በአንጸባራቂ ድል ወደፊት እየገሠገሡ የሚገኙት ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ የጸጥታ ኃይሎች አብዛኞቹን የዋግ ኅምራ አካባቢዎች ነጻ በማውጣት የዞኑን ዋና ከተማ ሰቆጣን ተቆጣጥረዋል፡፡
አካባቢው ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በሚወጣበት ጊዜ የዋግ ኽምራ ሚሊሻዎች አስደናቂ ጀብዱ የፈጸሙ ሲሆን፣ የአካባቢው ሕዝብም ከመከላከያ ሠራዊትና ከአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመጣመር ደጀንነቱን በብቃት አሳይቷል፡፡ የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ የጸጥታ ኃይሎች ቀሪዎቹን ቦታዎች እያጸዱ፣ የፈረጠጠውን የአሸባሪውን ጀሌ እየደመሰሱ፣ ወደ አበርገሌ በመገሥገሥ ላይ ይገኛሉ፡፡
በተያያዘም ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች፣ በቆቦ ግንባር በአንድ በኩል ዋጃና ጥሙጋ ላይ የሠፈረውን የጠላት ኃይል በመጥረግ ወደ አላማጣ ከተማ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ተኩለሽን ተቆጣጥረው በማጽዳት፣ ወደ መረዋና ኮረም እየገሠገሡ ይገኛሉ፡፡
በእሳታማው የጀግኖች ክንድ የተደቆሰው አሸባሪው ሕወሐት፣ ተቸካይና ኋላ ቀር በሆነ የጦር ዘይቤ፣ ዕብሪትን እንደ መሣሪያ በመጠቀም፣ ከገባባቸው የአማራና የአፋር ክልል አካባቢዎች እንደገባ መውጣት አቅቶት፣ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሣራ ደርሶበት ተደመስሷል፡፡
ይሄንን ሐፍረቱን መሸፈን ሲያቅተው በአንድ በኩል ለሰላም ሲል የወጣ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለሽንፈቱ ውኃ የማይቋጥር ምክንያት እያቀረበ፣ አድኑኝ የሚል እሪታ እያሰማ፣ በለመደው ውሸት የትግራይን ሕዝብና የዓለምን ማኅበረሰብ ለማደናገር እየሞከረ ይገኛል፡፡
በዚህ ጦርነት የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ የሆነውና አሸባሪውን ሕወሐት በጀግንነት የታገለው የዋግ ኅምራ ሕዝብ፣ በጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ የጸጥታ ኃይሎች፣ እንዲሁም በራሱ በዋግ ኅምራ ሕዝብ ትግል፣ ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በመውጣቱ፣ በዚሁ አጋጣሚ መንግሥት እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት ይወዳል፡፡
ነጻነታችንን የምናስከብረው በተባበረው ክንዳችን ነው!
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
- ተጨማሪ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሊደረግ ነውየኢትዮጵያን…
- ከአርሰናልና ከሲቲ የተሻለ ዕድል ለማን? አሃዛዊ መረጃዎች ወዴት ያደላሉከሚታወቅበት…
- የበዓሉ ግርማ ኦሮማይ – ዛሬ ለምን?ትህነግ…
- የበታችነትና የበላይነት ስቃይ “እኩል የኢትዮጵያ ስጋት ናቸው”መባሉ ጫጫታ አስነሳ?ዛሬ…
- ሩሲያ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቿን ቤላሩስ ውስጥ ልታጠምድ ነውሩሲያ…
- ኦሮሚያ በአራት ወር መቶ ሺህ ዘመናዊ የገጠር መኖሪያ ቤቶች ሊገነባ ነውበቀጣዮቹ…
- በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅከለውጥ…
- በእውሸት “ታሰሩ፣ታፈኑ” በሚል ስማቸው በሚዲያዎች የተሰራጨው ስድስት ወጣቶች የፍቅር ግንኙነት መስርተው ተገኙበአንድ…
- ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ዛሬ ከጉራጌ ማህበረሰብ በቤተመንግስት በነበረው ውይይት ከተናግሩት“ደሜ…
- ህወሓት ከሽብርተኛነት ተሰረዘየህዝብ…
- በረከት ገበሬዋ የመደመር ትውልድ መጽሀፍን በ50 ሺህ ዩሮ ገዝታለችበረከት…
- የአማራ ብልጽግና ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በዝግ እየመከሩ ነውየብልጽግና…