የኢቶጵያ መንግስት የኢምባሲዎችን ቁጥር እንደሚቀንስ፣ ይህም የሚሆነው ኤምባሲዎቹ ወጪ ከማብዛታቸው በላይ የግለሰቦች ምሽግና መጠቀሚያ በመሆናቸው እንደሆነ አስታውቆ ነበር። ይህን ተከትሎ ለተወሰኑና ለተመረጡ አምባሳደሮች በደብዳቤ ጥሪ መላኩን አዲስ ስታንዳርድ ” ሰበር” ሲል ዘግቦታል።
ደብዳቤው በገሃድ የተሰራጨና ባለፈው ዓመት የተጠናው ጥናት ውጤት መሆኑን መንግስት በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ እንደነበር ይታወሳል። በተመሳሳይ በዲፕሎማሲው ረገድ ፋይዳ የሌላቸው ዲፕሎማቶች አገሪቱን ዋጋ እንዳስከፈሏት በተደጋጋሚ ሲተች ነበር። በዚሁ መነሻ “እንደቀድሞው በጅምላ በግዢ ዲግሪ የተመረቁ ” ሳይሆኑ አዳዲስ ዲፕሎማቶች ተመልምለው ሲሰለጥኑ እንደነበር መንግስት አስታውቆ ነበር።
የዚህ አካል እንደሆነ የተነገረለት የማስፈጸም ጅማሮ ሲሰሩበት ለነበረው ሚሲዮን ንብረት አስረክበውወደ አገር ቤት በመመልስ ሪፖርት እንዲያደርጉ የታዘዘበትን ደብዳቤ ደብዳቤው ከተላከለት አንድ አካል በመውሰድ “ሰበር” ዜና በሚል አዲስ ስታንዳርድ አትሟል። በደብዳቤው እንደተጠቀሰው ፣ጥሪ የተደረገላቸው እስከ ነሃሴ 15 ቀነ ገደብ ተሰጥቷቸዋል።
ኢትዮጵያ እንደ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ካሳ ተክለ ብርሃን፣ ተሾመ ቶጋ፣ ኩማ ድሪባ፣ አይነት ዲፕሎማቶች ያሏት አገር መሆኗ እጅግ አሳዛኝ እንደሆነ ለዲፕሎማሲው ቅረበት ያላቸው በተደጋጋሚ ሲተቹ እንደነበር።
የኢትዮ 12 የአዲስ አበባ ተባባሪ ያነጋገራቸው የብልጽግና ከፍተኛ አመራር ” ሰበር ዜና መሆን ያለበት መንግስት ህዝብን ሰምቶ እርምጃ ወሰደ የሚለው በሆነ ነበር” ሲሉ ጥቅል ምላሽ ሰጥተዋል።
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው አፍሪካ ህብረትን… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑም ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡ በሀገራችንም የሽግግር ፍትህ አስፈላጊነት ታምኖበት ፖሊሲ… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና በፕሬዚዳንቱ ስምና ፊርማ የተሰራጨው ደብዳቤ የሚሊሻ… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ሮማናት አደባባይ ላይ የተለመደው… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን