“ከአማራ ሕዝብ እና ከሀገር መከላከያ ሠራዊታችን ጎን በመሠለፍ መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን” የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ የሰጠው መግለጫ ሙሉ ቃል!

በሀገራችን ኢትዮጵያ ከለውጡ ማግሥት አንስቶ የሕዝቦችን ፍትሐዊ የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲ ሥርዓት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሪፎርሞችን በማካሄድ ትርጉም ያላቸው ስኬቶች ተመዝግበዋል፡፡

በሀገራችን አዲስ የለውጥ ምዕራፍ ከተጀመረበት ማግስት አንስቶ ባለፉት ሦስት አመታት ውስጥ የተጀመረው ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ እጅግ የሚበረታታ ውጤት የተመዘገበበትና አካታች እንደነበር በተለይ ለክልላችን ማኅበረሰቦች ግልጽ ነው፡፡

በአንፃሩ በሸፍጥ እና በሴራ ፖለቲካ የረዥም ዓመታት ልምድ ያካበተው የሕወሓት ሽብርተኛ ቡድን ላለፉት ዓመታት ክልላችንን ጨምሮ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶችንና በንጹሐን ዜጎች ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶችን ከማቀናበር፣ ከመደገፍ እና በቀጥታ ከመሳተፍ ባለፈ የሀገራችን መከታና የሕዝባችን አለኝታ በሆነው የመከላከያ ሠራዊታችን ላይ የክህደት ጥቃት በመፈፀም ሉዓላዊነታችንንም ጭምር አደጋ ውስጥ የጣለ የሽብር ተግባር ፈፅሟል፡፡

ህልውናውን ማቆየት የሚችለው በግጭት ብቻ እንደሆነ አጥብቆ የሚያምነው ይህ ጠብመንጃ አምላኪ ቡድን በቅርቡ ለሰላም ሲባል የተከፈተለትን በር ጥሶ በመግባት የሽብር ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትን የተለያዩ አካባቢዎች በመውረር በንጹሐን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ ሳያንስ ሕጻናትን ጠብመንጃ በማስታጠቅ እና በጦርነት እንዲማገዱ በማድረግ እጅግ አስነዋሪ ተግባር በመፈፀም ላይ ይገኛል፡፡

ይህ የሽብር ቡድን ክልላችንን እንደሁለተኛ የሽብር ማስፈፀሚያ ግንባር በመቁጠር ተላላኪዎችን በማሰልጠንና በመደገፍ የበርካታ ንጹሐንን ህይወት እንዲቀጠፍና አለመረጋጋት እንዲሰፍን በማድረግ ሀገር የማፍረስ እና ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨት ዓላማውን በተጨባጭ ከማረጋገጥ ባለፈ ወደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚወስደውን መንገድ ለማዘጋት እና የግንባታ ሂደቱን ለማስተጓጎል አበክሮ በመሥራት የተለመደ የተላላኪነት ተግባሩን ለመፈፀም ሲውተረተር ቆይቷል፡፡

በመሆኑን ይህ ሽብርተኛ ቡድን ራሱ በለኮሰው እሳት ተቃጥሎ ማለቁ የማይቀር የመሆኑ ዕውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እየተወሰደ ያለውን ሀገራዊ እርምጃ የክልላችን መንግሥትና ሕዝብ አጥብቀው ከመደገፍ ባሻገር ከአማራ ሕዝብ እና ከሀገር መከላከያ ሠራዊታችን ጎን በመሠለፍ የሚጠበቅባቸውን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡

መላ የክልላችን ሕዝቦች በሕወሓትና በተላላኪዎቹ የተዛባ የፈጠራ ትርክት እና የሐሰት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ሳትበገሩ ወንድማማችነት አንድነታችሁንና ሀገራዊ ሕብረታችሁን ይበልጥ በማጥበቅ የአካባቢያችሁን ሰላም ከማስጠበቅ ባሻገር ሀገራዊ ኀላፊነታችሁን በላቀ ሀገራዊ ስሜት እንድትወጡ የክልሉ መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የባንዳዎችን ሴራና ተንኮል በማክሸፍ ሀገራዊ አንድነታችን እና ሉዓላዊነታችን የበለጠ ይጠናከራል!!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት

