የአክሲዮን ማኀበር እና የኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ልዩነት

1/ #አክሲዮን ማህበር

የአክሲዮን ማህበር ማለት ዋናው ገንዘቡ ወይም ካፒታሉ አስቀድሞ ተወስኖ በአክሲዮን የተከፋፈለና ለዕዳው ንብረቱ ብቻ ዋስ የሆነ ማህበር ነው፡፡ ይህም ማለት አባላት አስቀድሞ ተወስኖ የተከፋፈለ አክሲዮን በመግዛት የንግድ ማህበሩ ባለቤት የሚሆኑበት ሲሆን ማህበሩ በሚያጋጥመው ማናቸውም አይነት አዳ እያንዳንዱ አባል ኃላፊነት ሊወስድ የሚችለው በማህበሩ ላይ ባለው ካፒታል መጠን ብቻ ነው ማለት ነው፡፡

የአክሲዮን ማህበር አባላት ቢያንስ አምስት መሆን ያለባቸው ሲሆን የመነሻ ካፒታሉም በሃምሳ ሺህ ብር በታች መሆን እንደሌለበት የንግድ ህጉ ላይ ተመልክቷል፡፡

መስራች አባላት ለሶስተኛ ወገኖች ለማህበሩ መቋቋም ለገቡባቸው ግዴታዎች በአንድነት ሳይከፋፈል ያለወሰን ሃላፊዎች ሲሆኑ የማኀበሩም መቋቋም የሰዎች ወይም የአባላት ማንነት ላይ ሳይሆን በኩባንያው ውስጥ የሚገባውን ገንዘብ ከግምት በማስገባት ነው፡

👉#የአክሲዮን ማኀበር ጠቀሜታ

ኃላፊነቱ የተወሰነ መሆኑ፡- እንደ ግለሰብ ነጋዴና የሽርክና ማህበር ባለአክሲዮኖች በማህበሩ ላይ ካላቸው ድርሻ በላይ በእዳ ሊጠየቁ አይችሉም፡፡

የአክሲዮን ባለቤቶችና በድርጅቱ ሥራ አመራር የተለያዩ መሆኑ፡- የአክሲዮን ማህበር የአክሲዮን ባለቤቶችና የድራጅቱ ሥራ አመራር የተለያየ በመሆኑ ድርጅቱ የተሻለ ብቃት ባላቸው ሙያተኞች ይመራል፡፡

የአክሲዮን ድርሻን ወይም ባለቤትነትን በቀላሉ ከአንዱ ወደ አንዱ ማስተላለፍ ይቻላል

የአክሲዮን ማህበራት ያልተገደበ የጊዜ ቆይታ ያላቸው መሆኑ፡- የአክሲዮን ማህበራት ህልውና እንደ ግለሰብ ነጋዴና የሽርክና ማህበር በጥቂት ግለሰቦች ላይ የተወሰነ ሳይሆን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ባለአክሲዮኖች ሊኖሩት ስለሚችሉና የአክሲዮን ዝውውር የተፈቀደ በመሆኑ የንግድ ድርጅቱ ህልውና በቀለሉ አደጋ ላይ ሊወድቅ አይችልም፡፡

በህግ የሰውነት መብት ያለው መሆኑ፡- በስሙ የመክሰስ የመከሰስ፣ ንብረት የመያዝ፣ የመበደርና የመሳሰሉትን መብቶች አንዲያገኝ ያስችለዋል፡፡

ካፒታሉን ለማሳደግ ቀላል መሆኑ፡- የአክሲዮን ማህበራት የአክሲዮን ባለቤትነት የሚሸጋገር በመሆኑ፣ ኃላፊነቱ የተወሰነ በመሆኑና የቢዝነስ ዘመኑ ያልወሰነ በመሆኑ ካፒታሉን ለማሳደግ ምቹ ሁኔታን ይፈጥርለታል፡፡ የአክሲዮን ማህበራት ካፒታላቸውን ለማሳደግ ከፈለጉ በቀላሉ አዳዲስ አክሲዮኖችን ለገበያ ማቅረብና አዳዲስ ኢንቨስተሮችን መሳብ ይችላሉ፡፡

