(ይትባረክ ዋለልኝ)
የ2013 ዓ.ም “ ዘጠነኛው የበጎ ሰው ሽልማት” ዛሬ እሑድ ነሐሴ 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል አዳራሽ ተካሂዶ ነበር።በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ነበሩ::በዚህ ለዘጠነኛ ጊዜ በተዘጋጀው የ 2013 ዓ.ም የበጎ ሰው የሽልማት ፕሮግራም ላይ በ አስር ዘርፎች ሽልማት ተሰጥቷል:: በዚህም መሰረት በሁሉም ዘርፍ እጩ ሆነው የቀረቡትንና ተሸላሚዎቹ እንደሚከተለው ቀርበዋል::
1. በኪነጥበብ ዘርፍ እጬዎች የነበሩት
_ በዕውቀቱ ስዩም
_ ጃርሶ ሞትባይኖር ኪሩቤል
በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት
በዕውቀቱ ስዩም ነው:: የበእውቀቱ ስዩምን ሽልማት የተቀበሉት አባቱ አቶ ስዩም መሰለ ናቸው::
2.በማህበራዊ ጥናት ዘርፍ እጬዎች የነበሩት
_ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ
_ ፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ
_ ፕሮፌሰር አሉላ ፖንክረስት
በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት
ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ ናቸው::
3 . በቅርስና ባሕል ዘርፍ እጬዎች የነበሩት
_ ዶ/ር መንግስቱ ጎበዜ
_ አቶ ሲሳይ ደምሴ
_ ቢላል ሐበሽ ሙዚየም የልማትና የበጎ አድራጎት ማህበር ሲሆኑ
በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት
ቢላል ሐበሽ ሙዚየም ናቸው::
4.በመምህርነት ዘርፍ እጬዎች የነበሩት
– ዶ/ር ልዑል ሰገድ አለማየሁ
– ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ
– ፕሮፌሰር ጥሩሰው ተፈራ ሲሆኑ
በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት
ዶ/ር ልዑልሰገድ አለማየሁ ናቸው::
5.በሚዲያና በጋዜጠኝነት እጬዎች የነበሩት
_ ጋዜጠኛ ደጀኔ ጥላሁን
_ ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ
_ ስለአባት ማናዬ
በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት
ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ ናቸው::
6. በበጎ አድራጎት እጬዎች የነበሩት
– ማርያም ሙኒር
– እልልታ ውመን አት ሪስክ ግብረሰናይ ድርጅት
– አቶ አማረ አስፋው ሲሆኑ
በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት
አቶ አማረ አስፋው ናቸው::
7. በሳይንስ ዘርፍ እጬዎች የነበሩት
_ ዶ/ር አየለ ተሾመ
_ ኤመሬትስ ፕሮፌሰር አለማየሁ ተፈራ
_ ፕሮፌሰር የወይንሐረግ ፈለቀ ሲሆኑ
በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ
ኤመሬትስ ፕሮፌሰር አለማየሁ ተፈራ ናቸው::
8. በንግድና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ እጬዎች የነበሩት
_ ወ/ሮ ብሩክታዊት ጥጋቡ
_ አቶ በላይነህ ክንዴ
_ ፓን አፍሪክ ግሎባል ኩባንያ
በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት
አቶ በላይነህ ክንዴ ናቸው::
9. መንግስታዊ የስራ ኃላፊነት በብቃት በመወጣት ዘርፍ እጬዎች የነበሩት
_ ኢንጂነር ሐብታሙ ተገኝ
_ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ
_ አቶ ይኩኑዓምላክ መዝገቡ
በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት
ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ናቸው::
10.ኢትዬጵያ መልካም ስራ የሰሩ ዲያስፖራዎች ዘርፍ እጬዎች የነበሩት
_ ዶ/ር እንዳወቀች ዘርጋው
_ አለምፀሐይ ወዳጆ
_ ኤልያስ ወንድሙ
በዚህ ዘርፍ ከእነዚህ እጩዎች መካከል የ2013 ዓ .ም የበጎ ሰው ተሸላሚ የሆኑት
አቶ ኤልያስ ወንድሙ ናቸው::
የ2013 ዓ.ም የበጎ ሰው ልዩ ተሸላሚ የሆኑት
ጸሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሐብተወልድ ናቸው::
በዛሬ የ2013 ዓ.ም የበጎ ሰው ተሸላሚዎቹ ሽልማት የተሰጠ ሲሆን በየዘርፉ እጩ ሆነው ለቀረቡት የሰርተፍኬት ሽልማት ተሰጥቷቸዋል:: በዚህ የሽልማት ፕሮግራም ላይ መምህርና ተማሪ የሆኑት ሁለት ሰዎች ተሸልመዋል:: ተሸላሚው መምህር ኤመሬትስ ፕሮፌሰር አለማየሁ ተፈራ ሲሆኑ ተማሪው ተሸላሚ ደግሞ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ናቸው:: ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በዛሬው እለት ከመምህሬ ጋር በመሸለሜ እጅግ ደስተኛ ነኝ ብለዋል::