የኢንደስትሪ መንደሩ በተለይ ለኢንደስትሪ እንቅስቃሴ በእጅጉ አስፈላጊ የሆኑ የግብርና ምርቶች ማቀነባበርያ ፤የእንጨትና ብረታብረት ስራዎች፤የጨርቃጨርቅና አልባሳት፤የኮንስትራክሽን ግብአቶች ፤የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ፤ የኬሚካልና ፕላስቲክ ውጤቶች ኤሌክትሮኒክስና የመድሃኒት ፋብሪካም እንደሚይዝ

– በግንባታው 21 የተለያየ ወለል ያላቸው ሼዶች፤400 የግብዓት አቅራቢዎችና ምርት መሸጫ ሱቆችም ይኖሩታል፡፡

በዛሬው እለት 7.7 ቢሊዮን ብር በሆነ ወጪ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የአነስተኛና የመካከለኛ ማምረቻ የኢንዱስትሪ ልማት የሚያቀላጥፍ የኢንደስትሪ ፓርክ ግንባታ ለማካሄድ ኤም ሲጂ ቲ ኤን ቲ ኮንስትራክሽን ከተባሉ ተቋራጮች ጋር የስምምነት ፊርማ ተካሄደ፡፡

ግንባታው ከ18 እስከ 20 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥርም ተገልጧል፡፡

የኢንደስትሪ መንደሩ በተለይ ለኢንደስትሪ እንቅስቃሴ በእጅጉ አስፈላጊ የሆኑ የግብርና ምርቶች ማቀነባበርያ ፤የእንጨትና ብረታብረት ስራዎች፤የጨርቃጨርቅና አልባሳት፤የኮንስትራክሽን ግብአቶች ፤የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ፤ የኬሚካልና ፕላስቲክ ውጤቶች ኤሌክትሮኒክስና የመድሃኒት ፋብሪካም ጭምር የሚይዝ ይሆናል፡፡

የስምምነት ፊርማውን ያከናወኑት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት ከተማችንን ለማሳደግ የከተማው አስተዳደር ለኢንደስትሪ እስከ 93 ሄክታር መሬት ያህል ማዘጋጀቱ ምን ያህል ለዘርፉ ትኩረት እንደሰጠው አመላካች ነው ብለዋል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ከተማው በራሱ በጀትና በራሱ እቅድ የሚያከናውነው ፕሮጀክት መሆኑን የገለፁት ከንቲባ አዳነች በከተማችን የኢኮኖሚ ሽግግር ለማረጋገጥ፤ የውጪ ምንዛሬን ለማስቀረት ፤ስራ እድልን ለመፍጠር ፤ተኪ ምርቶችን ለማምረት ፤አይነተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በሁለት አመት እንዲጠናቀቅ የውለታ ጊዜ የተያዘለት መሆኑን የገለፁት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ይህ ማለት ግን የግድ ሁለት አመት ላይወስድ ይችላል ያሉ ሲሆን ስንፍናንና ታካችነትን እያስወገድን ፤በሽፍትም ጭምር እየሰራን ለውጥ ለማምጣት እየሰራን ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በፕሮጀክቱ የበለጠ አቅማችንን እያሳደግን ከዚህ በፊት ለውጪ ኮንትራክተሮች የሚሰጠውን የሜጋ ፕሮጀክቶች ስራ ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች በመስጠት የራሳችንን አቅም የምናሳድግበት ነው ብለዋል፡፡

ኢንጂነር ደቦ ቱንካ የሜጋ ፕሮጀክቶች ሃላፊ በበኩላቸው ይህ ፕሮጀክት በአይነቱ የመጀመርያ መሆኑን ገልፀው ፤ይህ ፕሮጀክት በተለይም ሜጋ ፕሮጀክት በራሱ ባወጣው ጨረታ በውድድር አልፎ ለዚህ ሂደት የደረሰ መጀመርያው ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡

ግንባታው በአጠቃላይ በ93 ሄክታር መሬት ላይ የሚካሄድ ሲሆን በአሁኑ በአሁኑ ስምምነት ግንባታው የሚጀምረው የሎት አንድና የሎት ሶስት ሲሆን ሌሎቹም በሂደት ሚቀጥሉ ይሆናሉ፡፡

በግንባታው 21 የተለያየ ወለል ያላቸው ሼዶች፤ 400 የግብዓት አቅራቢዎችና ምርት መሸጫ ሱቆችም ይኖሩታል፡፡
በስራው የተሳተፉት ኮንትራክተር ኢንጂነር ጃገማ ቀነኒ በበኩላቸው ፤ፕሮጀክቱ ሃገራዊ ሃላፊነታችን በመሆኑ እንደ አንድ የቢዝነስ ሰው ሳይሆን እንደ ራሳችን ሃብት በታሰበው ጊዜ አጠናቀን የምናስረክብ ይሆናል ብለዋል፡፡

Addis Ababa city administration

በዛሬው እለት ለአዲስ አበባችን የመጀመርያና አዲስ ብስራት የሆነ የአነስተኛና መካከለኛ የኢንደስትሪ ፓርክ፣በ7.7 ቢሊዮን ብር በ93 ሄክታር መሬት ላይ ለመገንባት ስምምነት ፈፅመናል፡፡

ኢትዮጵያ ወደ ምንመኝላት ብልፅግና እንድትተም ኢንደስትሪን ማስፋፋት፣ የስራ ባህልን መቀየር ፣ አምራችን ማበራከት፣ ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግርን ማረጋገጥ የግድ ይለናል፡፡
በዛሬው እለት የፈረምነው የኢንደስትሪ ፓርክ ግንባታ ስምምነት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንደስትሪዎች መስፋፋት የሚያግዝ ፣ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጪ ምንዛሬን የሚያስቀርና በቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸው የላቁ ፣ የስራ ባህላቸው የጎለበቱ ፣አምራች ዜጎችን የሚያፈራ እንደሚሆን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
ፓርኩ ከ18-20 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል የሚፈጥር ከመሆኑም ባሻገር ፤ ከአግሮ ፕሮሰሲንግ ጀምሮ የጨርቃ ጨርቅ አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የኮንስታራክሽን፣ የኬሚካል እና ፕላስቲክ፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ የመድሀኒትና የመድሃኒት ማምረቻ እቃዎች ግብዓቶች የመሳሰሉት ዘርፈ ብዙ የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች የሚመረቱበት በመሆኑ በአጠቃላይ ለከተማችን ሁለንተናዊ ለውጥ አይነተኛ ሚና የሚጫወት ይሆናል።

ግንባታው 21 የተለያየ ወለል ያላቸው የማኑፋክቸሪንግ ሼዶችና 400 የግብዓት አቅራቢዎችና ምርት መሸጫ ሱቆች ይኖሩታል፡፡
ስለኢትዮጵያችን እንትጋ፤ ታካችነትና ስንፍናን እናስወግድ ፣ የስራ ባህላችን ይቀየር ፣ በየእለቱ ዛሬ ለኢትዮጵያ ምን ሰራሁላት እንበል!!

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!

Leave a Reply