#የአክሲዮን ማኀበር ጉዳት

የጽሁፍና የሪኮርድ ሥራዎች የሚበዙበት መሆኑ፡– የአክሲዮን ማህበራት የመመስረቻ ሰነድ /Article of incorporation or charter/ የሚያስፈልገው ሲሆን ሰነዱ ከሌሎች ማህበራት በተለየ መልኩ በርካታ ጉዳዮችን ያካተተ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አመታዊ ሪፖርት፣ የባለአክሲዮን መረጃዎች፣ የባለአክሲዮን ስብሰባዎች ቃለጉባኤ፣ የቦርድ አመራሮች ቃለጉባኤ ወዘተ.. ሰነዶችን ማደራጀትና መያዝን ይጠይቃል፡፡

See also  ሳይፋቱ ፍቺ (Defacto Divorce)

ሁለት ጊዜ ግብር የሚከፍሉ መሆናቸው፡– የአክሲዮን ማህበራት በራሳቸው ህጋዊ የሰውነት መብት ያላቸው በመሆኑ ግብር የመክፈል ግዴታ ሲኖርባቸው ካገኙት ትርፍ ባለድርሻ የሆኑ ባአክሲዮኖችም ካገኙት ገቢ ላይ ግብር የሚከፍሉ በመሆናቸው ግብር የሚታሰበው ሁለት ጊዜ ይሆናል፡፡

የአክሲዮን ማህበራትን ለማደራጀት በርካታ ሂደቶችን ማለፍ የሚጠበቅብን በመሆኑ ብዙ ጊዜንና ወጪን የሚጠይቁ መሆናቸው፡፡

የባለ አክሲዮኖች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ በእነሱ መካከል አለመግባባትና ግጭቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡

2/ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

የዚህ አይነቱ ማህበር የአባላት ቁጥር ከሁለት ያላነሰና ከሃምሳ ያልበለጠ እንደሆነ በንግድ ህጉ በግልጽ ተቀመጧል፡፡ የመነሻ ካፒታሉም ከአስራ አምስት ሺህ ብር

ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚከተሉት ጠቀሜታዎችና ጉዳቶች ይኖሩታል፡፡

👉 ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጥቅም

ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚመራው እንደ አክሲዮን ማህበር ሁሉ በቦርድ ሳይሆን በራሳቸው በባለቤቶቹ መሆኑ፡፡ ይህም ከሽርክና ማህበር ጋር ተመሳሳይነት አንዲኖረው ያደርገዋል፡፡

እንደ አክሲዮን ማህበር ሁሉ ለመመስረት ብዙ ሂደቶችን ማለፍ የማይጠይቅ መሆኑ፣

ኃላፊነተ የተወሰነ መሆኑ፡- እንደ አክሲዮን ማህበራት ሁሉ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለአክሲዮኖች በማህበሩ ላይ ካላቸው ድርሻ በላይ በእዳ ሊጠየቁ አይችሉም፡፡

ያልተገደበ የጊዜ ቆይታ ያላቸው መሆኑ፡- ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በተወሰኑ አባላት የግል ሁኔታ ህልውና በቀላሉ አደጋ ላይ ሊወድቅ አይችልም፡፡ ስለዚህ በገበያው ውስጥ ረጅም ጊዜ የመቆየት እድል አለው፡፡

ካፒታሉን ለማሳደግ ቀላል መሆኑ፡- ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ኃላፊነቱ የተወሰነ በመሆኑና ከፋይናንስ ተቋማት በቀላሉ ብድር ማግኘት የሚችል በመሆኑ ካፒታሉን ለማሳደግና ለማስፋፋት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርለታል፡፡

ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጉዳት

አክሲዮን ከማህበሩ አባላት ውጭ ለሆኑ ሰዎች የማይተላለፍ መሆኑ፡፡ የሚተላለፍ ከሆነም ሁሉም አባላት መስማማት ያለባቸው መሆኑ (ነገር ግን በውርስ ሊተላለፍ ይችላል)፣

እንደ አክሲዮን ማህበር ሁሉ አክሲዮኖችን በገበያ ላይ አውጥቶ መሸጠ እና አዳዲስ ኢንቨስተሮችን መሳብ የማይችል መሆኑ፣

ከፍተኛው የአባላት ቁጥር የተገደበ በመሆኑ እና አክሲዮን ለገበያ የማይሸጥ በመሆኑ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እድገት በእነዚህ አባላት ሀብት ብቻ የተወሰነ ነው፡፡

See also  የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ከ348 ሚሊዮን ብር በላይ ህገ-ወጥ ግዥ በሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

ጠበቃ ሳሙኤል ግርማ 0911 190 299

ምንጭ ሕግ አገልግሎት / Legal Service

Leave a Reply