በአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ታቅዶ ነበር

ለአማራ ክልል ሙሉ የጨለማ፣ ለመላው ፍትህ ወዳድ ዜጋ ሕመም የሆነው የሰኔ 15ቀን 2011 ዓ.ም ድራማ ጠባሳው ክፉ ነው። ይህ ጠባሳ ምርጥ የሚባሉ የአማራ ክልል መሪዎች፣ የኢትዮጵያን ልጆች የተገደሉበት ነው። በዚህ የዕብዶች ሂሳብ የደረሰው ጉዳት ዛሬ ድረስ ቁስሉ ያልሻረ ቢሆንም በድጋሚ ተመሳሳይ ድርጊት ለመፈጸም ዝግጅቱ ተጠናቆ እንደነበር ለዝግጅት ክፍላችን መረጃ ደርሷል።

በባሕር ዳር ከተማ በክልሉ መስተዳደር ጽህፈት ቤት ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ፕሬዝዳንቱን ዶክተር አምባቸው መኮንን፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ምግባር ከበደ እና የርዕሰ መስተዳደሩ አማካሪ አቶ እዘዝ ዋሴ መገደላቸው ይታወሳል። በዚህ “መፍንቅለ መንግስት” በተባለ ሙከራ የወቅቱ የክልሉ ልዩ ሃይል አዛዥ ብ/ጄነራል አሳምነው ሃይሉን እየመሩ ወደ አስተዳደሩ ቢሮ መግባታቸው፣ ሁሉንም ጉዳይ እሳቸው ይመሩት እንደነበር ባልደረባቸውና ምክትላቸው ጀነራል ተፈራ በወቅቱ ምስክርነት መስጠታቸው ይታወሳል።

መረጃውን ያደረሱን እንዳሉት በአማራ ክልል በተመሳሳይ መፈንቅለ መንግስት ለማካሄድ በልዩ ሃይሉ ውስጥ ሰርጎ ለመግባትና ሃይሉን ለመቆጣጠር ሲሰራ እንደነበር ስለላው በደንብ ያውቅ ነበር። በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ሰማ ጥሩነህ ባይዘርዝሩትም የክልሉን ልዩ ሃይል ለማስከዳት፣ ከነትጥቁ እንዲኮበልል፣ መከላከያ ውስጥ ያሉ አባላትን ለማሸፈት ሲሰራ እንደነበር ሰሞኑን በአማራ ክልል ማስ ሚዲያ በግልጽ አስታውቀዋል።

“አደገኛ መዛባሪዎችና ሃብት ያካበቱ” ድልድይ ሆነው በሚሳተፉበት የአማራ ክልልን መንግስት በሃይል የመገልበጥ ዝግጅት ውስጥ እነማን፣ እንዴትና፣ ከነማን ጋር ይሰሩና ይዘጋጁ እንደነበር ስለላው ያውቅ እንደነበር ያመለከቱት የመረጃው ምንጮች፣ የሕግ ማስከበሩ ስራ ሲጀመር ቀድሞ የመከነ ተግባር መኖሩን አስታውቀዋል።

በእቅዱ መሰረት በባህር ዳር በለሊት የሚፈጸም የመፈንቅለ መንግስት እንዲካሄድ ታስቧል። ይሁን እንጂ ጊዜ አልመረጠም። ለዚህ ደግሞ ዋናው ምክንያት በባህር ዳር አንዳች ሙከራ ቢደረግ የመከላከያ ሃይል በቅጽበት እርምጃ ስለሚወስድና፣ መከላከያ ዙሪያ ክፈተት አለመገኘቱ የፈጠረው ስጋት ነው።

መፈንቅለ መንግስት አሳቢዎቹ የሰለጠኑ ታጣቂዎች ያላቸው ሲሆኑ በገንዘብና በሚዲያ ድጋፍ የሚደረግላቸው ናቸው። በውጭ አገር ባሉና አገር ቤት በተደራጁ ሚዲያዎች በተዘዋዋሪ ቅስቀሳ የሚሰራላቸው እንደሆኑ ለማንም የተሰወር እንዳልሆነ የመረጃው ባለቤቶች አመልክተዋል።

“አማራ ክልል ልክ እንደ ትግራይ የራሱ የሆነ ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ የሆነ መከላከያ ማቋቋም አለበት” በሚል በ360 አዘጋጆች በተደጋጋሚ ቅስቀሳ ሲደረግ እንደነበር በማስታወስ፣ ይህንንም ተከትሎ ጎጃም አካባቢ በፋኖ ስም ኢመደበኛ የሆነ ሃይል ማደራጀት ከተጀመረ ዓመት ማለፉን የሚገልጹት ክፍሎች ” አሁን ሁሉም ነገር ከሽፏል” ሲሉ አብዛኞቹ መያዛቸውን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ብዛታቸውንና የአቅማቸውን መጠን አላብራሩም።

