“ቤተክርስቲያን ጦርነት አታውጅም። በቤተክርስቲያን ስም ክፉ ነገርን መቀስቀስና ምዕመናንን ማባላት አይገባም” ሲሉ የሰሜን ወሎ ሀገረ ሥብከት ሊቀ ጳጳስ እና የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ተናገሩ። “በጦርነት የሚገኝ ሰላም የለም” እንደሌለም አመልክተዋል።
“እንደ ሃይማኖት አባት ሀገር እና ሃይማኖትን እናድናለን እንጂ ለማባላት አንሠራም” ማለታቸውን አሚኮ በስፍራው ተገኝቶ ያጠናከረው ሪፖርት ያስረዳል። ሰው በመግደል ችግሮችን መፍታት እንደማይቻልም አምልክተው ነው “ቤተክርስቲያን ጦርነት አታውጅም፤ በቤተክርስቲያን ስም ክፉ ነገርን መቀስቀስ እና ምዕመናንን ማባላት እንደማይገባም” ሲሉ ያሳሰቡት።
ብጽዕነታቸው ይህን ያሉት በላሊበላ ከተማ አሥተዳደር በወቅታዊ የሰላም ጉዳዮች ዙሪያ በተካሄደ ውይይት ላይ ተገኝተው ነው።በውይይቱ
ዘላቂ ሰላምን ለማጽናት ችግሮችን መፍታት፣ በመከራ ውስጥ ያሉትን መታደግ፣ ተፈናቅለው በችግር ውስጥ ያሉትን ማቋቋም እንደሚገባ አመልክተዋል። ሕዝብ ከመንግሥት የመፍትሔ ሀሳብ እንደሚሻ ጠቁመው “መንግሥት ባለበት ሀገር ወደ ፌዴራል ከተማ ለመግባት መከልከል፣ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው እየተፈናቀሉ መውጣት ብዙዎችን አስቆጥቷል፤ ይሄን ስህተት መታረም አለበት” ሲሉ እርምት ሊደረግበት የሚገባውን ጉዳይ አመላክተዋል። በቅዱስ ላሊበላ ጉዳይ መስተካከል ያለበትንና የሚወገዘውን ጉዳይ አውግዘዋል። መክረዋል። አስጠንቀቀዋል።
“የተቀደሰን ሥፍራ የጦርነት ቦታ ማድረግ ነውር ነው” ያሉት ብጽዕነታቸው ። ” ደብሩ ውስጥ ቀሳውስት፣ መነኮሳት፣ ዲያቆናት እና ምዕመናን ይከትሙበታል እንጂ የሚታኮሱ ሰዎች ሊከትሙበት አይገባም” ሲሉ ነቅፈዋል። “ቤተክርስቲያን በላሊበላ ከተማ ደወል መትታ ጥል አስነስታለች” የሚባለው የተሳሳተ አካሄድ ነውር መኾኑንም አም፤ልክተዋል። ይሄን የሚሉና በተባለው የሚያምኑ ከሕሊናቸው ሊፍቁልን እንደሚገባ ገልጸዋል። “የተቀደሰውን እና የቃል ኪዳን ቦታ የኾነውን የማይመጥን ድርጊት አውግዘናል፤ እናወግዛለንም” ሲሉ ፊትለፊት ተናግረዋል።
በጦርነት ሰላም እና መረጋጋት አይገኝም ብለዋል። ላሊበላ እንደሌሎቹ ከተሞች ከተማ ብቻ አይደለም ያሉት ብፁዕነታቸው የቅዱሳን ከተማ ነው፤ የቅዱሳን ከተማን በቅድሥና መጠበቅ ይገባል ነው ያሉት። የሃይማኖት ቦታዎች ላይ ጥንቃቄ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል። ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብቶ መተኮስ የተወገዘ መኾኑንም ተናግረዋል።
በንጹሓን ወገኖች ላይ የሚደረግ ዘረፋ፣ ቅሚያና ግድያ መቆም ይገባልም ብለዋል። ሕግን በማስከበር ሂደት የሚፈጸም ስህተት ካለ መሥተካከል እንደሚገባውም ገልጸዋል። መከላከያ ሠራዊትን መጥላት ማለት ሀገርን መጥላት ነው፤ እኛ የምንፈልገው የድሮው ልዕልናው ተመልሶ ማየት ነው፤ የኮሪያን፣ የሩዋንዳን፣ የሶማሊያን እና የሌሎችን ሀገራት ሰላም ያስከበረውን መከላከያ እንሻለን፤ መከላከያን አንጠላም፤ እናከብራለን፤ ቤተክርስቲያን መከላከያን ትጥላለች የሚባለው ውሸት ነውም ብለዋል።
መንግሥት ችግሮችን መፍታት እንጂ ማድበስበስ እንደማይገባውም ተናግረዋል። አሁን ባለው የጸጥታ ችግር ተፈናቃይ ወገኖች ጠያቂ እንዳጡም ገልጸዋል።
የሀገር መከላከያ ሰራዊትን እየጠሉ ሀገሬን እወዳለሁ ማለት ስህተት መኾኑንም ተናግረዋል። የፖለቲካ ሰዎችም ስህተቶቻቸውን እያረሙ፣ ችግሮችን እየፈቱ ሕዝብን ጠብቀኝ ማለት አለባቸውም ብለዋል።
