እስራኤል “በእጆቻችን ያሉትን የሉዓላዊነት ሥልጣኖች እንጠቀማለን”-ግጭት ወደ ሙሉ ጦርነት እንዳያመራ ተሰግቷል

… ለማስቆም በየአቅጣጫው ለተግባር እንዲንቀሳቀሱ እና እንዲያወግዙት ለሁሉም ማኅበረሰብ መሪዎች፤ በተለይም ለዓረብ ማኅበረብ መሪዎች ጥሪ አስተላልፋለሁ። ሥርዓት ለማስጠበቅ፣ እንዲሁም ለእስራኤል ዜጎች እና ለእስራኤል ከተሞች ፀጥታ ለማስፈን ብሎም ደኅንነት ለማስጠበቅ በማንኛውም ኹኔታ በእጆቻችን ያሉትን የሉዓላዊነት ሥልጣኖች እንጠቀማለን

ቤኒያሚን ኔታኒያሁ

እስራኤል እና ሀማስ አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ከፈረንጆቹ 2014 በኋላ ከፍተኛውን ወታደራዊ ጥቃቶች እየወሰዱ ይገኛሉ። የእስራኤል ወታደሮች በአል አቅሳ መስጊድ ገብተው ወስደውል ያሉትን እርምጃ ተከትሎ የተጀመረው ግጭት የበርካቶች ህይወት እንዲልፍ እና የአካል ጉዳት እንዲደርስ አድርጓል ተብሏል።እስራኤል የጦር ጄቶቼ በተጠኑ የሐማስ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት ሰንዝረው በርካታ የሐማስ የስለላ መሪዎችን ገድለዋል ብላለች።

እስራኤል በጋዛ በሚገኙ የሀማስ ወታደራዊ የማዘዣ ጣቢያዎች እና የጦር መሪዎች ላይ በፈፀመቻቸው የአየር ጥቃቶች ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ የ53 ሰዎች ህይወት ማለፉ ን የሐኪም ቤት ምንጮች ጠቅሰዋል ። በተመሳሳይ ሀማስ ኢላማቸውን ወደ እስራኤል ግዛቶች ያደረጉ በርካታ ሮኬቶችን መተኮሱን አስታቋል። ስድስት እስራኤላውያን መገደላቸውና 1 ሺህ 500 ሮኬቶችን እንደተተኮሱ አልጀዚራ ከጋዛ ሰርጥ ገልጿል። እስራኤል ከሀማስ የተተኮሱ 500 ሮኬቶችን እንዳከሸፈች ዘግቧል።

በሌሎች ጥቃቶች ደግሞ ፍልስጥኤሞች ሮኬት የሚያስወነጭፉባቸው ስፍራዎች፤ የሐማስ ጽ/ቤት እና የሐማስ መሪዎች መኖሪያ ቤቶች መደብደባቸውን ገልጣለች። ኾኖም ጋዛ ውስጥ በርካታ ሰዎች የሚኖሩበት ሕንፃ በጥቃቱ መደርመሱ ተገልጧል። እስራኤል ነዋሪዎች መኖሪያቸውን ለቅቀው እንዲወጡ ቀደም ሲል ማስጠንቀቋንም ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል።

በዛሬው እለት እስራኤል በመቶዎች የሚቆጠሩ የጦር ጄቶች ድብደባዎችን ፈጽማለች። ፍልስጤማውያን ሚሊሺያዎች በበኩላቸው ወደ ቴል አቪቭ እና ደቡባዊ ከተማ ወደ ሆነችው ቤርሳቤህ በርካታ ሮኬቶችን አስወንጭፈዋል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ጥቃቱን ለማስቆም ማንኛውንም ነገር እንደሚያደርጉ አስጠንቅቀዋል። «ማድረግ የምንሻው ቀዳሚው ጉዳይ ይኽን ያለመረጋጋት መአበል ማስቆም መሆኑን መረዳት ያስፈልገናል።

