በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 90 ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ከእነሙሉ ትጥቃቸው ተመለሱ፤ አቀባበልም ተደጎርላቸዋል።
በጦርነትና ግጭት ከመጠፋፋት ውጭ ምንም አይነት መፍትሄ አለመኖሩን በመረዳት መንግስት ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል 90 የሚሆኑት ከእነሙሉ ትጥቃቸው የተመለሱ ሲሆን የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን በመያዝ ነው።
በዞኑ ውስጥ በዳንጉርና ጉባ ወረዳዎች አዋሳኝ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ሰላም ሲመለሱ የግልገል በለስ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎችና ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ቢኒያም መንገሻ እንደገለጹት መንግስት የዜጎችን ደህንነት ከማስጠበቅ ባለፈ በቀጠናው ዘላቂ ሰላምን በማስፈን ወደ ልማት ለመግባት ያቀረበውን ሰላም በመቀበል ለተመለሱ አካላት ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲገቡ በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል።

የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ለሜሳ ዋውያ በበኩላቸው የሰላምን አማራጭ በመጠቀም ወደ ሰላም የተመለሱ ወገኖችን በማመስገን እነዚህ አካላት ወደ ኑሯቸው እንዲመለሱና ወደ ልማት ለማስገባት ይሰራል ብለዋል።
እነዚህን አካላት ወደ ሰላም ለመመስ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት በተጨማሪ የሀገር ሽማግሌዎች ጉልህ ሚና ተጫውተዋል።
በቀጠናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እያካሄደ ባለው ህግ የማስከበር ተግባር ወደ ሰላም መመለሱ ይታወቃል ሲል የዞኑ ኮምንኬሽን ዘግቧል።