ከአርባ ሚሊዮን ብር በላይ ለ217 ፍሬ አልባሳት፤ አመራሩ ሰራተኞቹና አቅራቢዎቹ በሌብነት ክስ ተመሰረተባቸው

217 ፍሬ አልባሳትን በ40 ሚሊየን 67 ሺህ 748 ብር የገዙት አመራር እና ሰራተኞች ላይ የሌብነት ክስ መመስረቱ ተሰማ። ዜናው መነጋገሪያ ሲሆን መረጃውን ይፋ ያደረገው የኤፍቢሲ ነው ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው . . .

የሙስና ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች፦

1ኛ. የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ሰለሞን ፍስሃ፣
2ኛ. የተቋሙ የመንግስት የግዢ ዳይሬክተር ግሩም ወልዴ፣
3ኛ. የኮሚሽኑ የለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ባለሙያ ደረጄ ተፈራ፣ 
4ኛ. የኮሚሽኑ የሎጀስቲክስ ምዝገባና ቁጥጥር ባለሙያ ወንድሜነህ ምስጋናው፣
5ኛ. የአደጋ ስጋት ትግበራ ቡድን መሪ እዮብ ታደሰ ካሳ ፣
6ኛ. በኮሚሽኑ የህክምና ባለሙያዋ ሲስተር  አልማዝ ጌቶ፣
7ኛ. የአደጋ መረጃ ሀርድ ዌርና ሶፍትዌር ባለሙያ መስፍን ለገሰ 
8ኛ. ነጋዴ የሆኑት ንጉስ አማን ይባላሉ።

የቀረበባቸው የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ከሆነ ፤ በሰኔ ወር  በ2014 ዓ.ም በጀት አመት ከአንደኛ እስከ ሰባተኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች የግዢ ጨረታ ሂደት ውስጥ ይሳተፋሉ።

ግለሰቦቹ በሂደቱ በስውር በመመሳጠር በወቅቱ በተደረገ የገበያ ዳሰሳ ጥናት የአልባሳቱ ዋጋ 46 ሺህ 923 መሆኑ የተረጋገጠ ተከሳሹቹ ግን ” ቡልዶዘር ” የተሰኘ የእሳት አደጋ መከላከያ ልብስን  ከፍተኛ በሆነ ዋጋ በፍሬ 184 ሺህ 644 ብር ከ8ኛ ተከሳሽ ተጫራች ድርጅት ግዢ እንዲፈጸም ያፀድቃሉ።

አጠቃላይ 217 ፍሬ አልባሳትን በ40 ሚሊየን 67 ሺህ 748 ብር በመግዛት በመንግስት ላይ በልዩነት 29 ሚሊየን 885 ሺህ 441 ብር ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግም በተከሳሾቹ ላይ የተሳትፎ ደረጃ ጠቅሶ የከባድ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።

ክስ የተመሰረተባቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ከተከሳሾቹ መካከል 1ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች ያልቀረቡ ሲሆን ቀሪ ስድስት ተከሳሾች ግን ክሱ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

ኤፍቢሲ ምንጭ

ይህንን ማስፈንጠሪያ ethio12news ተጭነው በቴሌግራም ገጻችን ይከተሉን

See also  ምዕራባውያን የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት የችግር አባባሽነት ዘመቻ ላይ ናቸው

Leave a Reply