የውጭ ሀገር ገንዘቦችን በማተም እና የተለያዩ ማዕድኖችን በመያዝ ወንጀል የተከሰሱት የፀሐይ ሪል ስቴት ጀነራል ማናጀርን ጨምሮ 9 የውጭ ሀገር ዜጎች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ።
ፍርድ ቤቱ የተከሳሾቹን የዋስትና ጥያቄና የዐቃቤ ሕግ የመቃወሚያ ክርክሮችን መርምሮ የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ ያደረገው።
የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ ያደረገው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ልደታ ምድብ 8ኛ የገቢዎችና ጉሙሩክ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
በቀረበባቸው ተደራራቢ ክስ ላይ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ከተደረገባቸው ተከሳሾች መካከል የፀሐይ የሪል ስቴት መስራች፣ ባለድርሻ እና ስራ አስኪያጅ ቺያን ኩዊን ጨምሮ ዘጠኝ የውጭ ሀገር ዜጋ የሆኑ ተከሳሾች ናቸው።
የፍትህ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ የወንጀል ተሳትፎ ጠቅሶ ተደራራቢ ሰባት ክሶችን በየድርሻቸው አቅርቦባቸው ነበር።
በተለይም ባቀረበው በ1ኛ ክስ ላይ ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ በቀረበው ክስ ላይ እንደተመላከተው የወንጀል ህግ አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 1/ሀ እና አንቀጽ 356 ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳሾቹ ፀሀይ ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ውስጥ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ቤት ውስጥ ከነሃሴ 24 ቀን 2015 ዓ. ም እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ሀሰተኛ ገንዘብ ለመስራት የሚያገለግሉ መሳሪያዎች፣ የተለያዩ ኬሚካሎች እና ወረቀቶች በመጠቀም ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር፣ ዩሮ፣ የእንግሊዝ ፓውንድ፣ የቻይና ይዋን እና የሌሎች የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችን አመሳስለው በማተም ላይ እያሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል የሚል ክስ ቀርቧል።
በሁለተኛው ክስ ደግሞ የወንጀል ህጉ አንቀፅ 32/ንዑስ ቁጥር 1/ሀ እናአንቀጽ 371 ንዑስ ቁጥር 2 ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ፣ በሚኖሩበት ቤት ውስጥ ገንዘቦች ለመስራት የሚያገለግሉ፣ 2 የብር ማተሚያ ማሽን እና የተለያዩ ኬሚካሎች ማለትም በጀሪካን፣ በጠርሙስ፣ በብልቃጥ እና በበርሜል ባለ 500 ኖት ሀሰተኛ ዩሮ ለመስራት የተዘጋጀ 60 ሚሊየን 750 ሺህ ብር የሚገመት ነጭ ወረቀት ብዛት በነጠላ 121 ሺህ 500 ዩሮ እና 42 ሚሊየን 400 ሺህ ዶላር የሚገመት ሀሰተኛ ዶላር ለመስራት የተዘጋጀ ባለ 100 ኖት 424 ሺህ አረንጓዴ ወረቀት የተገኘባቸው መሆኑን ዐቃቤ ህግ ጠቅሷል።
በተጨማሪም 16 ሚሊየን 150 ሺህ የሚገመት ነጭ የዶላር ወረቀት፣ የተለያየ ነጭ ዱቄት፣ አንዱ እሽግ በውስጡ 500 ወረቀት የያዘ 32 እሽግ በብር ቅርፅ የተቆራረጡ ወረቀቶች፣ በአልሙንየም የተጠቀለለ በገንዘብ ቅርፅ የተቆረጠ ጥቁር ቀለም ያለው ወረቀት፣ 28 እሽግ አንዱ 500 የያዘ የገንዘብ መስሪያ ወረቀት፣ እንዲሁም ገንዘብ ለመስራት የሚያገለግሉ መስሪያና መሳርያዎች ይዘው በፀጥታ አካላት በተደረገ ክትትል ይዘውት የተገኙ መሆኑን ዐቃቤ ሕግ ጠቅሶ ሀሰተኛ ነገሮችን ለመስራት የሚያገለግሉ መስሪያ እና መሳሪያዎች መያዝ ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።
