“ድፈሩ፣ዝረፉ፣አግዙ፣አውድሙ… ተብለናል፤ የያዝናቸውን ከተሞች አውድመናል፣ የግለሰብ ዕቃና ፋብሪካዎች ዘርፈናል ማሳ አቃጥለናል

ያልደረሰ ማሽላ ለማጨድና ለመውሰድ ስለማይመች ቆርተው ሲጥሉ እንደነበርና የግለሰብ ቁሳቁሶችን በደረሱበት ከተማ ሁሉ በመዝረፍ ወደ ትግራይ ማጋዛቸውን ምርኮኞች አረጋገጡ። አማራና አፋርን አቅም አሳጡ መባላቸውን አምነዋል።

በወረኢሉ፣ ጭፍራ፣አጣዬና፣ ቡርካ ግንባር በተደረገ ውጊያ የተማረኩና በትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር አመራሮች አማራናና አፋርን አጥፉ የሚል መመሪያ እንደሰጣቸው ተናግረዋል። የኢትዮጵያን ሕዝብ መበደላቸውን ጠቅሰዋል።

“ቆቦ ጉብዬ ሃራ ሂዳ ጭፍራ ከሎዋን ቼሊ፣ አሌሌ ሱሊዋ … ሙሉ በሙሉ ንብረት አውድመናል። ሕዝብ ጨፍጭፈናል፣ ወደ ትግራይ የሚጫነውን ንብረት ጭነናል። በተያዙ ከተሞች የፋብሪካ ዕቃዎችን ፈቶ ወደ ትግራይ የሚወስደ ሃይል ጋር ሆነን ማሽን አጓጉዘናል፣ የሆቴሎችንና የግልከሰብ ንብረቶችን ዘርፈናል” ያሉት ምርኮኞች የአርሶ አደር የደረሰ ምርት ሲቃጠል አይተናል” ብለዋል።

“በገባንበት እህል፣ ፍየል እየበላን ማህበረሰቡን አሰቃይተናል። ሕዝቡን እንጨፈጭፍ ነበር። አማራን አፋርን ጨፍጭፉ ተበለን ነበር” ያሉት ምርኮኞች ሙሉ ቃላቸውን ከታች ይመልከቱ። ገጻችንን ፈቃድዎ ከሆነ ላይክና ሰብስክራይብ ያድርጎ

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2653 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply