አዲስ ጅሃዳዊ ቡድን የሱዳን ሰላዮችን መግደሉን አስታውቋል

ራሱን የስብከት እና የትግል ንቅናቄ ብሎ የሚጠራው አዲስ ጅሃዳዊ ቡድን የሱዳን ሰላዮችን መግደሉ ተነግሯል
እምብዛም እውቅና የሌለው ራሱን የጅሃዲስት ቡድን በሚል የሚጠራው አዲስ ሃይል ስድስት የሱዳን የስለላ መኮንኖችን መግደሉን አስታውቋል በትላንትናው እለት አስታውቋል።
እንደ ቢቢሲ አፍሪካ ዘገባ መንግስት ጥቃቱ ራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ ከሚጠራው (አይ ኤስ) ቡድን ታጣቂዎች ጋር እንደሚገናኝ ገልጻል ፡፡
ይህንን የመንግስት ወንጀላ ያጣጣለው ራሱን የስብከት እና የትግል ንቅናቄ ብሎ የሚጠራው ጅሃዲስት ቡድን ከአይ ኤስ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ቢያሳውቅም ጉዳዩን ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡
ባለስልጣኖቹ በማክሰኞ ጥቃት አምስት አባሎቻቸው እንደተገደሉባቸው አምነው 11 የቡድኑን ታጣቂዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አሳውቀዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት የሱዳን ጦር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራን ማክሸፉን ተከትሎ በሽግግር መንግስቱ በሲቪል አስተዳዳሮች እና በወታደራዊ ክንፎች መካከል ያለውን ግንኙነት በይበልጥ መካረሩ እየተነገረ ነው።
ያይኔአበባ ሻምበል FM 108
መስከረም 19 ቀን 2014 ዓ.ም
Related posts:
«ድርድር አያዋጣንም ሀገሪቷን ማተራመስ አለብን» ታዋቂው ግብጻዊ ፓለቲከኛ
ስምንት የነዳጅ ቦቴዎች ተወረሱ
ሱዳን ትሪቡን ያሰራጨው አሳሳች ምስል!
ከትግራይ የመጡ የሽብር ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ
የጌታቸው አሰፋ ፍርድ
“ጠላት አርፎ እንደማይተኛ ታውቆ ለየትኛውም ተጋድሎ ራስን ማዘጋጀት” አማራ ክልል
የፓትሪያርኩ የውጭ ጉዞና - "ተቀነባብሯል" የሚባለው ሴራ እያነጋገረ ነው
በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕከተኛ ራሳቸውን አሰናበቱ፤ ለአራተኛ ጊዜ የተሰማው ስንብት አነጋግሪ ሆኗል