” 19 ሰዎች ሕክምና አጥተው ሕይወታቸው አልፏል ” – ዶ/ር ብርሃኑ ዓለሙ

የአምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሽብርተኛው ህወሓት ባደረሰው ውድመት ምክንያት 19 ሰዎች ህክምና በማጣት ህይወታቸው ማለፉን ሪፖርት አደረገ። የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ዓለሙ ለአሚኮ በሰጡት ቃል ሆስፒታሉ ከተመሰረተ ጀምሮ ያከማቻቸው የሕክምና መሳሪያዎች፣ መድኃኒቶች እና ሌሎች ግብዓቶች ወድመዋል።

በሆስፒታሉ ክትትል ላይ የነበሩ 19 ሰዎች ሕክምና አጥተው ሕይወታቸው አልፏል። በህክምና እጦት ህይወታቸው ያለፈው 7 ነፍሰጡር፣ 5 ሕጻናት እና 7 ተመላላሽ ታካሚዎች መሆናቸውን ዶ/ር ብርሃኑ አሳውቀዋል።

ህወሓት በሆስፒታሉ ንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት መሆኑንን ዶ/ር ብርሃኑ ጨምረው ተናግረዋል። አምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ150,000 በላይ ሕዝብ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሆስፒታል መሆኑን ከአሚኮ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በመዘዞ ንጹሃንን ከመግደል በሻገር፣ ዝርፊያና የንብረት ማውደም ተግባር ፈጽሟል።

Leave a Reply