የተያዙ ያሉ ቢሆኑም ጭካ ገብተው ራሳቸውን የደበቁ መኖራቸውናና እነሱን ለመያዝ ዘመቻው እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል። ክልሉም እንደሚገፋበት ይፋ አድርጓል። የህግ ማስከበሩ ዘመቻ በስፋት እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው ትህነግ “ምርኮኛ እለቃለሁ” ሲል የተናገረው። ወደ አማራ ክልል አስጠግቶ እንደሚለቃቸው ማስታውቁን ተከትሎ ቀይ መስቀል ጉዳዩን እንደማያውቀው፣ መንግስትም የሰለተኑ ሰርጎ ገቦችን የማስገባት ዓላማ ያካተተ ተግባር እንደሆነ አስታውቋል። ሰርጎ ገብ ማስገባት የተፈለገበት ዋና ምክንያት ከህግ ማስከበሩ ጋር ስለመያያዙ የተባለ ነገር የለም።

በአማራ ክልል መፍነቅለ መንግስት ለማካሄድ መታሰቡን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ተባባሪያችን ለክልሉ ባለስልጣናት ቅርብ የሆኑ ወገኖችን ጠይቆ ” ሃሳቡ አላቸው። ግን እንቅስቃሴያቸው ሁሉ ከቁጥጥር ውጭ አልነበረም” ሲሉ ትዝብታቸውን እንደገለጹለት አስፍሯል። ” እንደው ነገሩ አንዳንዴም የውርጋጥ አይነትም ነው” ያሉትም አሉ።

አሁን ያለው የመንግስትም ሆነ የክልሉ ሃይል በደንብ የደረጀ እንደሆነ ጠቅሰው “መፈንቅለ መንግስት አይታሰብም። እንኳን መፍንቅለ መንግስት ትህነግ እንኳን ጦርነት አይከፍትም” ሲሉ አስተያየታቸውን አክለዋል። ዳያስፖራ ውስጥ ያሉት ወገኖች መሬት ላይ ያለው ሃቅ እንዳልገባቸውም አመልክተዋል።

ከመቶ የወልቃይት ሕዝብ የት እንደገባ አይታውቀም”

አሸባሪው ሕወሓት በወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ላይ ላለፉት አርባ ዓመታት በፈፀመው ስልታዊና የተቀናጀ የዘር ማፅዳት ወንጀል ከእያንዳንዱ ቤተሰብ 29 ከመቶ ለህልፈት፣ 26 ነጥብ 5 ከመቶ ለስደት መብቃቱንና 19ነጥብ 5 ከመቶ ደግሞ የት እንደገባ እስካሁን እንደማይታወቅ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጥናት አመላክቷል። 12 የጅምላ መቃብር

አማራ ክልል ለሚንቀሳቀሰው ክፍል በዲያስፖራ በኩል ከፍተኛ ሃብት እየትሰበሰበ እንደሆነ ይታወቃል። ይህን ሃብት በተከታታይ ለመቀበል አገር ቤት እንቅስቃሴ መደረግ አለበት። በዚህም ሳቢያ ዘወትር የሁከት ዜና እንዲሰራጭ ይፈለጋል። በሚል የነገሩን አካሄድ በተደጋጋሚ የሚገልጹ ” ዲያስፖራውን ደም ተፍቶ የሚየገኘውን ብር በብከት እያስረከበ አገሩ ላይ ቢንዚን ይረጫል።” ሲሉ ወቀሳቸውን ይሰነዝራሉ።

በአማራ ክልል የተጀመረውን አመጽ ተከትሎ የትህነግ ደጋፊዎች በይፋ “እኔም የአማራ ትግል ይመለከተኛል” በሚል በማህበራዊ ገጾቻቸውና ሚዲያዎቻቸው እያስተጋቡ እንደሆነ ለማየት ተችሏል። የትህነግ አመራሮችም “አማራ ወገናችን” የሚል አሳብ ሲያራምዱ እየተሰማ ነው።

ትህነግ ከወራት በፊት አማራና አፋር ክልልን በወረረበት ወቅት በአማራ ክልል እናቶች፣ አረጋዊያን፣ ህጻናት ላይ ያደርሰው ዘግናኝ ተግባር ሰሞኑንንበመረጃ ተደግፎ በጎንደር ዩኒቨርስቲ አማካይነት ይፋ መሆኑ ይታወሳል። በወረራው ወቅት በጅምላ የተረሸኑ፣ የጥይት ማብረጃ የሆኑ፣ የተደፈሩ ሲትና ወንዶች፣ የት እንደደረሱ የማይታወቁ ሰዎች፣ የወደመና የተዘረፈ ንብረት በዝርዝር ነው ጥናቱ ያስረዳው። ይህን የፈጸሙና ያስፈጸሙ ሃይሎች በውጭ አገር ካሉ “አማራ ነን” ከሚሉ ወገኖች ጋር አንድ ላይ ሆነው “እኔም የማራው ትቃት ይመለከተኛል” እያሉ መሆኑንን ያስተዋሉ በነሱ ሳይሆን “አማራ ነን” በሚሉ ወገኖች ማዘናቸውንና ማፈራቸውን እየገለጹ ነው። ለነሱ ድጋፍ የሚሰጡትን ወገኖች ጤንነት እንደሚጠራጠሩም እየገለጹ ነው።

በአማራ ክልል ምን ታቅዶ እንደነበር የሚገባቸውና የሚያውቁ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው የህግ ማስከበሩን ስራ እየተቃወሙ ሲሆን፣ ሕዝብ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ የሰላም ያለህ፣ የህግ ያለህ በሚል ተቃውሞ ሲያሰማ ነበር።

Leave a Reply