“መቀሌ ለወታደራዊ ስትራቴጂነት የቀራት ነገር የለም፤ በተራዘመ ጦርነት ላለመድቀቅ የታክቲክ ለውጥ ተደርጓል” አብይ አሕመድ

ዛሬ ማምሻውን በመቶዎች የሚቆጠሩ የሚዲያ ባለሙያዎች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝተው ነበር፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በምርጫው ወቅት ሚዲያዎች በነበራቸው አስተዋጽኦ ዙርያ ምስጋና ባቀረቡበት ንግግራቸው ስለ ትግራይ ተኩስ አቁም ዙርያ ሰፊ ገለጻ አድርገውላቸዋል

ጠሚ አብይ ሲናገሩ እስካሁን ለእርዳታ ብቻ ከ100 ቢሉየን ብር በላይ ወጭ ሁኗል። ይህም ለክልሉ ፌደራል መንግስት ሊሰጠው ከሚችለው አመታዊ በጀት 10 እጽፍ በላይ ነው። በተረጅዎች አማካኝነት ርዳታው ለጁንታው እንዲደርሰው ይደረግ ነበር ሁለት ልጅ ያለው 5 ና 7 እያለ በተረጂዎቹ አማካኝነት ጁንታው እርዳታውን ያገኝ ነበር ይህም ሁሉ ዋጋ ተከፍሎ ከውስጥም ከውጭም ያሉ አካላት ማናቸውም እየተደረገ ላለው ድጋፍ እውቅና መስጠት የፈለገ የለም::

መንግስት ይህንን ሁሉ ተቋቁሞ እየሰራ የነበረ ቢሆንም በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ከውስጥ የሚደርሱበት ጫናዎች እና በመንግስት ላይ ከውጭ እየደረሱ ያሉ ጫናዎች የሚከፈለው ዋጋ ለማን ነው የሚል ጥያቄ እንዲነሳ አድርገዋል። ምንም አቅም የሌለው ቀሪ የጁንታው አካል አዲሱ ታክቲክ እኛን አመድ እንዳደረጉን በተራዘመ ጦርነት ሀገሪቱም አብራ እንድትዳከም እና እንድትወድቅ ማድረግ ነው የሚል ነው። እኛም ይህን በመረዳት እየሞተ ካለ ቡድን ጋር አብሮ ላለመሞት የታክቲክ ለውጥ ማድረግ ያስፈልግ ነበር። ሳምንት ተወያይተን የወሰነውም መከላከያው ደጀን ወደሚያገኝበት አካባቢ እንዲመጣ ህዝቡም ከስህትቱ የሚማርበት የጥሞና ጊዜ መስጠት ለአለም አቀፍ ማህበረሰቡም እውነታውን የሚረዳበት ሁኔታን መፍጠር አለብን በሚል ነው የተወሰነው።

ጦሩ ትግራይን ለቅቆ እንዲወጣ ከወሰኑ በኋላ ትናንት እስከ እኩለ ሌሊት ከብዙ የአለም መሪዎች የስልክ ጥሪ እንደደረሳቸው በተለይም ጦሩን ሲከስሱ እና ሲወቅሱ የነበሩ ሀገራት በጦሩ መውጣት መበሳጨታቸውን ተናግረዋል፡፡
ለሚዲያ ፍጆታ የማይውለው የጠቅላይሚንስትሩ ንግግር ብዙ አስገራሚ አሳዛኝ እና ለህዝቦች አብሮነት ሲባል በትዕግስት የታለፉ አናዳጅ አዳዲስ መረጃዎች የተሰሙበት ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ገለጻ ውስጥ ግን ሁሉም ያደነቀው እና የኮራበት ነገር የመከላከያ ሰራዊቱ ጀግንነት ፣ ትዕግስት እና ያለፈባቸውን ፈታኝ ሁኔታዎችን ነው::

አንዳንዶች ተሸንፈው ነው ይላሉ 80 በመቶ ወታደራዊ ትጥቅ ከመንግስታዊ ስልጣን ጋር የያዙ አካላትን በሶስት ሳምንት አሽንፈን አሁን ማንም በሌለበት እንዴት ተሸንፈን እንወጣለን ሰው ይህን ማገናዘብ ይኖርበታል ብለዋል። በክልሉ ብሎም በመቀሌ የነበሩ ዋና ዋና የምንፈልጋቸውን ነገሮች አውጥተናል አሁን መቀሌ ምንም አይነት የስበት ማዕከል አይደለችም ምንም ለወታደራዊ ስትራቴጂነት የቀራት ነገር የለም ብለዋል። እስከ ቅርብ ሰዓት ድረስ ማንም የህውአት አመራር ወደ ከተማዋ እንዳልገባም አረጋግጠናል ብለዋል የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቅሊንጦ ኢንዱስትሪያል ፖርክ በተዘጋጀውና ከ100 በላይ ጋዜጠኞችና ከ600 በላይ ታዳዲዎች በትገኙበት ስነስርዓት ላይ ከተናገሩት

ናትናዔል መኮንን

Related posts:

ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ
ፊንላንድ 3.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሚይዙ ዋሻዎች አዘጋጀች - ለኢትዮጵያውያን ጠቃሚ የጥንቃቄ መረጃ
"አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንና የጥፋት ኃይል ዳግም ከሞከረ የማያዳግም ቅጣት ይጠብቀዋልʺ
ሻዕቢያና ትህነግ - ሰሞኑን ይህ ሆነ
ትህነግ ጦርነት እንደሚከፍት ይፋ አደረገ፤ አማራ ክልል "ለክተት ተዘጋጁ"አለ፤ መከላከያ በተጠንቀቅ ላይ ነው
ወልቃይት "የወር ስንቅህን አዘጋጅተህ ለክትተ ጥሪ ተዘጋጅ”

1 thought on ““መቀሌ ለወታደራዊ ስትራቴጂነት የቀራት ነገር የለም፤ በተራዘመ ጦርነት ላለመድቀቅ የታክቲክ ለውጥ ተደርጓል” አብይ አሕመድ

  1. ይህ ዜና ከጻፍከው 6 ሰዓት ሆኗል ማንም ኣልደገመውም ። ጠቅላይ ሚኒስትር ለመቶዎች ለዛውም ለጋዜጠኞች…? አንተ ብቻ ነው የሰማኸው ….?

Leave a Reply