በሃይማኖታዊ እና ሕዝባዊ በዓላት፤ በብልጽግና ፓርቲ ሥልጠና የክልሉ ሕዝብ ላሳየው ፍቅር፣ ትብብር እና የጋራ ኀላፊነት ስሜት የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ምሥጋና ካቀረበ በሁዋላ ነው የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ የሰዓት ማሻሻያውን ያስታወቀው።
” ባህር ዳር ከተማ በከፍተኛ ከበባ ውስጥ እንደምትገኝ ህዝባዊ ሃይሉ አስታውቋል።ከተማዋን በቀላሉ ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ሁኔታዎች በመኖራቸው …” በሚል ምናላቸው ስማቸው የንቅናቄውን አመራሮች ዋቢ አድርጎ አስጠንቅቆ ነበር። መንግስትም ተስፋ መቁረጡን፣ እንዲሁም 23ኛ ክፈለጦር ሙሉ በሙሉ መደምሠሱንም ምናላቸው ስማቸው በህዝብ ግንኙነት ደረጃ አስታውቆ ነበር።
ሌላው የህዝብ ግንኙነት ዓይነት መረጃ የሚሰጠው ደረጀ ከባህር ዳር ከአንድ የንቅናቄው የጦር አመራር ጋር በቀጥታ ስርጭት ባደረገው ውይይት መሳሪያ መጨረሳቸውን፣ ተጨማሪ ፋኖ የመጣል ቢባልም እንዳልደረሰ፣ ዘመነ ካሴ አለ በሚባልበት (አዴት ግድም ነው) መንግስት የከፋ ድብደባ መፈጸሙ፣ በቋሪት አቅጣጫም ሃይል አጠንክሮ በከባድ መሳሪያ እያጠቃ መሆኑን ተናጋሪው ካስታወቀ በሁዋላ ” በግለሰቦች ቤት መሳሪያ ያለው ሁሉ መሞቱ ስለማይቀር እንዲዋጋ ቢደረግ” ሲል ተደምጧል። መረጃው አሜሪካ ያለው ምናላቸው በቋሪት በኩል የመከላከያ ሃይል እየተደመሰሰ ነው ካለው መረጃ ጋር የሚቃረን በመሆኑ ደረጄ ” መረጃው የተለይ ሆኖብኛል” ለማለት ሲገደድ ለመስማት ተችሏል።
የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ በክልሉ በርካታ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረውን የሰላም መደፍረስ ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን አስታውሶ፣ ጥቅምት 10/2016 ዓ.ም የክልሉን ወቅታዊ የሰላም ኹኔታ በጥልቅ የገመገመው የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ማሻሻያዎችን ማድረጉን ነው ያመለከተው።
የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኅላፊ እና የኮማንድ ፖስቱ አባል መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) በሰጡት መግለጫ የሰዓት እላፊ ገደብ ማሻሻያው እንደየ አካባቢው ተጨባጭ ኹኔታ የሚወሰን ይኾናል ብለዋል። ይህንን ተከትሎም በጎንደር እና ደብረ ብርሃን የተሽከርካሪ ስዓት እላፊ ገደብ ባለበት የሚጸና ኾኖ ለሰው እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት መንቀሳቀስ የሚያስችል ማሻሻያ ተደርጓል።
ባሕር ዳር ከተማ ተሽከርካሪ እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት እና ለሰው እስከ 3: 00 ሰዓት ድረስ መሻሻሉን ዶክተር መንገሻ ጠቁመዋል። ዶክተር መንገሻ በመግለጫቸው በክልሉ በርካታ ከተሞች እየታየ ባለው የህዝብ ድጋፍና የጸጥታ መሻሻል ወደፊትም ተመሳሳይ የሰዓት ማሻሻያ ሊደረግ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል።
ከጦርነት ያላገገመው የአማራ ክልል በሚቻለው ሁሉ ሰላም እንዲወርድ ጠብመንጃ ያነሱ ወገኖች ሁሉ ወደ ድርድር እንዲያመሩ አቅሙ ያላቸው በሙሉ ሊሰሩ እንደሚገባ፣ ውጭ ተቀምጠው ጦርነት የሚቆሰቁሱና ንግድ የሚያጧጡፉ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ህዝብ ጫና እንዲያደርግ በርካቶች እየጠየቁ ነው። የአማራ ክልል ጦርነት ለዩቲዩብ ነጋዴዎች ሲሳይ የሆነ ሲሆን፣ ለጦርነቱ ምዋጮ እንሰበስባለን የሚሉና ” ሚዲያዬን፣ አገልግሎቴን እርዱ” በሚሉ የደም ነጋዴዎች ኪስ ማደለቢያ መልካም አጋጣሚ እንደሆነ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። እነዚህ ወገኖች ብህዝብ ደም፣ እልቂትና መፈናቀል ንግድ በመስከራቸው ጦርነቱ እንዲቆምና ንግግር እንዲጀመር የሚሰሩ አካላት ላይ የተባበረ ክንዳቸውን እንደሚያሳርፉ፣ ቤተሰብና ዘመድ አዝማድ ሳይቀር የማቆሸሽ ዘመቻ እንደሚያካሂዱ በተደጋጋሚ የታየ ሃቅ ነው። እነዚህ ወገኖች “ግፋ በለው” አቁመው መንግስትም ሆነ ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲያመሩ ጫና ቢፈጥሩ ንግዱ ስለሚቆምባቸው አያስቡትም ሲሉ በደንብ የሚያውቋቸው ይገልሳሉ። ሰሞኑንንበገንዘብ የተነሳው ጸብም የዚሁ ማሳያ እንደሆነ ያመልክታሉ።
- የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስአንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ የልብ በሽታና በደም ዝውውር ማነስ ምክንያት ለሚከሰት የአዕምሮ ሥራ መታወክ (ስትሮክ) የመጋለጥ… Read more: የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
- የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶችየስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ የህመም አይነት ነው። በዋናነት አራት የስኳር ህመም አይነቶች አሉ፤ እነርሱም… Read more: የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
- ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮ ጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል። ትዳርንም ሊያፈርስ ይችላል። “ስለ ባለቤቴ… Read more: ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New Development Bank. In a media briefing regarding… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከሃምሳ ሺህ… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”