የዓድዋ ማስታወሻ! – በላይ ባይሳ


…ትርጉሙ ብዙ ነው – የዓድዋ!…. ለዓለም አሻራ!
ለአፍሪካ ቅርስና ኩራት!
ለጥቁር ሕዝቦች ታሪክ!
ለኢትዮጵያ ዘመን ተሻጋሪ ገድል ነው! …. ዓድዋ!

ለዓለም አሻራ!
ለአፍሪካ ቅርስና ኩራት!
ለጥቁር ሕዝቦች ታሪክ!
ለኢትዮጵያ ዘመን ተሻጋሪ ገድል ነው! …. ዓድዋ!

እንደድር-ያበረ የአንድነት ማስታወሻ!
የዓብሮነት መዘከሪያ!
የተባበረ ክንድ፣
ያልበገር ባይነት መንፈስ ማደሻና ማፅኛ ነው!… ዓድዋ!

የደማቅ ታሪክ ቱባና ዘለላ፣
የጥንካሬ መቀነት፣
ባለብዙ ህብረ-ቀለም፣
የማንነት ውበት አንጓ፣
የአሸናፊነት መገለጫ፣
የድል መቀናጂያ፣
የነፃነት ዋንጫ ጌጥ ነው… ዓድዋ!

በፈረስና ፈረሰኞች ገድል የደመቀ!
በጀግኖች አባቶቻችን አጥንትና ደም ለትውልድ የተከፈለ ውድ ዋጋ ነው! … ዓድዋ!

በደልን አስቀርቶ!
ፍትህን ያሰፈነ!
ትዕቢትን ያዋረደ!
ጠላትን ያሳፈረ!
ወገቡን የሰበረ!
የበላይነትን የተፍለመ!
ቅኝ ቀዢዎችን አንገት ያስደፋ!
እኩልነትን አቀንቅኖ!
አፍሪካን ለህብረት ያነሳሳ፣ ያሰባሰበ!
ለፖን-አፍሪካኒዝም መሠረት የጣለ… ጥንስስ ነው…. ዓድዋ!

በጥልቅ የአመራር ጥበብ፣ የጦር ስልትና ዜማ የተቃኘ!
ባልበገር ወኔ፣ ፉከራና ሽለላ የታጀበ!
በፈጣሪ ክንድ የተደገፈ! በጠንካራ የእምነት መንፈስ የዳበረ… የደረጀ ቱባ ትውፊት!
በዓለም አዲስ ታሪክ ሰርቶ ብዙ ያስተማረ ትምህርት ቤት ነው….. ዓድዋ!

ሁል ጊዜ የማያረጅ አዲስ!
የሩቅ ትዝታ ሳይሆን የቅርብ!
ከደማችን የተዋሃደ!
ከመንፈሳችን የተጋባ!
ትኩስ የማይደበዝዝ ድል! የሚናፈቅ ታሪክ ነው…. ዓድዋ!

የአባቶቻችን የእውነትና የእምነት ውርስ አደራ እና አሻራ ማስታወሻ ነው… ዓድዋ!

የድል ብስራት!
የነፃነት መጎናፀፊያ ልብሳችን!
ባለብዙ የፍትህ ትርጉም ፊደል ነው…. ዓድዋ!

በላይ ባይሳ
✍️ የካቲት 23/2013 ዓ.ም

See also  የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? "ወያኔ ነኝ"

Leave a Reply