የአሜሪካ ውሳኔ እርስ በእርሱ የሚጣረስ የበቀለ ሴራ መሆኑ ተጠቆመ፤ ወልቃይት ለትግራይ እንዲሰጥ መንግስትን አንቃ መያዟ ተሰማ

ኢትዮጵያ የተዛባውን የዓለምን ሚዛን ያስተካክላል በተባለው የብሪክስ ህብረት ውስጥ መካከተቷን ተከትሎ “በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አልተሻሻለም” በሚል የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከሁለት ዓመታት በፊት ፈርመው ያወጡትን ፕሬዚደንታዊ ትዕዛዝ በአንድ ዓመት ማራዘማቸው እርስ በእርሱ የሚጋጭ የበቀል ሴራ ውሳኔ መሆኑ ተመለከተ። አሜሪካ ወልቃይትን ጨምሮ የአማራ መሬት ለትግራይ እንዲተላለፍ መንግስትን አንቃ መያዟ ተሰማ።

ትህነግ የአማራና አፋር ክልሎችን በሰው ማዕበል ወሮ በያዘበት ወቅት ወረራውን ለመቀልበስ የተካሂደውን የህልውና ጦርነት ተከትሎ አሜሪካ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽመዋል በተባሉ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ ያተኮረ ማዕቀብ በፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ አስተላልፋ እንደነበር ይታወሳል።

ትዕዛዝ ወራሪንና ተወራሪን በእኩል የሚፈርጅ እንደሆነ በወቅቱ ዛሬ በተቃውሞ የተሰለፉና ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚቀሰቅሱትን ጨምሮ በገሃድ በሰልፍና በተለያዩ ዘመቻዎች ሲቃወሙት እንደነበር ይታወሳል። ጆ ባይደን የፈረሙበት ይህ ትዕዛዝ በጅምላ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የኤርትራ መንግሥት፣ የአማራ ክልል አስተዳደርና የህወሓት አባላት ላይ ማዕቀብ መጣልን የሚደነግግ ነበር።

ከትህነግ ጋር በተደረገው የህልውና ጦርነት የመብት ጥሰት ፈጸሙ በሚባሉ ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ አግባብ ያላቸው የአሜሪካ ተቋማት ማዕቀብ እንዲጥሉ የሚፈቅደው ትዕዛዝ፣ ለአንድ ዓመት መራዘሙ ዛሬ ይፋ የሆነው ” በሰሜን ኢትዮጵያ አሁንም ያለው ሁኔታ የአገሪቱንና የመላው የአፍሪካ ቀንድ በአሜሪካ ብሔራዊ ጸጥታና የውጪ ፖሊሲ ላይ ያልተለመደ ልዩ አደጋ የደቀነ በመሆኑ ነው” የሚል ምክንያት እንደቀረበበት መግለጫውን ያሰራጨው የዋይት ሃውስ መረጃ ያስረዳል።

ዜናውን የተከታተሉ እርምጃው ብዙም ባያስገርምም እርስ በእርሱ የሚጣረስ መሆኑንን ገልጸዋል። ይህ ሊሆን የቻለው ደግሞ በሁለት ምክንያት ነው። ስማቸውን አቆይተው አስተያየት የሰጡ የከፍተኛ ተቋም መምህር ” ሁሉም ወገኖች ተገደው ወደ ሰላም ቢመጡ ደስተኛ ነኝ። ይህ ውሳኔ ግን ዓላማው ሌላ ነው። ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ የፈጠረው ብስጭትና ቁጭት የመጀመሪያው ሲሆን ሌላው ምክንያት ወልቃይትን ጨምሮ ወያኔ የሚጠይቀውን አካባቢ መንግስት በአስቸኳይ እንዲመልስ አሜሪካ በከፍተኛ ደረጃ ግፊት እየፈጠረች በመሆኑና መንግስት እነሱ በፈልጉት መልኩ መንግስት ለማስፈጸም ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለማስገደድ ነው” ይላሉ።

ሲያስረዱ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ክስ ጁላይ መጀመሪያ በይፋ ማንሳቷን ይጠቅሳሉ። አክለውም ዛሬ የተራዘመው ትዕዛዝ ቀደም ሲል የተነሳው የተጣለው ክስ የተነሳበትን ምክንያት ይገልጠዋል ይላሉ። ይህ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት፣ መበደርና የፋይናንስ ስምምነት ማድረግን የሚከለክልና የኢኮኖሚ ማነቆ የሚጥለው ክስና ማዕቀብ የተነሳው ኢትዮጵያ ወደ ብሪክስ እንዳትገባ ማበበያ እንደነበር ፍጹም እርገጠኛ መሆን እንደሚቻልም ያስረዳሉ።

