ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ባስተላለፉት መልዕክት ʺትህነግ ላለፉት 30 ዓመታት በአማራ ላይ ላደረሰችው ግፍና መከራ ተመጣጣኝ ካሳ ለተጎዳው ሕዝባችን ያስፈልገናል” ነው ያሉት፡፡

ትህነግ በማይካድራ፣ ሁመራ፣ ወልቃይት፤ ጠገዴ፣ ዳንሻ፤ ራያ፣ አላማጣ፣ ኮረም እና በሌሎች አካባቢዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ አፈናቅላለች ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ።

ተቆጥረው በማያልቁ የጀምላ መቃብሮቿ ሺዎች በጀምላ ተቀብረዋል፤ በቅርቡ በሺህ የሚቆጠሩ ንጹህ የአማራ ተወላጆች በማይካድራ በግፍ በጅምላ ተቀብረዋል፣ በሺህ የሚቆጠሩ ህጻናት ወላጅ አልባ ሆነዋል፣ አዛውንቶች ጧሪ ቀባሪ የላቸውም፤ ሚሊዮኖች ተሰደዋል፤ በርካታ ወጣቶች የት እንደደረሱ አይታወቅም ነው ያሉት።

ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ በሚሊዮን የሚቆጠረው አማራ በቋንቋው አይናገርም፣ አይማርም፣ ባህልና ወጉን ተነጥቋልም ብለዋል። ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ሳይቆጠር ተዘሏል ወይም ተቀንሷልም ብለዋል።

የአማራ ሕዝብ በኢኮኖሚ አሻጥር ደሀ ሆኖ እንዲኖር ተደርጓል ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ታዲያ ለዚህ ሁሉ ግፍ ተከፍሎ የማያልቅ እዳ ያለበት ወገን እንዴት መልሶ ሊከሰን ሲዳዳ እንኳን አያፍርም? ሲሉም መጠየቃቸውን ከአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ባሕር ዳር፡ የካቲት 24/2013 ዓ.ም (አብመድ)

Leave a Reply