ታግቻለሁ በማለት የፍቅር ጓደኛዋን 500 ሺህ ብር የጠየቀችው ተከሳሽ ተያዘች

ሳትታገት ታግቻለሁ ብላ የፍቅር ጓደኛዋን 500 ሺህ ብር የጠየቀችው ተከሳሽ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

ግለሰቧ የማታለል ወንጀሉን የፈፀመችው በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ አይ ሲ ቲ ፓርክ አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ተጠርጣሪዋ ለቦታ መያዣ ተብለው ከተሰሩ የጎጆ ዳስ ውስጥ ታግቻለሁ በማለት የፍቅር ጓደኛዋን 500 ሺህ ብር እሱ በማያውቀው ስልክ መክፈል አለብሽ ተብያለሁ በማለት መልዕክት ጽፋ እንደነበር ፖሊስ አረጋግጧል፡፡

የለሚኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መርማሪ ሳጅን እንግዳ በላይ ÷ የግል ተበዳይ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሰረት ተከሳሿ መያዟን ጠቅሰዋል፡፡

የላከችው መልዕክትም ሐሰት መሆኑን ነው አረጋግጠናል ብለዋል፡፡

ተከሳሿ የውሸት መልዕክቶችን አጋቾች እንደጻፉት አስመስላ ስትጽፍ  እንደነበር ያመላከቱት መርማሪው÷ ድርጊቱን የፈፀመችው የማይገባትን ጥቅም  ለማግኘት በማሰብ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ሕብረተሰቡ መሰልየወንጀል ተግባር ሰለባ ላለመሆን ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እና ምንም ጉዳይ ቢሆን ገንዘቡን ፈጥኖ ከመስጠት እንዲቆጠብ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ፋና ዜና

See also  በአሸባሪው የትህነግ ተጠርጣሪ አባላት ላይ በዚህ ሳምንት ክስ እንደሚመሠረት ተገለጸ።

Leave a Reply