See also  "ልጃችሁ ፋኖ ነው ተብለው ወላጆች ተገድለዋል"ቢቢሲ "የቆቦ ሕዝብ እውነቱን ያውቃል" አቶ ጌታቸው

በጄኖሳይድ ባለስልጣናትን ፈርጆ ለመክሰስ የሚያመቻች ትልቁ ማዕቀብ ተነስቶ የቪዛ ክልከላና የአጎዋን ተጠቃሚነት መገደብ በግል ሲያስቡት ” የፖለቲካ ዝሙት” የሚሉት አይነት የተለመደው የአሜሪካ ጸያፍ አካሄድ እንደሆነ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪ ” በግሌ የሰውን ልጅ መብት የጣሱና ህገወጥ ተግባር የፈጸሙ ሁሉ በህግ መጠየቅ እንዳለባቸው አምናለሁ። ነገር ግን በንዲህ ያለ የብስጭት ሴራና ጥቅምን ተንተርሶ የሚወሰን የፖለቲካ ዳንስ ሲሆን ያመኛል። ጉዳቱም እጥፍ ያደርገዋል” ሲሉ አቋማቸውንና የቅሬታቸውን መሰረት ያብራራሉ።

ከአጎዋ በመታገዳችን የኢንዱስትሪ መንደር ሲዘጋ፣ ሰራተኞች በዚሁ የተነሳ ሲበተኑ ወይም ምርት በገበያ እጦት ሲጣል እንዳላዩና እንዳልሰሙ አስታውቀዋል። ከአጎዋ መገለል ጉዳት ቢኖረውም ይህን ያህል የሚታይ ጫና እንዳለመጣ፣ ይልቁኑም እሱን የሚተካ ገበያ በቻይናና ኤሺያ አገሮች መገነቱን እንደሚያውቁ ገልጸዋል።

ከሁሉም በላይ የተወረረ ህዝብ ራሱን ለመከላከል ከመከላከያ ጎን መሰለፉ እየታወቀ፣ “የአማራ ታጣቂ” ስትል አሜሪካ በመግለጫዋ፣ በጀት መድባ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሲፈልግ ቅስቀሳ እንዲያመርቱ ባቋቋማቸው ሚዲያ፣ በዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ሚዲያዎች ሳይቀር ዘመቻ ስታካሂድበት ለነበረ ህዝብ ዛሬ ተቆርቋሪ መምሰሏ፣ ይህንኑ ዘንግተው ” አሜሪካ እንዲህ አለች ብለው በሚደንሱ ደነቋቁርቶች” ክፉኛ ማዘናቸውን የገለጹት አስተያየት ሰጪ ” አሜሪካ ወልቃይት ጠገዴን ጨምሮ በግፍ ከአማራ ክልል በፖለቲካ ውሳኔ የተወሰዱ አካባቢዎችን ወደ ትግራይ ተመልሰው እንዲካተቱ ግፊት ላይ መሆኗን አውቃለሁ። እዚህ ላይ ብንነቃና በብልሃት ብንጓዝ ይሻላል” ብለዋል።

እግር ቀንሰው የነበሩት ማይክ ሃመር ኢትዮጵያ ብሪክስን ከተቀላቀለች በሁዋላ ወድ ምስራቅ አፍሪቃና አውሮፓ በመመላለስ በዚሁ ጉዳይ ላይ ሲወሳወሱ መቆየታቸውን አንዳን ሚዲያዎች መዘገባቸው የሚታወስ ነው። በድጎማ የሚሰሩት ሚዲያዎች በተለየ ልዩ ቅድሚያ በመስጠት አሜሪካ የአማራ ክልል ሁኔታ እንዳሳሰባት ሲገልጹ መሰነበታቸውም ይታወሳል።

