የኦሮሞን ህዝብ ለማደናገር ሸኔ በሚል የተደራጀው አሸባሪ ቡድን እድል ተሰጥቶት ወደ ስልጣን ከመጣ በቀሉ የሚከፋው በዋናነት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ነው።
የሕወሓትና የሸኔ ጥምረትም የስም ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ሁለቱም አንድ ናቸው ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይና ደህንነት ቋሚ ኮሚቴ አባል እና የኦነግ መስራች የሆኑት ዲማ ነገዎ(ዶ/ር) አስታወቁ።
ዶ/ር ዲማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት አስተያየት፣ አሸባሪው ሕወሓትና ሸኔ የስም ልዩነት ካልሆነ በስተቀር በተግባርም በዓላማም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች በመሆናቸው ሁለቱን የተለያዩ አካላት አድርጎ ማየት አይገባም።
አሸባሪው ሕወሓት ዛሬ ህዝቡን ለማደናገር የኦሮሞ ህዝብ ወገንተኛ ለመምሰል ከፍተኛ መፍጨርጨር እያደረገ መሆኑን ያነሱት ዶ/ር ዲማ፣ ዳሩ ግን በታሪክም ሆነ በተግባር ወደኋላ መለስ ተብሎ ከተቃኘ ቡድኑ በማስተር ፕላን ምክንያት በርካታ የኦሮሞ ወጣቶች በጠራራ ፀሐይ ያለምንም ርህራሄ በጥይት የፈጀ፣ ይሄ ሳያንስ የእሬቻ በዓል ለማክበር የወጡ የኦሮሞ ንጹሃንን በመጨፍጨፍ ጥቁር ጠባሳና ዘግናኝ ድርጊቶችን ጥሎ ያለፈ ቡድን መሆኑን አስታውሰዋል ።
የሽብር ቡድኑ ፍላጎት ትናንትም ዛሬም ኦሮሞን በመስበር የኦሮሞን ሀብት መውረስ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ዲማ፣ ለዚህ ዓላማ ማሳኪያም እውነተኛ የኦነግ ታጋዮችን በመግደል እንዲሁም በማሰር በሕይወት የተረፉትን ከአገር በማባረር ከአሥር ዓመታት ወዲህ ደግሞ ተላላኪውን በማደራጀትና በኦሮሞ ስም አምሳያውን ቡድን በማቋቋም ኦሮሞን የማደናገር ሥራ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
ቡድኑ ኦሮሞን ለማደናገር በኦሮሞ ስም ሸኔ በሚል ስም ተደራጅቶ መምጣቱ ምናልባት ለማያውቁት ለአንዳንዶቹ ማደናገሪያ ቢሆንም እውነታው ግን የሕወሓት ትልቁ ዓላማ እንደ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለየ መልኩ ደግሞ የስልጣኑን እድሜ ያሳጠረውን ኦሮሞን ህዝብ ክፉኛ ለመበቀል መሆኑ መታወቅ አለበት ያሉት ዶ/ር ዲማ፣በቡድኑ አምባገነናዊ አገዛዝ በግፍ ያልተገደለ፣ያልተሰቃየና አገር ጥሎ ያልጠፋ ብሔር ባለመኖሩ የቡድኑ ዳግም ወደ ስልጣን የመመለስ ቅዠት ከንቱ ለማድረግ በጋራ መቆም ጊዜው አሁን ነው ብለዋል።
አሸባሪው ሕወሓት ትንሽ ቀዳዳ አገኝቶ ወደ ስልጣን የመመለስ እድል ካገኘ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንገቱን ደፍቶ የሚኖርባት የሰቆቃ ምድር እንደምትሆን የተናገሩት ዶክተር ዲማ ህዝቡ አገሩን ከምስቅልቅል፤ ራሱንም ከስቃይ ለመታደግ ብቸኛው አማራጭ በጋራ መታገል መሆኑንም አስምረውበታል።
በመጨረሻም የሽብር ቡድኑ በሸረበው ሴራ የህይወት መስዋዕትነት በመክፈልና በመፈናቀል እንዲሁም በውጭ ኃይሎች ጫና ሳይንበረከክ የጋራ ጠላቶቹን በአንድነት በጽናት እየተፋለመ ላለ ለኢትዮጵያ ህዝብም ምስጋና አቅርበዋል።
ምንጭ :ኢ.ፕ.ድ
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች