የጀነራል ሰአረ መኮንን ገዳይ አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት በ27/9/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የጀነራል ሰአረ መኮንን ገዳይ አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በተከሰሰበት የህግ ድንጋጌ ስር የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ለመጠባበቅ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት ጉዳዩን የተመለከተው ሲሆን አቃቤ ህግ በሞት እንዲቀጣ ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም 4 የቅጣት ማቅለያ በማቅረቡ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ቅጣቱ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል ።

Leave a Reply