የቀድሞ የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት
ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ በ18 አመት ጽኑ እስራት በ20 ሺህ ብር እንዲቀጡ ተወሰነ።

ሌሎችም ተከሳሾች በሌሉበት ከ18 አመት እስከ 7 አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ በየደረጃው ተወስኗል።

የቅጣት ውሳኔውን የፌደራል ከፍተኛ ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

በሰባዊ መብት ጥሰት ተከሰው በሌሉበት ጉዳያቸው ሲታይላቸው የቆዩት አቶ ጌታቸው አሰፋ በ18 አመት ጽኑ እስራት እና በ20 ሺህ ብር የተቀጡ ሲሆን አቶ አጽብሀ ግደይ ደግሞ በ16 አመት ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተወስኗል።

11 ኛ ተከሳሽ አሰፋ በላይ በ7 አመት ጽኑ እስራትና በ7 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ የተወሰነ ሲሆን 12ኛ ተከሳሽ አቶ ሺሻይ ሀይለ ደግሞ በ11አመት ጽኑ እስራትና በ14 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተወስኗል።

ተከሳሾቹ ጥፋተኛ በተባሉበት የወንጀል ህግ አንቀጽ 423 እና 556 መሰረት ነው።

ቀሪዎቹ የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ እንደማይፈልጉ ገልጸው ፍርድ እንዲሰጣቸው ጠይቀው የነበሩት ተከሳሾች ማለትም 5ኛ ተከሳሽ ደርበው ደንበላሽ 3 አመት ከ6 ወር እስራትና በ1ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ የተወሰነ ሲሆን

14 ኛ ተከሳሽ ዩሀንስ ውበት ደግሞ በ3 አመት ከ3ወር እና በ500 ብር የገንዘብ መቀጮ ተጥሎበታል።

23ኛ ተከሳሽ አሸናፊ ተስፋሁን በተመለከተ ደግሞ 5 አመት ከ8 እና የአንድ ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኗል።

25 ኛ ተከሳሽ ሀዱሽ ካሳ በ9 ወር ቀላል እስራትና በ500 ብር የገንዘብ መቀጮ ተወስኗል።

26 ተከሳሽ ማርክስ ፀሀዬ በተመለከተ 3 አመት ከ3 ወር እስራትና አንድ ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተወስኗል።

ተከሳሾቹ እያንዳንዳቸው ያቀረቡት የቀደመ የወንጀል ሪከርድ እንደሌለባቸው :የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸው:ሀገራዊና ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን መወጣታቸውን: እና የጤና ዕክል እንዳለባቸው ያቀረቡት የቅጣት ማቅለያ አስተያየት በወ/ህ /አ86 መሰረት ተይዞላቸዋል።

ከ23 ኛ ተከሳሽ ውጪ ያሉት ተከሳሾች ከጥቅምት ወር 2011 ጀምሮ በስር ላይ በማሳለፋቸው የስር ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው የገንዘብ መቀጮውን በመክፈል ከዛሬ ጀምሮ ከስር እንዲፈቱ ታዟል።

የፌደራል ፖሊስ ያልተያዙ አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ አራት ተከሳሾችን አፈላልጎ የተጣለባቸውን እስራት እንዲያስፈጽም ታዟል።

ሌሎች 12 ተከሳሾች የመከላከያ ማስረጃ አቅርበው በሂደት ላይ ናቸው።

የፍ/ቤቱ ውሳኔ መሰማት ተከትሎ በተለይ በማህበራዊ ሚድያ ሰፊ የመነጋገርያ አጀንዳ ሆኗል።

(ታሪክ አዱኛ እና ድሬቲዩብ)

Leave a Reply