(በዶክተር መሐመድ በሽር፣ በጅማ ዩኒቨርስቲ የህፃናት ሐኪም የተፃፈ)

አንድ አባት ልጅ ታሞበት አገኘውት፣ እባካችሁ እርዱኝ እያለ ይማፀናል። አይዞህ ብለን ካርድ አውጥተን ልጅን ምርመራ ጀመርን።

በምርመራውም ልጅ በደረት ውስጥ በቋጠረ ፈሳሽ መተንፈስ አቅጦት እያጣጣረ ነው። በተጨማሪም የሚጥል በሽታ እንዳለበት መድሃኒት እየወሰደ እንደሆን እንዲሁም የምግብ እጥረት እና የኦቲዝም ህመም ተጠቂ እንደሆነ ተረዳን።

የልጁን ህይወት ለማትረፍ የኢመርጀንሲ እክምና ያስፊለገዉ ነበር። የቀዶ ሃኪሞች እንዲተባበሩ ካደረኩኝ በኃሏ በደረት ውስጥ ቲቦ ገብቶለት የቋጠረው ፊሳሽ ወጣለት የልጅም አተነፋፍስ ማገገም ጀመር እኔም ደስ አልኝ። ቀጥሎም የክፍሉ ሃኪሞች መጥተው 11 አይነት መድሃኒቶች አዘው ሄዱ።

አባት እያለቀሰ ደውሎ ከአቅሙ በላይ እንደሆነ ልጁ ከሞተም ይሙት ብሎ ወደ ቤት ሊገባ እንደሆነ ሲነግረኝ ተረጋጋ ብዬ መድሃኒቶች እግዛለዉ አልኩት።

ወደ ፋርማሲ ሄጄ ዋጋ ብጠይቅ ዋጋው የሚቀመስ አይደለም። የእንዱ ደም ማቅጠኛ ዋጋ 750 ብር ነው። እንግዲህ ከገባሁበት አልኩና 6,000 አዉጥቼ ገዛሁኝ። ለአባት ስሰጠው በምድር ፈተና አትፈተን አለኝ።

ቀጥሎም የሶስት ልጅ አባት እንደሆነ ሶስቱም የአይምሮ ታማሚ የኦቲዝም ተጠቂ እንድሆኑ በልጆቹ ምክንያት ስራ እንደተባረር ነገረኝ። በልጆቹ ውስብስብ ችግር እናት እና እባት የአይምሮ ጭንቀት ተጠቂ እንድሆኑ ነገረኝ እንባዬ መጣ። የአይምሮ መድሃኒት ተጠቃሚ ናችው።

ልጆቹ በጣም ስልሚጮሁ ማንም ቤት አክራይ እንደማይፊልግ ነገረኝ። በነዚ ልጆች ምክንያት ሰርግ ለቅሶ ሳይሆን የገዛ ወንድሞች ጋር እንደማይሄዱ ነገረኝ። እነሱንም ማቆያ ተቋም እንደሌለ ነገረኝ።

አዲስ አበባ የኦቲዝም ማህከል ሄዶ እንደነበርም ይሁንና እንደዚህ እራሳቻውን የማይችሉ ልጆች እንደማይቀብሉ ነገረኝ። እጅግ ከባድ ነው።

ይህን የተገነዘቡ የህፃናት ህክምና ሬዚደንቶች ልብስም እቅማቸው የቻለውን 1,600 ብር ስብስብው አስረከቡት። ምስጋና ይገባቸዋል። አላህ ሁሉንም ይፊትናል እኛንም ነገ ሊፊትነን ይችላል። አይተናል ሰምተናል እንድረስላቸው። አላህ በሰጠን ፀጋ ሁሌም ማመስገን አለበን።

[ከልጆቹ አባት የተላከ አጭር መልዕክት]

ስሜ ደርቤ በየነ በዳኔ የትውልድ ዘመን 1955 ዓ/ም የትውልድ ቦታ በጅማ ዞን አጋሮ ከተማ ነው። የትምህርት ዝግጅት የመጀመሪያ ዲግሪ በግብርና ምርቶች ገበያ ትስስር ነው። ባለትዳርና የአራት ወንዶች ልጆችና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነኝ።

ከተወለዱት አምስት ልጆቼ መካከል ሶስቱ በአእምሮ ህመም እየተሰቃዩብኝ ከጅማ ሆስፒታል በሪፈር ከ2006 ዓ/ም ጀምሮ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በመመላለስ ያለኝን ንብረት ሳይቀር አሟጥጬ በመጨረስ በቅርብ የልጆቼን ሕክምናና ት/ት በአዲስ አበባ ከነቤተሰቦቼ በመግባት ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጥቁር እንበሳ ሆ/ል ቦርድ በቀን 17/10/2013 ዓ/ም በቁጥር Ref:PD/MF/408/20 ወስኗል።

እኔም ይህንን ውሳኔ ለመተግበር አቅም የሌለኝ መሆኔን ተረድታችሁልኝ የልጆቼን ጤናና ት/ት ማስተካከል ይቻላል ብለው ቦርዱ ስላመነበት የችግሬን ስፋትና ጥልቀት የተረዳችሁልኝ ወገኖቼ

በኢት/ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
1000018421813

በስልክ ቁጥር 0941880187/0917062442

በምክር ፥ በፀሎት ፥ በገንዘብ እርዳታችሁ እንዳይለየኝ በፈጣሪ ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ።

[በቤተሰብ ፍቃድ የተወሰደ]

  • እኔም ከደቂቃዎች በፊት አቶ ደርቤ በየነን በስልክ አዋርቼያቸው አሳዛኝ ታሪካቸውን ካሉበት የጅማ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ሆነው አጋርተውኛል። የአቅማችንን ድጋፍ በመስጠት እንደግፋቸው፣ እኔም የአቅሜን በማድረግ ተካፍያለሁ።

Story via Hakim Facebook page

Leave a Reply