ኬንያና ኬንያታ የተመረጡበት ሚስጥር

ዋናው ሚስጥር ይሄ ነው! ኬንያ ለከፈላት የምታገለግል ሴተኛ አዳሪ ነች! በሚከፈላት ዶላር ልክ አቤት ወዴት ብላ የምታጎበድድ የፈረንጅ ተላላኪ ስለሆነች ነው በቀድሞ ፕሬዝዳንቷ ኡህሩ ኬንያታ አማካኝነት የኢትዮጵያ መንግስትና የወያኔ አደራዳሪ እንድትሆን በእነአሜሪካ የተመረጠችው። ኬንያውያን ባለስልጣናት በአውሮፓውያንና አሜሩካውያን አድርጉልን ተብለው ተጠይቀው እምቢ የሚሉት ነገር እንደማይኖር ፈረንጆቹ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ኬንያውያኑም አያሳፍሯቸውም።

ነጻ አሳብ – ሃይሌ ሙሉ

ባራክ ኦባማ ገና የ 27 አመት ወጣት በነበረበት ወቅት ከጥቂት አመታት በፊት በሞት የተለየውን የአባቱን ታሪክ(ማንነት) ለማወቅና ቤተሰቦቹንም ለመተዋወቅ ወደ ኬንያ ተጉዞ ነበር። ታዲያ ኬንያ በቆየባቸው እለታት አንድ ቀን ከሚወዳት እህቱ ኦማ ኦባማ(የአባቱ ልጅ) ጋር ምሳ ለመብላት ወደ ከተማ ጎራ ይሉና New Stanley በተባለ ሆቴል ቨረንዳ ቁጭ ብለው የሚታዘዛቸው አስተናጋጅ እስኪመጣ ይጠብቃሉ።

እነኦባማ አላፊ አግዳሚውን ቱሪስት እየቃኙ አስተናጋጅ እስኪመጣ በመጠባበቅ ላይ ባሉበት ሰአት የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አሜሪካውያን ቱሪስቶች እነሱ ከተቀመጡበት ጠረጴዛ ትንሽ ራቅ ብለው ቦታ ሲይዙ ተመለከቱ። ነጮቹ አሜሪካውያን ቱሪስቶች በተቀመጡ በቅፅበት ውስጥ ሁለት አስተናጋጆች ተወርውረው ፊታቸው ቆሙና ጆሮአቸው ጥግ ድረስ በተለጠጠ ፈገግታ ተሞልተው ትዕዛዛቸውን መቀበል ጀመሩ።

ከነጮቹ አሜሪካውያን ቱሪስቶች ቀደም ብለው የመጡት እነባራክ ኦባማ ግን የሚያስተናግዳቸው አላገኙም። በአጋጣሚ አላዩን ይሆናል ብለው ስላሰቡም ኪችን አጠገብ ለቆሙት ሁለት አስተናጋጆች እጃቸውን ማውለብለብ ጀመሩ። አስተናጋጆቹ ለተወሰነ ጊዜ የእነኦባማን የምልክት ጥሪ ያላዩ መስለው ለማለፍ ሞከሩ። መጨረሻ ላይ ግን አንድ ሽማግሌ አስተናጋጅ ፊቱን አጨፍግጎ መጣና ሜኑ አቅርቦላቸው ሄደ። ሜኑውን ጥሎላቸው የሄደው አስተናጋጅ ከብዙ ደቂቃዎች በኋላም ትዕዛዛቸውን ሊቀበል ተመልሶ አልመጣም።

በዚህ ሰአት ከእነኦባማ በኋላ የመጡት አሜሪካውያኖቹ ቱሪስቶች ያዘዙት ምግብ ቀርቦላቸው መመገብ ጀምረዋል። እነኦባማ ግን ትዕዛዛቸውን እንኳን የሚቀበላቸው አስተናጋጅ አጥተዋል። ኦማ በንዴት ጨሳለች። ባራክ ኦባማ አስተናጋጁን በድጋሜ ሲጠራው ወደ እነሱ መጣና ትህትና በጎደለው መንገድ አፉን ለጉሞ ትዕዛዛቸውን መፃፍ ጀመረ።

ይሄኔ ኦማ በድንገት ብድግ ብላ “እንሂድ!” አለችና ወደ ውጭ ማምራት ጀመረች። ወዲያውኑ ግን ወደ ኋላ ተመለሰችና ምንም አይነት ስሜት ወደማይነበብበት አስተናጋጅ ጠጋ ብላ ድምጿ በንዴት እየተንቀጠቀጠ “በራስህ ልታፍር ይገባሃል! ልታፍር ይገባሃል” አለችው። አስተናጋጁም ስርአት በጎደለው መልኩ በስዋሂሊኛ አጭር ምላሽ ሰጣት። ያኔ ኦማ ተኮሰች።

