ሮይተርስ በአንድ ቀን ልዩነት ሁለት ዜና “ምንጮቼ” ነገሩኝ ሲል አስነብቧል። ሁለቱም ዜናዎች ለምስራቅ አፍሪቃ የተሾሙትን ጄፊር ፌልትስማንን አስመልክቶ መሆኑ የበርካቶችን ቀልብ የሳበ ሲሆን የአሜሪካ ባልስልጣናት ዝምታን ሲመርጡ፣ ኢትዮጵያ ” እኔን አይመለከትም እዛው ጨርሱ ” አይነት መልስ ሰጥታለች ሰንዝራለች።

ሮይተርስ ሹክ አሉኝ ሲል የአሜሪካንን ባለስልጣን ተንተርሶ ፊልትሰማን ሃሙስ አዲስ አበባ ገብተው ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚመክሩ አመልክቶ ነበር። ይህንኑ የሮይተርስ የውስጥ አዋቂ ዜና በመቀባበል ስለ ሰውየው የአዲስ አበባ ጉዞ ጉንጫቸውን ያፍታቱ፣ መላቸውን የወረወሩና የተነተኑ ” ተንታኞች” ምራቃቸው ሳይደርቅ ሮይተርስ ፌልትስማን መነሳታቸውን መስማቱን አመልክቷል።

በኢትዮጵያ የሰሜኑ ክፍል ያለው ጦርነት እንዲያቆም ጫና እንደሚፈጥሩ፣ ለዚሁ ሲሉ ወደ ኢትዮጵያ ያመራሉ የተባሉት ፌልትስ ማን መነሳታቸው ብቻ ሳይሆን ማን እንደሚተካቸውም ጭምር ነው ይፋ የሆነው። እንደዜና በቱርክ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ዴቪድ ሳተርፊልድ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ተደርገው እንደሚሾሙ ተመልክቷል። ይህንኑ ዜና የአሜሪካ መንግስት ” ዝምታ ይሻላል” በሚል ምላሽ ከመስጠት መቆጠቡን፣ ስለጉዳይ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ “የአሜሪካ የውስጥ ጉዳይ ነው” በሚል ምላሽ መስጠታቸው በዜናው ተጠቅሷል።

ፌልትስማን ገና ሲሾሙ በሰጡት ቃለ ምልልስ የኢትዮጵያን መንግስት በማራከሳቸው ” ክብረ ነክ” ሲል መንግስት ዘልፏቸው እንደነበር ይታወሳል። ባልተለመደ መልኩ ለአሜሪካ ተመጣጣኝ ምላሽ የሚሰጠው መንግስት “ክብረ ነክ” ያላቸው ፌልትስ ማን መካለኛ ምስራቅንና የኢትዮጵያን ጎረቤት አገሮች በተደጋጋሚ እያዳረሱ ኢትዮጵያ ሲመጡ በዚሁ ባልተገባ ዝለፋቸውና የተዛባ አቋም ስለሚያራምዱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሊያገኞቸውና ፈቅደኛ እንዳልነበሩና በመጨረሻው ጉዟቸው ብቻ እንዳነጋገሯቸው መዘገቡ ይታወሳል።

የፌልትማን ስንበት አዲስ አበባ ደርሰው ሲመለሱ ይሁን አስቀድሞ በገሃድ ከአሜሪካ መንግስት የተሰጠ መግለጫ የለም። ጄፍሪ ፌልትማን ሐሙስ አዲስ አበባ እንደሚገቡ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ለጋዜጠኞች ማስታወቃቸው ይታወሳል። ይህንኑ የኔድ ፔንስን ሃሳብ ተንተርሶ ቪኦኤ ፌልትማን ልክ ለሃዋርያዊ ስራ አዲስ አበባ እንደሚመጡ አድርጎ ትናንት ቪኦኤ አማርኛው ክፍለ ጊዜ ዘግቧል።

Leave a Reply