ትህነግ “ክልል ነኝ” ብሎ ስሙን አስተካከለ

ራሱን የትግራይ መንግስት አያለ ሲጠራ የነበረው ትህነግ ስሙን አስተካክሎ ደብዳቤ አሰራጨ። ድርጅቱ ይህን ያደረገው አማራጭ በተባለው የሰላም ንግ ግር ላይ የሚገኙ አባላቱን ዘርዝሮ ለአፍሪካ ህብረት በጽስፈው ደብዳቤ ነው።
የትግራይ ክልላዊ መንግስት ሲል ቀድሞ በሞታወቅበት ስሙ ራሱን የገለጸው ት ህነግ ይህን ህያደረገው መንግስት የስም ማስተካከያ አንዲደረግ ለሚመለክታቸው ሁሉ ማሳሰቡን ተከትሎ ነው። አሜሪካን ጨምሮ አማጺ አያሉ የሚጠሩት ት ህነግ የወሰደው ማስተካከያ ለንግ ግር ከመቀመጡ በፊት ስያሜውን አንዲያስተካክል ተደርጎ መሆኑ ታውቁዋል በዚሁ ደብዳቤ ለንግግሩ የሚቀርቡትን አባላት በስም ተዘርዝረዋል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ በሰላም ንግግሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ዛሬ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቷል ብሏል።

ፕሮፌሰር ክንድያ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በሚደረገው ውይይት የትግራይ ኃይሎች የሚያነሷቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች ግጭት በአስቸኳይ ማስቆም፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ እና የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ማስወጣት የሚሉት መሆናቸውን አስታውቀዋል። ሲል ቢቢሲ ንግግሩን “ድርድር” ባለበት ዜው አመልክቱዋል።

መንግስት ማለዳ ላይ ባወጣው መግለጫ “አጋጣሚውንም የሰላም ንግግሩን ግጭቱን በሰላም ለመፍታት የሚቻልበት ዕድል አድርጎ ይመለከተዋል። በመከላከያ ኃይላችን መሥዋዕትነት እየተስተካከለ የመጣውን ሁኔታ የበለጠ ለማጠናከር ምቹ አጋጣሚ የሚፈጥሮ አድርጎ ይወስደዋል።”

ይህ የመንግስት መግለጫ ክንድያ አንዳሉት ምንም በር የሌለ መሆኑን ነው። መንግት በመስዋዕትነት የተገኘ ሲል የት ህነግን መሸነፍ ገሃድ ኣድርጉዋል። ቢቢሲ የዘገበው ምን አልባትም ለደጋፊዎች መጽናኛ አንዲሆን ታስቦ ካልሆነ በስተቀር ለውጥ ሊያመጣ የሚያስችል ምድራዊ ምክኛቶች የሉም።
ከተለያዩ ምንጮች አንደሚሰማው የጥነግ ወኪሎች ወደ ትግራይ ኣይመለሱም። ቀሪ ህይወታቸውን ለጊዜው በስደት ያደርጉታል አየተባለ ነው። መንግስት ንግግሩ በሚጀመርበት ቅጽበት ስም ሳይዘረዝር የትግራይን ቁልፍ ከተሞች በመቆጣጠር ማስተዳደርና መምራት መጀመሩን ማመልከቱም የዚሁ ምልክት ተደርጎ ተወስዷል

“ባለፉት ቀናት የፌደራሉ መንግሥት ጥምር ኃይሎች በርካታ ከተማዎችን እና የትግራይ አካባቢዎችን ከትግራይ ኃይሎች አስለቅቋል የሚሉ ዘገባዎች እየወጡ ነው” ሲል ቢቢሲ የሰማውን የተረጋገጠ ዜና አሉባልታ አስመስሎ ዘግቧል። የት ህነግን ይቲውተር ሃሜት ሲያስተጋባና ሲያትም የኖረርው ቢቢሲ መንግስት አረጋግጦ የነገረውንና ይፋ ያደረገውን ዜና በዚህ መልክ መዘገቡ የሚጠበቅ አንደሆነ ተገልጿል። መንግስት ለቢቢሲ ያሳየው ትዕግስት ከልክ በላይ አንደሆነ በተደጋጋሚ የሚገለጽ ጉዳይ ነው።

See also  አዲስ ጅሃዳዊ ቡድን የሱዳን ሰላዮችን መግደሉን አስታውቋል

Leave a Reply