በዛሬው (ማክሰኞ) የፓርላማ ውሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “ባለፉት ሳምንታት በሰሜን ሸዋ እና በጎጃም ያያችሁት ዝናብ የተፈጥሮ ሳይሆን እኛ ያዘነብነው ነው፤ ዓለም ላይ ያላቸውን ደመናን ወደዝናብ የቀየሩ አገራት ጥቂት አገራት ናቸው፤ እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ መቼ አየዋለሁ ብዬ ከምቀናባቸው ነገሮች አንዱ ይሄ የተከማቸ ደመና በተመረጠ ሁኔታ ማዝናብ መቻልን ነው፤ አሁን ኢትዮጵያ ይሄንን አቅም ገንብታለች፤ ባለፉት ሳምንታት በሰሜን ሸዋ እና በጎጃም ያያችሁት ዝናብ የተፈሮ ሳይሆን እኛ ያዘነብነው ነው፤ በግልጽ በሚቀጥሉት ሳምንታት እናስመርቀዋልን፤ ወይንም እናስጀምረዋለን፤ ኢትዮጵያ ደመናዋን ተጠቅማ ዝናብ ማዝነብ ችላለች” ብለው ነበር። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል።

ይህንየጠቅላይሚኒስትሩንግግርተጨባጭሳይንስነው?

የብሄራዊ ሚትሪዮሎጂ ድርጅት ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ክንፈ ኃይለማርያም ዛሬ ምሽት በነበረው የቢቢሲ ሬድዮ ስርጭት ፥ “… በቤጂንግ ኦሎምፒክ መክፈቻ ቀን ቻይና በዓሉን በብሩሃማ ቀን ለማክበር ብላ ተጠቅማበታለች። ያ ምን ማለት ነው ደመናማ ሆኖ በዛ ቀን ሊዘንብ የነበረውን በቤጂንግ ኦሎምፒክ አካባቢ በዝናብ መልክ ቀድሞ በማበልፀግ መክፈቻውንም መዝጊያውንም በብሩህ ቀን እንዲከበር አድርጋለች” ሲሉ በምሳሌ አስረድተዋል።

ዝናብ ማዝነቡ ድርቅን በማጥፋት ደረጃ እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ክንፈ ዝናብ ማዝነበ ድርቅን በማጥፋት ደረጃ አይደለም ያሉ ሲሆን ድርቅን ማጥፋት ሰፊ ጊዜ የሚወስድ ነው ብለዋል።

አቶ ክንፈ ፥ “ደመናው ከሌለ ዝናቡን ማበልፀግ አይቻልም፤ ደመናውን መፍጠር አንችልም፤ ዝናብ ለማበልፀግ ዝግጁ የሆነ ደመና በተፈጥሮ መምጣት አለበት፤ ሳይንሱም እሱን ነው የሚነግረን ነው” ሲሉ ገልፀዋል።

እንዴት ነው የሚሰራው? ጎጃምና ሸዋ ላይ እንዴት ዘነበ?

እቶ ክንፈ ኃይለማርያም ፦ “…ደመና በትነት መልክ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወደዝናብ ያልተቀየሩ የውሃ ነጠብጣቦች የሚይዝ ነው። እነዛ ተሰብስበው መጠናቸው አድጎ በመሬት ስበት ወደመሬት ዝናብ ሆነው እንዲመጡ መሰባሰብ አለባቸው፤ ያን የሚያሰባስብ ኬሚካል ነው የሚደረገው።

ይህ ከደመናው አይነት ይለያያል እኛ የሞከርነው ውሃ የሚስማማው አይነት ነው። ይህ የጨው አይነት ያላቸው ሶዲየም፣ ፖታሲየም፣ ክሎራይክ፣ ሌላም ናኖ ቴክኖሎጂ የተጨመረባቸው አሉ። 

አንዳንድ ሀገሮች በሮኬት መልክ ይተኩሱታል፤ ለምሳሌ ቻይና፣ አንዳድን ሀገሮች ደግሞ በድሮን ደመናው ጋር ያደርሳሉ ለምሳሌ ኢራን፣ ሌሎች ሀገሮች ከመሬት ግራውንድ ጄኔሬተር ይባላሉ ተራራማ የሆኑ እንደኛ አይነት ሀገራት ደመናው ቅርብ ስለሆነ ንፋስ በሚመጣበት አቅጣጫ ከመሬት ኬሚካሉን በጭስ መልክ በመልቀቅ ወደ ደመናው እንዲደርስ ያደርጋሉ። ዋነኛው በአውሮፕላን የሚረጭ ነው፤ እኛ ባለፈው የሞከርነው በአውሮፕላን የረጨነውን ነው።”

ኢትዮጵያንእያገዙያሉሀገራትእነማንናቸው?

“አሁን ላይ በቴክኒክም በፋሲሊቲም የሚያግዙን የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) መንግሥት እና የሜትሪዮሎጂ ማዕከል ናቸው። ቴክኖሎጂውን አሁን የምንሞክረውን ቀጥታ ከነሱ በመጣ ቴክኖሎጂ ነው ኤር ክራፍቱም ፣ ንጥረ ነገሩም ከነሱ የመጣ ነው። ዋና የሚያስተባብረው እና የሚመራው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው”።

ቀጣዩሙከራየትነውየሚደረገው?

“አሁን Weather Condition ያለው ሻውራ ነው። ሻውራ ማለት ከጣና በስተምዕራብ ነው ያለው። ስለዚህ ከአ/አ እስከ ሻሁራ የተሻለ ደመና የተገኘበት ነው የሚሆነው። ከተቻለ ጥሩ ደመና ካገኘን ቅድሚያ ሰጥተን የምንሞክርበት ከሻውራ ወደ ወልዲያ አቅጣጫ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ጨምሮ ነው። የሚወስነው በአየር ሁኔታ መከታተያ ራዳር የምያገኛቸው የደመና ይዘቶች እና መጠን ነው።”

ምንጭ፦ ቢቢሲ ሬድዮ (Compiled By: Tikvah) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ


Leave a Reply