ትናንት በአፋር በኩል ትንኮሳ ፈጽሞ ሜይዴይ የሚባለው ሀይሉ የተደመሰሰበት አሸባሪው ህወሓት ህጻናትን በጦርነቱ ማሳለፉን የሚያረጋግጥ ተጨማሪ መረጃዎች እየወጡ ነው። በጌታቸው ረዳ ቅስቀሳ እየተማገዱ ያሉ ሕጻናትን ያዩ የትግራይ ተወላጆች ቁጣቸውን እያሰሙ ነው።
በትናንትናው እለት በአፋር ክልል አለሌ ሱሉላ በኩል የመጣውና የጁንታው ሜይደይ ተብሎ የሚጠራ ሀይል በሙሉ መደምሰሱ የተለጸ ሲሆን፤ ጁንታው ህጻናትን በጦርነቱ አሰልፎ እንደነበር በቁጥጥር ስር ከዋሉ ህጻናት ምርኮኞች ማረጋገጥ ተችሏል።
በቆቦ በኩል ሲተነኩስ የነበረው የአሻባሪው ሀይል እንደተደመሰሰ፤ ጁንታው ያሰማራቸው በርካታ ህፃናትም መማረካቸውን ምንጮቹን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ትናንት ምሽት ላይ መዘገቡ ይታወሳል። በዚህ ግንባር ተሰልፈው በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በአፋር ልዩ ሃይል ከተያዙ ህጻናት መካከል የተወሰኑት ህጻናት ምስል ከስር ተያይዞ ቀርቧል።
ጁንታው ህጻናትን ለጦርነት እያሰለፈ መሆኑ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ቢሆንም ዓለም አቀፉ ማህበሰብ እስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። ትናንት ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ አሸባሪው ህወሓት ህጻናትን ለውትድርና እየተጠቀመ መሆኑን በመጥቀስ የባይደን አስተዳደር ምን ምላሽ አለው በሚል ጥያቄ የተነሳላቸው የአሜሪካ የነጩ ቤተመንግስት ቃል አቀባይ ጥያቄውን ሳይመልሱት ማለፋቸው ይታወሳል።
ዞባ ተምቤን እንዳለው ጌታቸው ረዳ ለፍርድ መቅረብ አለበት። ሲያስረዳም “የትግራይ ህጻናት ለምን ይጨፈጨፋሉ? ተጠያቂው እሱ ነው” ብሏል። ዞባ ይህን ይበል እንጂ ትህነግ ሓጻናትን ለጦርነት ሲያበረታታና ሲያዘገጅ የነበረው አስቀድሞ በመሆኑ ሁሉም የዚህ ወንጀል ተተያቂ መሆን እንዳለባቸው ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ተሰሚነት ያላቸው ወገኖች ቀስ እያሉ ተቃውሞ ከሚያሰሙት ጎን እየሆኑ ነው።
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው አፍሪካ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑም ተመልክቷል። የኢትዮጵያ… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡ በሀገራችንም የሽግግር ፍትህ አስፈላጊነት ታምኖበት… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና በፕሬዚዳንቱ ስምና ፊርማ የተሰራጨው ደብዳቤ… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ሮማናት አደባባይ ላይ… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን