በህገ ወጥ ንግድ ስራ ላይ በተሰማሩ ከ60 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መዉሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡ቢሮዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ ባለፉት 10 ወራት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ 60 ሺህ 3 መቶ 45 ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ፣ የኑሮ ዉድነቱ አዲስ አበባ በሚሰሩ የንግዱ ማህበረሰብ ላይ ህጋዊ እርምጃዎች እየወሰድን ነዉ ብለዋል፡፡ለዋጋ ንረቱ መባባስ የህገ ወጥ ነጋዴዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት አቶ መስፍን ፤በዚህም ከፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ማገድ ድረስ የሚደርስ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ነዉ ያሉት፡፡
በዚህም 1 መቶ 9 ነጋዴዎች ታግደዋል፤ 2 መቶ 18 ክስ ተመስርቶባቸዋል፤ ከ19ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ታሽገዋል ተብሏል፡፡በተጨማሪም ከ39 ሺህ በላይ በሚሆኑት ላይ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸዉም ምክትል ሓላፊዉ ነግረዉናል፡፡ባጠቃላይ የኑሮ ዉድነቱ እንዲባባስና የዋጋ ንረቱ እንዲጨምር ሲያደርጉ በነበሩ 60 ሺህ 3 መቶ 45 ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡
በአሁኑ ወቅት በከተመዋ የሚስተዋለዉን የኑሮ ዉድነት ለማረጋጋት ከሸማች ህብረት ስራዎች ጋራ በቅርበት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ መስፍን፣ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለሸማች ማህበራት በማመቻቸት ወደ ስራ እንደገቡም ታወቋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም እንደ አገር ከዉጭ በሚገቡ የዘይት፤ ስንዴ፤ ሩዝ፤ ስኳርና የሕጻናት ወተት ለ6 ወራት ከታክስ ነፃ እንዲገቡ ስለመደረጉም አቶ መስፍን አስታዉሰዋል፡፡
ከህገወጥ ነጋዴዎች በተጨማሪ የምርታማነት ችግርና ኮቪድ 19 ለኑሮ መወደድ የራሳቸዉ አስተዋፅኦ እንዳለቸዉ የተገለፀ ሲሆን፣ ህብረተሰቡ ከሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት እንዲጠቀሙ መክረዋል፡፡ቢሮዉ ከ1 መቶ ሺህ ኩንታል በላይ የጤፍ ምርት ለሸማች ማህበራት ማከፋፈሉን የተገለጸ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት መንግስት በድጎማ ከዉጭ ያስገባዉን የስንዴ ምርት ከሸማች ስራ ማህበራት በ 2ሺህ 5 መቶ 40 ብር ማግኘት እንደሚቻልም ኃላፊዉ ተናግረዋል፡፡
- “አሜሪካን አገር ሆነው የኢትዮጵያ ሰላም የሚያውኩ ተላልፈው ይሰጡኝ” ፖሊስ በኤርቪን ማሲንጋን በኩል ጥያቄ አቀረበአሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ የፌደራል ፖሊስ መጠየቁ ተገለጸ። በጀርመን በተመሳሳይ ስራ መጀመሩ የሚታወስ ነው። More stories በቶማስ ሳንካራ ግድያ የቀድሞው የቡሪኪና… Read more: “አሜሪካን አገር ሆነው የኢትዮጵያ ሰላም የሚያውኩ ተላልፈው ይሰጡኝ” ፖሊስ በኤርቪን ማሲንጋን በኩል ጥያቄ አቀረበ
- ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷልፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው ሃሰተኛና የፈጠራ ወሬ ሲያሰራጩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች መያዛቸው ተገለጸ። ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በህዝብ ጥቆማ… Read more: ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል
- “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረበሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የሚዳክሩበት በዚህ ጦርነት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር /… Read more: “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ
- Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside Sudanese army regulars against fighters of the Rapid Support Forces (RSF), the paramilitary group is claiming. The RSF… Read more: Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?
- Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAFSudanese warring party Rapid Support Forces has officially accused the Tigray People’s Liberation Front Fighters of fighting in Sudan in support of the Sudanese Armed Forces (SAF). Civil… Read more: Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAF