በአራት መጋዘን የተከማቸ የምግብ ዘይት በነዋሪዎች ጥቆማ በቁጥጥር ስር ዋለ

በጉለሌ ክ/ከተማ አራት መጋዘን አለአግባብ የተከማቸ የምግብ ዘይት በተቋቋመው ግብረሃይል በቁጥጥር ስር ዋለ

በዛሬው እለት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ስሙ ሙሉጌታ መናፈሻ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በህብረተሰቡ ጥቆማ በአራት መጋዘን ውስጥ በርካታ መጠን ያለው የምግብ ዘይት ክምችት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እየሰራቸው ካሉ በርካታ ሌሎች ስራዎች በተጨማሪ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ግብረሃይል በየአካባቢው ሰፊ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል።

አሁንም ቢሆን ቁጥጥሩ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንና የከተማው አስተዳደር እያስታወቀ የከተማው ነዋሪም እንደተለመደው ጥቆማዎችን በማቅረብ የጋራ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡

አጠቃላይ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ሰው ሰራሽ የዋጋ ውድነት በመፍጠርና ምርቶችን በመደበቅ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ህገወጥ ደላሎችንና ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከትናንት በስትያ ግብረ ሃይል አቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወሳል፡፡

(ኢ ፕ ድ)

See also  ትህነግ አማራ በተጨፈጨፈ ማግስት አዲስ አሳብ ያልያዘ ስልታዊ የድርድር መግለጫ ሰጠ

Leave a Reply