ይኼን ለማስቆም በየአቅጣጫው ለተግባር እንዲንቀሳቀሱ እና እንዲያወግዙት ለሁሉም ማኅበረሰብ መሪዎች፤ በተለይም ለዓረብ ማኅበረብ መሪዎች ጥሪ አስተላልፋለሁ። ሥርዓት ለማስጠበቅ፣ እንዲሁም ለእስራኤል ዜጎች እና ለእስራኤል ከተሞች ፀጥታ ለማስፈን ብሎም ደኅንነት ለማስጠበቅ በማንኛውም ኹኔታ በእጆቻችን ያሉትን የሉዓላዊነት ሥልጣኖች እንጠቀማለን።»

የፍልስጥኤም ምንጮች፦የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ግብፅ፣ ኳታር እና የተባበሩት መንግሥታት ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካም ብለዋል። ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት ለ50 ቀናት ቀጥሎ በነበረው የእስራኤል ፍልስጥኤም ግጭት በርካቶች መገደላቸው እና ንብረት መውደሙ ይታወሳል።

ሩስያ እና ቻይና ደም አፋሳሹ የእስራኤል ፍልስጥኤም ግጭት «እጅግ እንዳሳሰባቸው» ተናግረዋል። የሩስያ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ሠርጊዬ ቨርሺኒን፦ እስራኤል በፍልስጥኤም ግዛቶች ውስጥ ሁሉንም ሠፈራዎች «በአስቸኳይ» እንድታቋርጥ ጥሪ አስተላልፈዋል። ሞስኮ የእየሩሳሌም የይርጋ ጥያቄ «ሊከበር ይገባል» ብላለች። ቻይና በበኩሏ፦ የእስራኤል እና የፍልስጥኤም ግጭት እጅግ እንዳሳሰባት በመግለጥ በአስቸኳይ እንዲያበቃ፤ ሁሉም ወገኖችም ከተጨማሪ ጥፋት እንዲታቀቡ አሳስበዋል።

BBC, DW


 • ኢትዮጵያ እንደገና አንድ ሆና ተሰፋች፤ ደስም አለን!
  ዛሬ ሁሉም ዜጋ ” አገሬ” አለ። ያለ ልዩነት ” ማን እንደ አገር” ብሎ ጮኸ። በራሱ ተነስቶ ” እኔም ወታደር ነኝ ” አለ። ከባህር ማዶ ያሉ ከሃጂዎች አገር ለማፍረስ ሲማማሉ፣ የስልጣን ክፍፍል ሲያደርጉ፣ ግማሾቹ በስተርጅና ሲቀሉ፣ ትርፍራፊ የሚጣልላቸው ሚድያዎች አገራቸው ላይ አድማ ሲጠሩ፣ አንዳንድ ባለሃብት ነን ባዮች ቀን ቀን ቤተ ክርስቲያን፣Continue Reading
 • “አሸባሪው ትህነግ”በማይጠብሪ፣ በዋግ በአበርገሌ አከባቢ፣ በራያና በአላማጣ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባታል
  የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት በአውደ ዉጊያ ዉሎው ጠላትን እያንበረከከ ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑን አስታወቁ። በማይጠብሪ፣ በዋግ በአበርገሌ አከባቢ፣ በራያና በአላማጣ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባታል ዋና ዳይሬክተሩ በቅጥረኛ የትህነግ ተቀጣሪ አክቲቪስቶች በሀሰት እንደሚነዛው መረጃ ሳይሆን በማይጠብሪ፣Continue Reading
 • አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቅጥፈት መግለጫ አወጣ፤ ቡድኑንን እየበጠበጠ ነው
  “ሕዝባችንና መንግስታችን” የሚል ተደጋጋሚ ሃረግ በመጠቀም መገልጫ ያሰራጨው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3000 መሰናክል እንዲወዳድር መደረጉ አግባብ እንዳልሆነ አስታወቀ። በመግለጫው የሰጠው ምክንያትና ቀደም ሲል ያቀረበው ሪፖርት አይሰማማም። ፌዴሬሽኑ በቶኪዮ ኦሊምፒክ አጠቃላይ ሂደት ላይ ያሰራጨው መግለጫ ” ከውዲሁ የለሁበትን” ዓይነት ሲሆን ውጤቱን አብዝቶ ሊጎዳ የሚችልና ኢትዮ 12 ባደረገው ማጣራትContinue Reading
 • (no title)
  Continue Reading

Leave a Reply