3ኛ ክስ ደግሞ በ1ኛ ተከሳሸ ላይ ብቻ የቀረበ ሲሆን÷ በዚህም የወንጀል ህግ አንቀፅ 359 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ በጳጉሜን 1 ቀን 2015 ዓ.ም በተደረገው ፍተሻ ሀሰተኛ የሆኑ ባለ 100 የገንዘብ ብዛቱ 297 ሺህ 400 የአሜሪካ ዶላር፣ ባለ 50 የገንዘብ ብዛቱ 36 ሺህ 250 የእንግሊዝ ፓውንድ፣ ባለ 500 ዩሮ 62 ሺህ የሆነ፣ እና ባለ 200፣ 650 ሺህ 600 ዩሮ፣ እንዲሁም ባለ 1 ሺህ 567 የቻይና ዩዋን ይዞ የተገኘ መሆኑ ተጠቅሶ ተከሳሹ ላይ ሀሰተኛ ገንዘብ ይዞ መገኘት ወንጀል ክስ ቀርቧል።
በሌላ በኩል በአንደኛ ተከሳሽ ላይ በሌላኛው በቀረበበት 5ኛ ክስ ላይ ደግሞ ተከሳሹ ማዕድን የመያዝ ፍቃድ ሳይኖረው ክብደቱ 108 ነጥብ 43 እና 51 ነጥብ 88 ግራም የሚመዝን ኦፓል የተፈጥሮ ማዕድን እና 4 ነጥብ 99 ግራም የሚመዝን ኳርትዝ እንዲሁም 77 ነጥብ 71 ግራም የሚመዝን አጌት የተፈጠሮ ማዕድን እና 104 ነጥብ 59 ግራም የሚመዝን ማግኔታይት የተፈጥሮ ማዕድን ይዞ የተገኘ መሆኑ በክሱ ተጠቅሶ ፍቃድ ሳይኖረው የተፈጥሮ ማዕድን መያዝ እና የአዋጁን ድንጋጌዎች መተላለፍ ወንጀል ክስ መቅረቡ ይታወሳል።
በተለይም አንደኛ ተከሳሽ በኮንትሮባንድ ወንጀል ክስ የቀረበበት ሲሆን÷ ሌሎቹ ማለትም ከ2ኛ እስከ 9ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተከሳሾች ላይ ደግሞ የፀና የመኖሪያ ፍቃድ ሳይኖር በሀገር ውስጥ መኖር ወንጀል ክስ ቀርቧል።፡
በአጠቃላይ ተከሳሾቹ ላይ የቀረበባቸው ተደራራቢ የወንጀል ክስን በችሎት እንዲደርሳቸው ተደርጓል ማንነታቸውም ተረጋግጧል።
ከ1 እስከ 6 ኛተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሽ ጠበቆች የአንደኛ ተከሳሽ የልብ ህመምተኛ መሆናቸውንና ቋሚ አድራሻ እንዳላቸው ጠቅሰው የዋስትና መብት እንዲፈቀድ ጠይቀዋል ነበር።
በተጨማሪም ከ2 እስከ 6ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ደንበኞቻቸውን በሚመለከት የቀረበባቸው ክስ ከ7 ዓመት በላይ የማያስቀጣ የወንጀል ድንጋጌ መከሰሳቸውን ጠቅሰው የዋስትና መብት ጥያቄ አንስተዋል።
በዐቃቤ ሕግ በኩል ደግሞ ተከሳሾቹ ከተከሰሱበት ተደራራቢ ክስ የቀረበባቸው እና ቋሚ አድራሻ የሌላቸው ከመሆኑ አንጻር ቢወጡ የዋስትና ግዴታቸውን አክብረው ሊቀርቡ አይችሉም ሲል በመቃወም ተከራክሯል።
የሰበር ሰሚ ችሎት ተደራራቢ ክሶችን በሚመለከት በልዩነት ዋስትናን ሊያስከለክል ስለሚችል ድንጋጌዎች በማብራራት በመከራከር ተጠርጣሪዎቹ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ጠይቋል።
ሌሎቹ ከ7ኛ እስከ9ኛ ተራ ቁጥር የተከሰሱ በኤሌክትሪክ ባለሙያ እና ሁለት እግር ኳስ ተጫዋች ነን ያሉ የላይቤሪያና የጊኒ ዜግነት ያላቸው ተከሳሾችን በሚመለከት በችሎት የተገኙ ጠበቃ ድጋፍ ለማድረግ በማስፈቀድ ተከሳሹ በቱሪስት ቪዛ ሀገር ውስጥ በገቡ በሁለት ሳምንታቸው በፀሐይ ሪል ስቴት በሄዱበት መያዛቸውን ጠቅሶ ቪዛና ፓስፖርት ያላቸው መሆናቸውን በማመላከት ከሀገር እንዳይወጡ እግድ ተጥሎ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጥያቄ ቀርቦ ክርክር ተደርጎበት ነበር።
የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው ችሎቱ ተከሳሾቹ ላይ የቀረበው ተደራራቢ ከባድ ወንጀል መሆኑን ተከትሎ ቢወጡ ተመሳሳይ ድርጊት ላይ ሊሳተፉና ቋሚ አድራሻ ስለሌላቸው የዋስትና ግዴታቸውን አክብረው ላይቀርቡ ይችላሉ የሚለውን ግምት በመያዝና እንዲሁም ዋስትና ሊገደብ የሚችሉባቸው የሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀመጣቸው የድንጋጌ ነጥቦች በምክንያትነት በመጥቀስ የተከሳሾቹን ዋስትና ጥያቄ አለመቀበሉን አብራርቷል።
የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው ተከሳሾች ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ በማለት ከቀጠሮ በፊት የሚቀርብ የክስ መቃወሚያ አስተያየትና የዐቃቤ ሕግ መልስን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለህዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በታሪክ አዱኛ – FBC
- ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!በፖለቲካም ሆነ በአካባቢያዊ አጀንዳ ነፍጥ ያነገቡ እና ጦርነትን አማራጭ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ኢ -መደበኛ አደረጃጀቶች ሁሉ የጦር መሳሪያ ፍላጎት ይኖራቸዋል፡፡ የጦር መሳሪያ ፍላጎት ሲኖር መሳሪያ ሸጦ ትርፍ ማጋበስ የሚፈልግ ይፈጠራል፡፡ የጦር መሳሪያ ፈላጊና አቅራቢ ሲገናኙ የጦር መሳሪያ ልክ እንደ ሌሎች መደበኛ የግብይት እቃዎች ሁሉ በግብይት ሥርዓት ውስጥ ይገባል፤ የጦር መሳሪያ ደግሞ፣ የፈለገ አካል ሁሉ የግሉ ሊያደርገው… Read more: ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!
- ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?ያለፈውን ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ሥነ መንግሥት ታሪክ በጥሞና የተከታተለ ኢትዮጵያዊ የግዛት አንድነቷን እና የፖለቲካ ነጻነቷን በአንጻሩ ጠብቃ የኖረች ሀገር፤ ከአሁን በኋላ በዜጎቿ ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ሃቀኛ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መስርታ ሁሉንም ዜጎቿን በእኩልነት ማቀፍ ካልቻለች እንደ ሀገር በጋራ የመቀጠል እጣ ፋንታዋ የመነመነ መኾኑ ይገለጥለታል፡፡ በርካቶች የሚስማሙበት አንድ ሃቅ ቢኖር ኢትዮጵያ ውስጥ እዛም እዚህም… Read more: ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?
- የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስአንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ የልብ በሽታና በደም ዝውውር ማነስ ምክንያት ለሚከሰት የአዕምሮ ሥራ መታወክ (ስትሮክ) የመጋለጥ ዕድሉ እጅግ በጣም ከፍተኛ ይሆናል፡፡ በኢትዮጵያ ከጠቅላላው ሕዝብ 20 በመቶው ከፍተኛ የደም ግፊት መጠን እንዳለበትና ከእነዚህ መካከል አብዛኛዎቹ ከፍተኛ የደም ግፊት መጠን እንዳለባቸው እንደማያውቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጥቁር… Read more: የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
- የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶችየስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ የህመም አይነት ነው። በዋናነት አራት የስኳር ህመም አይነቶች አሉ፤ እነርሱም አይነት አንድ፣ አይነት ሁለት፣ በእርግዝና ወቅት የሚከሰትና በሌሎች ተዛማች ህመሞች የሚመጣ የስኳር ህመም ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ሁለቱ (አይነት አንድ፣ አይነት ሁለት) ዋና የስኳር አይነቶች ሲሆኑ÷ አይነት አንድ የሚባለው ኢንሱሊን የሚያመነጨው በተለምዶ… Read more: የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
- ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮ ጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል። ትዳርንም ሊያፈርስ ይችላል። “ስለ ባለቤቴ ማንኮራፋት ቀላል አድርጌ ከቤተሰብ እና ከጓደኞቼ ጋር እቀልዳለሁ። እውነታው ግን ውስጤ በእጅጉ ይረበሻል” በማለት የሲንጋፖር ዜጋ የሆነችው የ45 ዓመቷ ባለትዳር አሩኒካ ሴልቫም ትናገራለች። ይህች ባለትዳር እና የልጆች እናት “ስለጉዳዩ ባለቤቴን ባናግረው… Read more: ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?