የማዳበሪያ ያለህ በሚባልበት አማራ ክልል 400 ኩንታል ማዳበሪያ በህገወጥ መንገድ ሲሰራጭ ተያዘ

አቶ ዮሐንስ ቧያለው በክልላቸው ምክር ቤት ፊት ስለ ማዳበሪያ አቅርቦት ዕጥረት አምርረው በተናገሩና “የክልሉ ገብርና ቢሮ ሥራ መሥራት ያልቻለ ደመወዝ በነጻ የሚበላ ነው” ብለው ባፌዙበት ማግስት በአማራ ክልል 400 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ በሕገወጥ መልኩ ሲሰራጭ መያዙን ኢቢሲ ዘግቧል።

ዜናው በአማራ ክልል የማዳበሪያን ችግር የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ ሲወራ የሰነበተው ሤራ ምን እንደሆነ ማሳያ ሆኖ ተወስዷል። የዓለምን አተቃላይ የማዳበሪያ ዋጋ መናርና የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ያሳደረውን የገበያ እጥረት ባለማገናዘብ ከሚቀርበው ውንጀላ ጎን ለጎን 400 ኩንታል ማዳበሪያ መያዙ ” ያልተያዘውስ፣ በሚታወቀው መንገድ እንደ ነዳጅ ወደ ጎረቤት አገር በኮንትሮባንድ የተጋዘውስ” የሚል ጥያቄ አስነስቷል። የዜናው ሙሉ መረጃ ከዚህ በታች ቀርቧል።

400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ሥር ዋለ

መነሻውን ከጅቡቲ ወደብ አድርጎ መዳረሻውን ወረታ ከተማ ለማድረግ የተንቀሳቀሰው 400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ የጫነ ተሳቢ ተሽከርካሪ፤ ከታሰበው ቦታ ሳይደርስ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

ሕገ ወጥ ድርጊቱ የተፈጸመው በባህርዳር ከተማ ሰባታሚት ቀበሌ ሐምሌ 16/2015 ሲሆን፤ አሽከርካሪው በአሳቻ ሰዓት በመጠበቅ ከሌሊቱ 6:00 ላይ የአፈር ማዳበሪያውን በሕገ ወጥ መንገድ ለግለሰቦች ሲያከፋፍል በኅብረተሰቡ ጥቆማ መያዙን የሰባታሚት ቀበሌ ፖሊስ ኦፊሰር ኮንስታብል ዮሐንስ ጥላሁን ተናግረዋል።

አብዛኛው ማዳበሪያ ሳይራገፍ ከነተሽከርካሪው ቢያዝም፤ ከ140 ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለግለሰቦች በሕገ ወጥ መንገድ መሰራጨቱ የተገለጸ ሲሆን፤ ፖሊስ ባደረገው ቤተ ለቤት ፍተሻ ከተሽከርካሪው ተራግፎ በግለሰቦች ቤት የተከዘነ በርካታ የአፈር ማዳበሪያ መገኘቱም ተነግሯል፡፡

በዚህም 89 ኩንታል ማዳበሪያ በአንድ ግለሰብ ቤት የተገኘ ሲሆን፤ 24 ኩንታል ማዳበሪያ ደግሞ በአንድ ግለሰብ ቤት በአልጋ ሥር እና በኩሽና ውስጥ መገኘቱ ተገልጿል።

አሽከርካሪው ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን ኮንስታብል ዮሐንስ ገልጸው፤ ኅብረተሰቡ እንደዚህ አይነት ሕገ ወጥ ተግባርን እንዲያወግዝ ጠይቀዋል።

በቴሌግራም ገጻችን ይከተሉን ethio12news

See also  ቻይና በኢትዮጵያ የቪዛ መጠየቂያ ማዕከል መክፈቷን ይፋ አደረገች

Leave a Reply