለ ኢትዮጵያ እናስባለን የሚሉት ሴረኞች መንጋ ደግሞ ዘምቶብኝ ነበር። ዛሬ አቶ ልደቱን ማመስገን ይጠበቅብኛል። ራሱ ይፋ አድርጎታል። በወቅቱ ያን ሰነድ ለእነ ኤርሚያስም ልኮት እንደነበር ይናገራል።

እነ ልደቱ ያን ለትግሬ ወራሪ ወደ ሱዳን መውጫ በትግራይ ክልል የሚተዳደር ኮሪደር ይከፈትለት ያሉበት ሰነድ በድብቅ ካወጡ በኋላ ሀሳቡን ብዙ የሚገዛው ሲያጡ በይፋ መጥተዋል። ማንነታቸውን ከገለፁ በኋላ የመጀመርያውና ስማቸውን ያልገለፁበት ሀሳብ በተነበበበት ርዕዮት በአቶ ልደቱ አያሌው፣ ታሬድ ጥበቡና ታምራት ላይኔ ፎቶ ታጅቦ ተነበበ። ርዕዮት የትግሬ ወራሪን አላማ በቀጥታ ማራመድ ስለጀመረና እነ ያሬድና ታምራትም ስለተወቀሱ ተቀባይነት አጡ። በሶስተኛው የትግሬ ወራሪ ቡድንን አላማ ስልታዊ ሆኖ ወደሚያራምደው ኢትዮ 360 መጡ። ታምራትና ያሬድን ቆዩ ብለው ልደቱና ጎዳና የሚባል ሰው በኢትዮ 360 ቀረቡ። በቀደም ሁለቱ ቀርበው ስለ ድርድር አወሩ። አልበቃቸው ስላለ ትናንት ልደቱን ብቻውን አቀረቡት። ልደቱም የቀደመ ታሪካቸውን ሲያወሳ በአምስት ወር በፊት ስማችን ሳይጠቀስ ሰነድ አውጥተናል ብሎ አመነ። ድሮም የታወቀ ቢሆንም፣ ሰነዱ የእነሱ ስለመሆኑ ሲናገር ከኤርሚያስ ጋር እጅ ከፍንጅ ተያዙ። ኤርሚያስንም ከአሁን ቀደም እነ ልደቱ ያወጧቸውን ሰነዶች እንደሚያውቅ ያምናል። ልደቱም ደርሷችኋል ይለዋል። (ቪዲዮው ተያይዟል)

እነ ልደቱ እየተመላለሱ የሽግግር መንግስት የሚሉን ኢትዮ 360 የሚያስተጋባላቸው በዋነኛነት የትግሬ ወራሪ ቡድን ከሱዳን ጋር የሚገናኝበት ኮሪደር እንዲሰጠው፣ ወልቃይትና ራያ ከአማራ ተነጥቀው የውጭ ጦር እንዲሰፍርባቸው የተቀመጠውን አላማ ለማሳካት ነው። ሀሳቡ የመነጫው ከእነ ስዬ አብርሃ ነው። እነ ልደቱና ኤርሚያስ ለማስፈፀም እየለፉ ነው። እየሸፋፈኑ የሽግግር መንግስት የሚሉት ይሄን የክህደት ሀሳብ ይዘው ነው። እነ ኤርሚያስ ድርድር ሲሉ የከረሙት ለዚህ እንጅ ለእውነተኛ ድርድር አይደለም። እነ ኤርሚያስ የአሜሪካ ጦር ከገባ ለኢትዮጵያ ሰላም ነው ያሉን ለዚህ አላማቸው ነው። የትግሬ ወራሪ ያሸነፈ ሲመስላቸው ሲደነፉ ከርመው ጋሸና ሲያዝ ከሚዲያ የጠፉት የትግሬ ወራሪን አላማ አስፈፃሚ ስለሆኑ ነው!

አቶ ልደቱ አያሌውን ግን ማመስገን ይገባል! የምናውቀውንም ቢሆን አምኗል። እጅ ከፍንጅ ሲያዝ እንዴት ደስ ይላል።

Via @Getachew Shiferaw

https://t.me/realseyoum/6302

Leave a Reply