See also  "መንግስት ይሰረኝና ልጀግን፣ ታዋቂም ልሁን"ቀረጥ የማይከፍለበት የገቢ ምንጭ

“የምትመግባቸው ስንት አፎች ( ቤተሰቦች) ስለመኖራቸው እኔን አያገባኝም። የራስህን ዜጎች ግን እንደ ውሻ ዝቅ አርገህ ልታስተናግዳቸው አትችልም። ይሄውልህ…..” ብላ ከቦርሳዋ ውስጥ ተጣጥፎ የተቀመጠ አንድ መቶ ሺልንግ አውጥታ “አየህ? አዝዥ ለምመገበው ምግብ መክፈል እችላለሁ” አለችና መቶ ሺልንጉን ኖት መሬት ላይ ወርውራለት ሄደች።

እነኦባማ ከሆቴሉ ከወጡ በኋላ ፀጥ ብለው ለብዙ ደቂቃዎች በደመ ነፍስ በጎዳናው ሲጓዙ ቆዩ። መጨረሻ ላይ ግን ኦባማ ባቀረበው ሃሳብ መሰረት ከማዕከላዊ ፖስት ኦፊስ አጠገብ በሚገኝ አግዳሚ ወንበር ላይ ሲቀመጡ ኦባማ “ደህና ነሽ አይደል?” የሚል ጥያቄ ለኦማ አቀረበላት። ኦማም አንገቷን በአዎንታ እየነቀነቀች እንዲህ አለች

” ገንዘቡን እንደዛ መወርወሬ ድድብና ነው። ከሌላ አፍሪካዊት ሴት ጋር ሆኘ በእንደነዚህ አይነት ሆቴሎች ክለብ መግባት እንደማልችል ታውቃለህ? የጥበቃ ሰራተኞቹ ሴተኛ አዳሪዎች ናቸው ብለው ስለሚያስቡ ገና ከበር ነው የሚመልሱን። እዚህ በምታያቸው ትላልቅ ህንፃዎችም ላይ ተመሳሳይ ነገር ነው የሚፈፀመው። እዛ ህንፃ ላይ የማትሰራ ከሆነ እና አፍሪካዊ ከሆንክ የስራ ሃላፊነትህን እስካልነገርካቸው ድረስ እንድትገባ አይፈቅዱልህም። ከጀርመናዊ ጓደኛህ ጋር ከሆንክ ግን ፊታቸው በፈገግታ ተሞልቶ “እንደምን አመሸሽ ወይዘሪት!” ብለው ሠላምታ ያቀርቡልሃል” አለችና ኦማ አንገቷን በሃዘን ነቅነቀች። ከዚያም ቀጠል አድርጋ

“ለዚህም ነው የቱንም ያህል ጠቅላላ ብሄራዊ ምርት ቢኖራት ኬንያ የአፍሪካውያን መሳቂያ ከመሆን ያልዳነችው። ባራክ! ኬንያ ለከፈላት ሁሉ እግሯን የምትከፍት የአፍሪካ ሸርሙጣ ነች ” ስትል ነበር ምሬቷን ለወንድሟ የገለፀችው። ( Dreams from My Father, Barack Obama, page 312-314)

ዋናው ሚስጥር ይሄ ነው! ኬንያ ለከፈላት የምታገለግል ሴተኛ አዳሪ ነች! በሚከፈላት ዶላር ልክ አቤት ወዴት ብላ የምታጎበድድ የፈረንጅ ተላላኪ ስለሆነች ነው በቀድሞ ፕሬዝዳንቷ ኡህሩ ኬንያታ አማካኝነት የኢትዮጵያ መንግስትና የወያኔ አደራዳሪ እንድትሆን በእነአሜሪካ የተመረጠችው። ኬንያውያን ባለስልጣናት በአውሮፓውያንና አሜሩካውያን አድርጉልን ተብለው ተጠይቀው እምቢ የሚሉት ነገር እንደማይኖር ፈረንጆቹ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ኬንያውያኑም አያሳፍሯቸውም።

ኬንያዊቷ ቤቲ ሙሩንጊ ሊቀመንበር ሆና የመራችው የአለም አቀፉ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኤክስፐርቶች ቡድን ሰሞኑን ኢትዮጵያን በሚመለከት ያወጣው ሪፖርት የዚህ አይነተኛ ማሳያ ነው። ነጮቹ ሲያራግቡት የነበረውን ኢትዮጵያን የማሰይጠን ፕሮፖጋንዳ ሳትጨምርና ሳትቀንስ በሪፖርቷ ላይ አካታላቸዋለች። አሁን ደግሞ ተራው የኡሁሩ ኬንያታ ነው። በድርድሩ ላይ ምን አይነት ተልዕኮ ይዞ መጥቶ ምን አይነት ተፅዕኖ እንደሚፈጥር ወደፊት የምናየው ይሆናል።

See also  የኢትዮጵያን ጉዳይ ከሸተተ ስጋ ጋር ያቆራኘው [የኤርትራ/ዊው] እይታ

Leave a Reply