ሐምሌ 9 ቀን 2013 ዓ.ም አሶሳ


 • ኦፌኮ ብሔራዊ ውይይቱ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪና ሸኔ እንዲካተቱበት ጠየቀ
  የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ በቅርቡ ይካሄዳል የተባለው የብሄራዊ ውይይት የታጠቁ ሃይሎች ሙሉ በሙሉ እንዲካተቱበት ሲል ጠየቀ። ወንጀል የሰሩና በከፍተኛ ደረጃ የመከላከያ ሰራዊትን ያሳረዱ፣ ሰላማዊ ዜጎች እንዲፈናቅሉና በጅምላ እንዲጨፈጨፉ፣ መጤ ተብለው እንዲሰደዱ አድርገዋል፣ አዘዋል፣ አመራር ሰጥተዋል በሚል ህግ ይጠይቃቸዋል የተባሉትን አስመልክቶ መግለጫው ስምና ድርጅት ጠቅሶ አልጠየቀም። ሙሉ መግለጫውን ያንብቡ የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲContinue Reading
 • ኢትዮጵያ በራሷ ዜጎች ላይ ጥቃት አልሰነዘረችም!
  ኢትዮጵያ በአሸባሪው ህወሓት የጦር ማሰልጠኛና መሳሪያ ማከማቻ ስፍራ ላይ እንጂ በራሷ ዜጎች ላይ ጥቃት አልሰነዘረችም ሲል ዋን ወርልድ አስገነዘበ። የኢትዮጵያ አየር ሃይል አሸባሪው ህወሃት በሚጠቀምባቸው የጦር ማሰልጠኛዎችና መሳሪያ ማከማቻዎቸ ላይ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ አንዳንድ የውጭ መገናኛ ብዙኋን ዜጎች ላይ ጉዳት ደርሷል በሚል የሚያቀርቡትን ዘገባ ሐሰተኝነት ዋን ወርልድ ባወጣው ሀተታዊ ጽሑፍContinue Reading
 • የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን መረጋጋት እንዲፈጠር ለሁሉም ወገኖች ጥሪ አቀረበ
  በሱዳን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን መንግስት አስታወቀ። መንግስት በካርቱም ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ ሰጥቷል። በሱዳን እየተከናወኑ ያሉ ክስተቶችን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የገለጸው መንግስት፥ ይህም በሃገራቱ ህዝቦች መካከል ለዘመናት ከኖረው ጠንካራ የወንድማማችነት ትስስር የመነጨ መሆኑን አንስቷል። መግለጫው የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን ከሲቪል እና ወታደራዊ አካላት የተውጣጣ ጥምር መንግስት እንዲመሰረት እናContinue Reading
 • ደመቀ መኮንን ዛሬ ያነጋገሯቸውን የአውሮፓ አገራት ዲፕሎማቶችን ወቀሱ
  “የአውሮፓ ህብረት እና አባል አገራት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ባከበረ መልኩ የሰብአዊ ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል” ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ። አቶ ደመቀ ዛሬ በኢትዮጵያ ከፈረንሣይ፣ ጀርመን፣ ሃንጋሪ፣ ኢጣሊያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፖርቱጋል፣ ሮማኒያ፣ ስዊድን እና ስሎቫኪያ አምባሳደሮች በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለጻ አድርገዋል። ገለጻውም በዋነኝነት በሰሜን ኢትዮጵያContinue Reading
 • ኤርዶዋን የአስር አገር አምባሳደሮች “ተቀባይነት” እንዲነሳ አዘዙ
  ቱርክ ውስጥ የሚገኙት የአሜሪካ፣ የካናዳ፣ የፈረንሳይ፣ የፊንላንድ፣ የዴንማርክ፣ የጀርመን፣ የኔዘርላንድስ፣ የኒው ዚላንድ፣ የኖርዌይ እና የስዊውዲን ኤምባሲዎች ሲሆኑ ከመካከላቸው ሰባቱ በኔቶ ውስጥ የቱርክ አጋሮች ናቸው። ፕሬዚዳንቱ “ምን መደረግ እንዳለበት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴራችን አስፈላጊውን ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ። እነዚህ 10 አምባሳደሮች በአንድ ላይ በአገሪቱ ውስጥ ተቀባይነት የሌላቸው [ፐርሶና ነን ግራታ] ሊባሉ ይገባል። በአስቸኳይም መፍትሄContinue Reading

Leave a Reply