ኢንጂነር ስለሺ ሹመታቸው ይፋ ሆነ – ዶ/ር ምህረት ተካተዋል

የአዲሱ ካቢኔ ስም ዝርዝርና ሹመት ሲጸድቅ ስማቸው ተዘሎ የነበሩትና ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆነው የነበሩት ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ሆነ ሞሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አስታወቀ። እሳቸው “በተመደብኩበት ሁሉ አገሬን አገለግላለሁ” ሲሉ በእሳቸው ቦታ ለተሾሙት መልካም የስራ ጊዜ ተመኝተው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች መስጠታቸውን ጠቅሶ ጽህፈት ቤታቸው ይፋ እንዳደረገው ዶክተር ምህረት ደበበ -ዶ/ር ምህረት ደበበ – የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት መሆናቸው ታውቋል።

በዛሬው እለት አቶ ተፈሪ ፍቅሬን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ የሾሙ ሲሆን ለ4 ከፍተኛ የሃላፊነት መደቦችም በሚኒስቴር ማእረግ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡-

1. አቶ አደም ፋራህ – በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ

2. አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ – በሚኒስትር ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ

3. ዶ/ር ስለሺ በቀለ – በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ

4. ዶ/ር ለገሰ ቱሉ – በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ በተጨማሪም፡-

-ዶ/ር ምህረት ደበበ – የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት፤

– አቶ ፍሰሃ ይታገሱ – የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ –

– እንዲሁም አቶ አብዱራህማን ሩቤ – የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል፡፡

Leave a Reply