እንደ ሃይማኖት አባት ሀገር እና ሃይማኖትን እናድናለን እንጂ ለማባላት አንሠራም ነው ያሉት። ሰው በመግደል ችግሮችን መፍታት እንደማይቻልም ተናግረዋል። ቤተክርስቲያን ጦርነት አታውጅም ያሉት ብፁዕነታቸው በቤተክርስቲያን ስም ክፉ ነገርን መቀስቀስ እና ምዕመናንን ማባላት እንደማይገባም አሳስበዋል።
“በጦርነት የሚገኝ ሰላም የለም” ያሉት ብጹዕነታቸው በጦርነት ጥቂት ጊዜ መቆየት ይቻል ይኾናል፤ ነገር ግን ዘላቂ ሰላም እንደማይገኝ መክረዋል። “ክርስቶስ አዳም ቢበደል ከሰማይ ወርዷል” ያሉት ብፁዕነታቸው መንግሥት ዝቅ ብሎ የወደቁትን ማንሳት፣ የተሳሳቱን መመለስ አለበት ነው ያሉት። ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚገባም አመላክተዋል። እኛ ሰላም የምንሰብከው ተላላኪዎች ሆነን ሳይኾን ሃይማኖቱ የሚያዝዘውን እና ሰላም ስለሚጠቅም ነውም ብለዋል።
የተቀደሰን ሥፍራ የጦርነት ቦታ ማድረግ ነውር መኾኑንም ገልጸዋል። ደብሩ ውስጥ ቀሳውስት፣ መነኮሳት፣ ዲያቆናት እና ምዕመናን ይከትሙበታል እንጂ የሚታኮሱ ሰዎች ሊከትሙበት አይገባም ነው ያሉት። ቤተክርስቲያን በላሊበላ ከተማ ደወል መትታ ጥል አስነስታለች የሚባለው የተሳሳተ አካሄድ ነውር መኾኑንም ገልጸዋል። ይሄን የሚሉና በተባለው የሚያምኑ ከሕሊናቸው ሊፍቁልን ይገባል ብለዋል። የተቀደሰውን እና የቃል ኪዳን ቦታ የኾነውን የማይመጥን ድርጊት አውገዘናል፤ እናወግዛለንም ነው ያሉት።
በጦርነት ሰላም እና መረጋጋት አይገኝም ብለዋል። ላሊበላ እንደሌሎቹ ከተሞች ከተማ ብቻ አይደለም ያሉት ብፁዕነታቸው የቅዱሳን ከተማ ነው፤ የቅዱሳን ከተማን በቅድሥና መጠበቅ ይገባል ነው ያሉት። የሃይማኖት ቦታዎች ላይ ጥንቃቄ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል። ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብቶ መተኮስ የተወገዘ መኾኑንም ተናግረዋል።
በንጹሓን ወገኖች ላይ የሚደረግ ዘረፋ፣ ቅሚያና ግድያ መቆም ይገባልም ብለዋል። ሕግን በማስከበር ሂደት የሚፈጸም ስህተት ካለ መሥተካከል እንደሚገባውም ገልጸዋል። መከላከያ ሠራዊትን መጥላት ማለት ሀገርን መጥላት ነው፤ እኛ የምንፈልገው የድሮው ልዕልናው ተመልሶ ማየት ነው፤ የኮሪያን፣ የሩዋንዳን፣ የሶማሊያን እና የሌሎችን ሀገራት ሰላም ያስከበረውን መከላከያ እንሻለን፤ መከላከያን አንጠላም፤ እናከብራለን፤ ቤተክርስቲያን መከላከያን ትጥላለች የሚባለው ውሸት ነውም ብለዋል።
እባካችሁ ስለ ሰላም እንሥራ፤ ሰላም ይጠቅመናል፤ ከሞት እና ከችግር ይታደገናልም ብለዋል። ምዕመናን ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጀው መሠረት ለሀገር ሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት እንዲጸልዩ፣ ምሕላ እንዲያደርጉም ብጹዕነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።
- ሰው ሰራሽ ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን መቀላቀል የኢትዮጵያ ሌላ አማራጭ?አርተፊሻል ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ኢትዮጵያ የባህር በር ሊኖራት ይችላል፤ ይህ በአለም ላይ በኢትዮጵያ የአፋር ምድር ረባዳነት የተነሳ ተፈጥሮ የሰጠው እድል ነው! በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል አርተፊሻል ቦይ በመስራት ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት መሆን ትችላለች፡፡ እንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሊፈጠር የቻለው፤ የኢትዮጵያ የአፋር ቦታ ከባህር ወለል በታች እስከ 110 … Read moreContinue Reading
- ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ቁጥጥሩን አጠንክሮ እንደሚገፋበት አስታወቀ፤ ህገወጥ የወርቅ አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ በአገሪቱ የሚታየውን የዋጋ አለመረጋጋት ለመግራት የግንዘብ ስርጭት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ የተጀመረው ስራ ውጤት እያሳየ መሆኑ ተመለከተ፤ ተጠናክሮ ክምሩ እንደሚሰራበትና ግሽበትን በዓመቱ መጨረሻ 20 ከመቶ ለማድረስ መታቀዱ ተሰማ። ህገወጥ የወርቅ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና የማበረታቻ መደረጉ ለውጥ ቢያሳይም በቂ እንዳልሆነ ተመለከተ። … Read moreContinue Reading
- የኮሚሽኑ የቀድሞ ሠራተኞች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የሙስና ክስ ጋር ተያይዞ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ሆነየአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የቀድሞ ሠራተኞች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የአልባሳት ግዢ ጋር ተያይዞ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ተደረገ። ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ … Read moreContinue Reading
- መንግስት የነዳጅ ድጎማን በህገወጥ መንገድ ሲጠቀሙ ነበሩ ያላቸውን 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከስርአቱ አስወጣ፣ የሰርቁትን ይከፍላሉየታለመለት የነዳጅ ድጎማን ላልተገባ ዓላማ ሲጠቀሙ የነበሩ 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ስርዓቱ እንዲወጡና ዕዳ እንዲከፍሉ መደረጉን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ። ሚኒስትሯ ይህን ያሉት የመንግሥት የ2016 የመጀመሪያ የሩብ ዓመት አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት ነው። የግምገማው ተሳታፊዎች መንግሥት የነዳጅ ድጎማን ጨምሮ በርካታ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋገጡ ተግባራትን ማከናወኑን አድንቀው፤ ሆኖም” ድጎማው … Read moreContinue Reading
- በዓመት አምስት ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ የሚያመርተው ፋብሪካ ከመጋቢት በሁዋላ የሲሚንቶ ዋጋ ወደ ነበረበት የሚመልሰ ነውበቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንዲያመርት እቅድ ተይዞለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ እየተገነባ ያለውን የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የግንባታ በመጋቢት ወር ይጠናቀቃል። ምርቱ በተባለው ወር ሲጀምር የሲሚንቶ ዋጋ አሁን ካለበት በግማሽ እንደሚወርድ ይጠበቃል። ከመጋቢት በሁዋላ ፋብሪካው በ50 በመቶ የሲሚንቶ እጥረቱን ያስወግዳል። ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ኩባንያ … Read moreContinue Reading