ትህነግ በአሜሪካ ቀጥተኛ ጫና ከሞት ተርፎ በአቶ ጌታቸው አማካይነት ትግራይን ዳግም በጊዚያዊ አስተዳደር ስም ለማስተዳደር ከበቃ በሁዋላ በተደጋጋሚ ሁሉም ነገር ወደ ቀደመው አስተዳደር ይዞታ እንደሚመለስ እየገለጸ ነው። ከጦርነቱ መነሻ ጀመሮ የሳሳም ቢሆን ያለውን ሃይል ወልቃይት ላይ አፍሶ መንገዱን የቀረቀረው የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን በህዝብ ፍላጎት እልባት ለመስጠት ሃሳብ እንዳለው ከማስታወቁ ሌላ ቅቶ ጌታቸው እንደሚሉት ለማድረግ ሲነቀስቀስ አልታየም። የወልቅይት ጠገዴና ሁመራ አካባቢ አመራሮችም በዚህ በኩል በግልጽ መንግስትን በጥርጥር ስለማየታቸው ያሰሙት ነገር የለም።

See also  ኤፍ ኤም ጣቢያዎች የውጭ አገር ፕሮግራሞችን ሊንክ አድርጎ ማሰራጨት ተከለከሉ

ኢትዮጵያ ብሪክስ እንዳትገባ ከደቡብ አፍሪካ መሪ በሴራ ይሁን በሌላ ለጊዜው ግልጽ ባልወጣ ሚስጢር የኢትዮጵያ ማመልከቻ ሩሲያ በሚካሂደው በቀጣዩ ጉባኤ እንዲታይ ተደርጎ ነበር። ይህ ከመሆኑ ቀድሞ በኢትዮጵያዊያን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ብሪክስ የመግባቱ ጉዳይ እንደማይሳካላቸው ሲገልጹም ነበር። በመጨረሻ በዝርዝር ባልተገለጸ ጥረትና ትንቅንቅ ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ይፋ ሆነ። መንግስት ዜናውን ከፍተኛ ድል እንደሆነ በተደጋጋሚ በብስራት ዜና ሲያሰማ ቅር ያላቸውም ባላቸው መድረክ ምክንያታቸው ግልጽ ባይሆንም ሊያጣጥሉ ሲሞክሩ ታይቷል።

አሜሪካ ትልቁን በጄኖሳይድ የማስፈራሪያ ክስ የሚያንቀውንና ኢትዮጵያን የኢኮኖሚያዊ መኮማተር ላይ የሚጥለውን ማዕቀብ አንስቶ የቪዛ እገዳና የአጎዋ ተጠቃሚነትን የሚከለክለውን ህግ ለአንድ ዓመት ማራዘሙ ያስገረማቸው ዜናውን “የሚጣረስ” ሲሉት የገለጹት ከላይ በተጠቋቆሙት ምክንያቶች ነው።

የብሪክስ በረከቶች የፖለቲካውን ሳይጨምር ብድር የማግኘት፣ በህብረቱ አባላት መካከል ሸቀጥን የመግዛትና የመሸጥ ግንኙነትን የሚያጎናጽፍ እንደሆነ ለአብነት የሚጠቅሱ ይህ እንዲራዘም የታዘዘው ህግ ጉዳት ቢኖረውም በተዘረዘሩት የብሪክስ አዳዲስ በረከቶች የሚተኩ ስለመሆናቸው ዓለም ዓቀፍ ተንታኞች ሰሞኑንን ይሰጡት ከነበረው መረጃ ለመረዳት ይቻላል።

የውሮፓ ህብረት ውስጥ ያሉ አንዳንድ አካልት ብሪክስን የተቀላቀሉ አገራት መፍረስ እንዳለባቸው ዛቻ እየሰነዘሩ መሆኑንን የሚጠቅሱ ወገኖች፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የተነሳው ግጭት ወደ ጠረጴዛ ንግግር እንዲመጣ ሁሉም ወገን በሚችለው ሁሉ ግፊት ሊያደርግ እንደሚገባ አመልክተዋል።

የኤትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል የአፍሪካ አገሮችን ጠቅልሎ የመውሰድ ያህል እንደሆነ ተደርጎ በሚነገርበት በአሁኑ ወቅት የጂ 20ን ህብረት አፍሪካ እንድትቀላቀል በይፋ ግብዣ ደርሷታል። ይህ ብቻም አይደለም የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ አፍሪካ ድምጽን በድምጽ በመሻር ሃይል እንድትወክል አስገዳጅ አቅም እንደሆነ ዓለም ዓቀፍ ተንታኞችና ዩቲዩበሮች በስፋት ዝርዝር መረጃ እያቀረቡ ነው።


Leave a Reply