ከ750 በላይ የሕወሃት ልዩ ሃይል፣ ፖሊስና ሚሊሻ አባላት ከተሐድሶ ስልጠና በኋላ ወደየ አካባቢያቸው ሊመለሱ ነው

ከ750 በላይ የቀድሞ የሕወሃት ልዩ ሃይል፣ ህዝባዊ ፖሊስና ሚሊሻ አባላት ከተሐድሶ ስልጠና በኋላ ወደየ አካባቢያቸው ተመልሰው መደበኛ ህይወታቸውን ይመራሉ።

የሕወሃት ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመውን ክህደት ተከትሎ በተደረገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት በርካታ የቀድሞ የሕወሃት ታጣቂዎች ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን ሰጥተዋል።

ከነዚህም መካከል በአፋር ክልል አዋሽ አርባ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል 764 የቀድሞ የሕወሃት ልዩ ሃይል፣ ፖሊስና ሚሊሻ አባላት በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ድጋፍ የተሃድሶ ስልጠና ሲሰጣቸው ቆይቷል።

የኮሚሽኑ ጽህፈት ቤት ሃላፊና የተሃድሶ ስልጠናው አስተባባሪ አቶ ዘሪሁን ዘውዴ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አብዛኛው ሰልጣኞች ከግብርና ስራ ላይ ተገደው ወደ ውጊያ የተሰማሩ አርሶአደሮች እንደሆኑ ገልጸዋል።

ከፖሊስና ሚሊሻ አባላቱ በርካቶቹ በፅንፈኛው የሕወሃት ቡድን ጠባብነትና ተገፊነት እኩይ አስተሳስቦች ሰለባ በመሆናቸው የተሃድሶ ስልጠና ማስፈለጉን ገልጸዋል።

በዚህም ወጣቶች የአገራዊ ለውጡን ምንነትና የህግ ማስከበር ሂደት የአቅም ግንባታና የአስተሳስብ ለውጥ ላይ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን አቶ ዘሪሁን ተናግረዋል።

የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እጅ ከሰጡበት ጊዜ ጀምሮ ከሎጀስቲክስ ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ አድርጎ በአዋሽ አርባ የተሐድሶ ስልጠና ሲወስዱ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይም ወደየ አካባቢያቸው ተመልሰው ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው መደበኛ ህይወታቸውን ይመራሉ ብለዋል።

ሰልጣኞቹ ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ የተለየ ሁኔታ ጥፋት የፈጸሙ ካልሆኑ በስተቀር ቀሪዎቹ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱና በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲደገፉ ይደረጋል ነው ያሉት።

ከመጀመሪያው ምዕራፍ ስልጠና በተጨማሪ ሌሎች ተጨማሪ ስልጠናዎች ተሰጥተው በቀጣይ ሶስት ሳምንት ተጠናቆ አባላቱ ወደየ አካባቢያቸው ይመለሳሉ።

የትይግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ነብዩ ስሁል በበኩላቸው እየተሰጠ ያለው ስልጠና የአባላቱን አቅም ለመገንባት፣ ህዝብና አገራቸውን የሚክሱበትና ራሳቸውን የሚለውጡበት እንደሆነ ገልጸዋል።

ስልጠናው በጥሩ ሂደት ላይ መሆኑን ገልጸው፤ ሲጠናቀቅም በቅርቡ በነጻነት ተንቀሳቅሰው ህይወታቸውን መምራት ይጀምራሉ ብለዋል።

የጋራ አስተሳሰብ በመያዝ የአገርን ብልጽግና ለማረጋገጥ፤ እንዲህ አይነት የተሀድሶ ስልጠናውን ላላገኙት ይሰጣልም ነው ያሉት።

(ኢዜአ) 

  • የተጠልፈቸው ጸጋ በላቸው ነጻ ሆነች፤ ጠላፊው አልተያዘም
    ወይዘሪት ፀጋ በላቸውን ከተጠርጣሪው ግለሰብ ማስጣል መቻሉን የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ። የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በተደረገው የተቀናጀ የፀጥታ ኦፕሬሽን በተጠርጣሪው ግለሰብ የተጠለፈችውን ወይዘሪት ፀጋ በላቸውን ማስጣል መቻሉን ተናግረዋል። ግንቦት 15 ቀን 2015 ከመደበኛ ስራዋ ወጥታ ወደቤቷ ስታቀና ተጠርጣሪው ግለሰብContinue Reading
  • ፌደራል ፖሊስ ሆን ብለው ሐሰተኛ መረጃ በሚያሰራጩ አካላት ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል አለ
    ሆን ብለው ሕብረተሰቡን ለማሳሳት ሐሰተኛ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። ተቋሙ አገራዊ ለውጡን ተከትሎ መንግስት ለህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ከወሰዳቸው እርምጃዎች መካከል የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈፀምበት የነበረውን ማዕከላዊ የወንጀል ምርመራን መዝጋት መሆኑንና ይሄንን ተከትሎ በፖሊስ የወንጀል ምርመራ ስራ ላይ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበትContinue Reading
  • ኢሰመኮ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች የጸጥታ ሃይሎችን ጨምሮ ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታወቀ
    በሸገር ከተማ ከመስጊዶች መፍረስ ጋር ተያይዞ የተነሱ ተቃውሞዎችን እና የደረሰ ጉዳትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በተለይም በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድ ውስጥ እና በተወሰኑ አካባቢዎች በሸገር ከተማ በመንግሥት አካላት ከፈረሱ መስጊዶች ጉዳይ ጋር ተያይዞ የተነሱ ተቃውሞዎችን ተከትሎ የደረሰውን የሰዎች ሞት እና ጉዳቶችን በተመለከተContinue Reading
  • አዲስ አበባና በሸገር ከተሞች የፈረሱትን ቤቶችና ማህበራዊ ቀውስ አስመልክቶ ኢሰመኮ መገለጫ አወጣ
    በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተሞች እየተካሄደ ነው ባለው የቤት ፈረሳ እና የግዳጅ የማስነሳት ሂደት 111 ሺህ 811 ቤቶች መፍረሳቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) አስታወቀ። ኢሰመጉ ይህንን የገለጸው ከጥቅምት 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በጉዳዩ ላይ ያካሄደውን የምርመራ ሪፖርት ግንቦት 23/2015 ዓ.ም. ይፋ ባደረገበት ጊዜ ነው። ኮሚሽኑ ይህንን አሃዝ ይፋContinue Reading
See also  ያልተነቀለው ሰንኮፍ "ትህነግ" - ዩሪ ቢስሜኖቭ እንዳለው፣ እኛም እንዳየነው...

Leave a Reply