በኦሮሚያ ሃያ አንድ ሺህ የሚጠጉ ፕሮጀክቶች ተጠናቀቁ፤ አስር ሺህ የሚጠጉ በግንባታ ላይ ናቸው

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሰፈሩት መልዕክት በምስል አስደግፈው እንዳመለከቱት በክልሉ በዚህ ዓመት እየተሰሩ ካሉት 29,762 ፕሮጀክቶች ውስጥ 19,912 ፕሮጀክቶችን ተጠናቀው መመረቃቸውን ገልጸዋል። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ሲሆኑ ይህም መንግስት ለህብረተሰቡ ጥቅም ለሚውሉ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ መስጠቱን እንደሚያሳይ አመልክተዋል። ሙሉ መልዕክታቸውን ክስር ያንብቡ።

በክልላችን የተከናወኑት የልማት ፕሮጀክቶች የህዝባችንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የሚፈቱና የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።

ላለፉት ዓመታት የተገነቡት ልማታዊ ፕሮጀክቶች በጥራት እና በፍጥነት ከመሰራታቸው በተጨማሪ ከተያዘላቸው ጊዜ ቀድሞ መጨረስን ባህል እያደረግን የመጣን ሲሆን የባለሀብቶች፣ የግል ድርጅቶችና ሌሎች የባለድርሻ አካላት ሚና ሊጨምር እንደሚገባም ተረድተንበታል፡፡

በለውጡ መጀመሪያ ላይ “የማናጠናቅቀውን ስራ አንጀምርም” በሚል መርህ ቃል እንደገባነው የጀመርናቸውን ፕሮጀክቶች በማጠናቀቅ ሪቫን መቁረጥ ባህል አድርገናል፡፡ ላለፉት ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ ፕሮጀክቶችን ሰርተን ለህዝብ ጥቅም እንዳዋልነው በዚህ ዓመትም እየተሰሩ ካሉት 29,762 ፕሮጀክቶች ውስጥ 19,912 ፕሮጀክቶችን አጠናቅቀን አስመርቀናል። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ሲሆኑ ይህም መንግስት ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ያሳያል።

በሌላ በኩል ከእነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ 14,600 የሚሆኑት በዜግነት አገልግሎት(Tajaajila Lammummaa) የተከናወኑ ሲሆን፣ 1,200 ፕሮጀክቶች በግሉ ዘርፉ የተገነቡ መሆናቸው በመንግስት እና በግሉ ሴክተር መካከል በመተማመን እና በህዝብ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ግንኙነት፣ የህዝብን ጥቅም መሰረት ባደረገ መልኩ መተማመን መፈጠሩን የሚያረጋግጥልን ነው፡፡

በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች ውስጥ ያለው የለውጥ አመራራችን ባሳለፍናቸው ጥቂት ዓመታት ውስጥ ላጋጠሙን ውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶች ሳይንበረከክ፣ ሁሉንም አስቸጋሪ ሁኔታዎች ወደ እድል በመቀየር ድልድይ አድርጎ እየተሻገረ ፣ የህብረተሰባችንን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ፕሮጀክቶችን ሰርተን እንዳስመረቅን ሁሉ አሁንም ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣውን የልማትና የለውጥ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠትና የያዝነውን የብልጽግና እቅዳችን ለማሳካት ላለብን ድርብ ኃላፊነት እንድንዘጋጅ ከወዲሁ አደራ ማለት እፈልጋለሁ፡፡

194194

See also  የህልም ጏደኛ!!! የእግዚአብሔርን ተአምር ላካፍላችሁ::በትእግስት አንብቡት - መሰረት መብራቴ

Leave a Reply